Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 13:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ከእ​ርሱ ጋር የወጡ ሰዎች ግን ፥ “በኀ​ይል ከእኛ ይበ​ረ​ታ​ሉና በዚህ ሕዝብ ላይ መው​ጣት አን​ች​ልም” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ከእነርሱ ጋራ የወጡት ሰዎች ግን፣ “ከእኛ ይልቅ ብርቱዎች ስለ ሆኑ፣ ልናሸንፋቸው አንችልም” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ከእርሱ ጋር ወጥተው የነበሩት ሰዎች ግን፦ “ከእኛ ይልቅ እነርሱ ብርቱ ናቸውና በዚህ ሕዝብ ላይ መውጣት አንችልም” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ከካሌብ ጋር ሄደው የነበሩት ሰዎች ግን “እኛ በእነርሱ ላይ አደጋ ለመጣል ከቶ ኀይል የለንም፤ በዚያ የሚኖሩት ሰዎች ከእኛ ይበልጥ ብርቱዎች ናቸው” ብለው ተናገሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ከእርሱ ጋር የወጡ ሰዎች ግን፦ በኃይል ከእኛ ይበረታሉና በዚህ ሕዝብ ላይ መውጣት አንችልም አሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 13:31
8 Referencias Cruzadas  

ወዴት እን​ወ​ጣ​ለን? ሕዝቡ ታላ​ቅና ብዙ ነው፤ ከእ​ኛም ይጠ​ነ​ክ​ራሉ፤ ከተ​ሞ​ቹም ታላ​ላ​ቆች፥ የተ​መ​ሸ​ጉም፥ እስከ ሰማ​ይም የደ​ረሱ ናቸው፤ የረ​ዐ​ይ​ት​ንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየ​ና​ቸው ብለው ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ልባ​ች​ንን አስ​ፈ​ሩት።’


ከእኔ ጋር የወጡ ወን​ድ​ሞች ግን የሕ​ዝ​ቡን ልብ አስ​ካዱ፤ እኔ ግን አም​ላ​ኬን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽሜ እከ​ተ​ለው ዘንድ ተመ​ለ​ስሁ።


አላ​መ​ኑ​ምና፥ ለመ​ግ​ባት እን​ዳ​ል​ቻሉ እነሆ፥ እና​ያ​ለን።


ወደ ወይን ዘለላ ሸለቆ መጡ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም አዩ​አት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ ሰጣ​ቸው ምድር እን​ዳ​ይ​ገቡ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ልብ መለሱ።


“እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ስማ፤ ከአ​ንተ የበ​ለ​ጡ​ት​ንና የበ​ረ​ቱ​ትን አሕ​ዛብ፥ የቅ​ጽ​ራ​ቸው ግንብ እስከ ሰማይ የሚ​ደ​ርስ ታላ​ላ​ቆች ከተ​ሞ​ችን ለመ​ው​ረስ ትገቡ ዘንድ ዛሬ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ትሻ​ገ​ረ​ዋ​ለህ።


ካሌ​ብም ሕዝ​ቡን በሙሴ ፊት ዝም አሰ​ኘና፥ “አይ​ደ​ለም! ማሸ​ነ​ፍን እን​ች​ላ​ለ​ንና እን​ውጣ፤ እን​ው​ረ​ሳት” አለ።


ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን፥ “አንተ ገና ብላ​ቴና ነህና፥ እር​ሱም ከብ​ላ​ቴ​ን​ነቱ ጀምሮ ጦረኛ ነውና ይህን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ ለመ​ው​ጋት ትሄድ ዘንድ አት​ች​ልም” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ቸው ምድር እን​ዳ​ይ​ሻ​ገሩ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ልብ ለምን ታጣ​ም​ማ​ላ​ችሁ?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios