ካሌብ ግን በሙሴ ፊት ሕዝቡን ጸጥ በማሰኘት “እነርሱን ድል ለመንሣት የሚያስችል በቂ ኀይል ስለ አለን አገሪቱን አሁኑኑ ሄደን እንያዛት አለ።”
ዘኍል 13:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከካሌብ ጋር ሄደው የነበሩት ሰዎች ግን “እኛ በእነርሱ ላይ አደጋ ለመጣል ከቶ ኀይል የለንም፤ በዚያ የሚኖሩት ሰዎች ከእኛ ይበልጥ ብርቱዎች ናቸው” ብለው ተናገሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእነርሱ ጋራ የወጡት ሰዎች ግን፣ “ከእኛ ይልቅ ብርቱዎች ስለ ሆኑ፣ ልናሸንፋቸው አንችልም” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱ ጋር ወጥተው የነበሩት ሰዎች ግን፦ “ከእኛ ይልቅ እነርሱ ብርቱ ናቸውና በዚህ ሕዝብ ላይ መውጣት አንችልም” አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርሱ ጋር የወጡ ሰዎች ግን ፥ “በኀይል ከእኛ ይበረታሉና በዚህ ሕዝብ ላይ መውጣት አንችልም” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱ ጋር የወጡ ሰዎች ግን፦ በኃይል ከእኛ ይበረታሉና በዚህ ሕዝብ ላይ መውጣት አንችልም አሉ። |
ካሌብ ግን በሙሴ ፊት ሕዝቡን ጸጥ በማሰኘት “እነርሱን ድል ለመንሣት የሚያስችል በቂ ኀይል ስለ አለን አገሪቱን አሁኑኑ ሄደን እንያዛት አለ።”
እስከ ኤሽኮል ሸለቆ ሄደው ምድሪቱን ተመለከቱ፤ ነገር ግን ከዚያ በተመለሱ ጊዜ ሕዝቡ እግዚአብሔር ወደ ሰጣቸው ምድር እንዳይገቡ ተስፋ አስቈረጡ፤
ታዲያ እዚያ የምንሄደው ለምንድን ነው? እንፈራለን፤ የላክናቸውም ሰዎች በዚያ የሚኖሩት ሁሉ ብርቱዎችና በቁመታቸውም ከእኛ ይበልጥ ረጃጅሞች መሆናቸውን፥ እንዲሁም ርዝመታቸው እስከ ሰማይ የሚደርስ የግንብ ቅጽሮች ባሉአቸው ከተሞች የሚኖሩ መሆናቸውን ነገሩን፤ እጅግ ግዙፋን የሆኑ የዔናቅ ልጆችንም አይተዋል።’
“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! አድምጥ፤ ከአንተ የሚበልጡትንና በኀይልም ብርቱ የሆኑትን የአሕዛብ ምድርና ቅጽሮቻቸው እስከ ሰማይ የደረሱ ታላላቅ ከተሞቻቸውን ለመውረስ ትገባ ዘንድ ዛሬ ዮርዳኖስን ትሻገራለህ።
ከእኔ ጋር ሄደው የነበሩ ሰዎች ግን የሕዝቡ ልብ በፍርሃት እንዲቀልጥ አደረጉ፤ እኔ ግን ለአምላኬ ለእግዚአብሔር በታማኝነት ታዛዥ ሆኛለሁ፤
ሳኦልም ዳዊትን፦ “አንተ ገና ልጅ ነህ፤ እርሱም ከልጅነቱ ጀምሮ ጦረኛ ስለ ሆነ ይህን ፍልስጥኤማዊ ለመውጋት ትሄድ ዘንድ አትችልም” አለው።