ዘኍል 14:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእኔ ላይ አድመው በተነሡብኝ በእነዚህ ዐመፀኞች ላይ ይህን ሁሉ አደርግባቸዋለሁ፤ በዚህ ምድረ በዳ የሁሉም መጨረሻ ይሆናል፤ ሁሉም ይሞታሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።’ ” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ፤ ደግሞም አንድ ሆኖ በተነሣብኝ በዚህ ክፉ ማኅበረ ሰብ ሁሉ ላይ እነዚህን ነገሮች አደርጋለሁ፤ መጨረሻቸው በዚሁ ምድረ በዳ ይሆናል፤ እዚሁም ይሞታሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ጌታ፦ በእኔ ላይ በተሰበሰበ በዚህ ክፉ ማኅበር ሁሉ ላይ በእውነት እንዲህ አደርጋለሁ ብዬ ተናገርሁ፤ በዚህ ምድረ በዳ ያልቃሉ፥ በዚያም ይሞታሉ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ እግዚአብሔር፦ በእኔ ላይ በተሰበሰበ በዚህ ክፉ ማኅበር ሁሉ ላይ እንዲህ አደርጋለሁ ብዬ ተናገርሁ፤ በዚህ ምድረ በዳ ያልቃሉ፤ በዚያም ይሞታሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ እግዚአብሔር፦ በእኔ ላይ በተሰበሰበ በዚህ ክፉ ማኅበር ሁሉ ላይ እንዲህ አደርጋለሁ ብዬ ተናገርሁ፤ በዚህ ምድረ በዳ ያልቃሉ፥ በዚያም ይሞታሉ። |
የሚነግርህን በማዳመጥ ለእርሱ ታዘዝ፤ በእርሱም ላይ አታምፅ፤ ለእርሱ ሙሉ ሥልጣን የሰጠሁት ስለ ሆነ የምትፈጽመውን ዐመፅ እየተመለከተ ይቅርታ አያደርግልህም።
ይህም የሆነው “ሁሉም በምድረ በዳ ይሞታሉ!” ብሎ እግዚአብሔር ተናግሮ ስለ ነበር ነው፤ ስለዚህም ከየፉኔ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር ሁሉም ሞተዋል።
ይህ ሁሉ ነገር የደረሰባቸው ለእኛ የማስጠንቀቂያ ምሳሌ እንዲሆን ነው፤ የተጻፈውም በዘመናት መጨረሻ ላይ ለምንገኘው ለእኛ ትምህርት እንዲሆነን ነው።
ከግብጽ ምድር የወጡት ለወታደርነት ብቃት የነበራቸው ወንዶች የእግዚአብሔርን ቃል ባለመስማታቸው ሁሉም እስኪያልቁ ድረስ እስራኤላውያን በበረሓ ለአርባ ዓመት ተጓዙ። ለልጅ ልጆቻቸው ሊሰጥ ለቀድሞ አባቶቻቸው ቃል ገብቶ የነበረውን በማርና በወተት የበለጸገውን ምድር በምድረ በዳ ያለቁት ልጆቻቸው እንደማያዩት አረጋግጦ ነበር።