ስለዚህም ከሕዝባችን መካከል ሰይፍ፥ ጦርና ቀስት የያዙ ሰዎችን በየጐሣቸው በማዘጋጀት፥ ሥራው ባልተጠናቀቀበት ቦታ ሁሉ በቅጽሩ ግንብ በስተጀርባ እንዲመሸጉ አደረግሁ።
ነህምያ 6:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም “አስቸኳይ ሥራ ስላለብኝ ተግባሬን አቁሜ እናንተ ወዳላችሁበት ስፍራ መውረድ አልችልም፤ ወደ እናንተ ለመምጣት ተብሎ ለምን ሥራው ይቆማል?” አልኳቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም፣ “ታላቅ ሥራ እየሠራሁ ስለ ሆነ፣ ወዳላችሁበት ስፍራ መውረድ አልችልም፤ ትቼው ወደ እናንተ ወርጄ ሥራው ለምን ይቆማል?” በማለት ይህን መልስ የሚያደርሱ መልእክተኞችን ወደ እነርሱ ላክሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም እንዲህ ብዬ መልእክተኞችን ላክሁባቸው፦ “ትልቅ ሥራ እሠራለሁ፥ መውረድም አልችልም፤ ሥራውን ትቼ ወደ እናንተ በመውረዴ ሥራው ለምን ይቆማል?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም እንዲህ ስል መልእክተኞችን ላክሁባቸው፥ “እኔ ታላቅ ሥራ እሠራለሁ፤ እወርድም ዘንድ አይቻለኝም። ስለምን ወደ እናንተ በመምጣቴና በመውረዴ ሥራው ይታጐላል? ሥራውን እንደ ፈጸምሁ እመጣለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም፦ ትልቅ ሥራ እሠራለሁ፥ እወርድም ዘንድ አይቻለኝም፥ ሥራውን ትቼ ወደ እናንተ በመውረዴ ስለ ምን ሥራው ይታጐላል? ብዬ መልእክተኞችን ላክሁባቸው። |
ስለዚህም ከሕዝባችን መካከል ሰይፍ፥ ጦርና ቀስት የያዙ ሰዎችን በየጐሣቸው በማዘጋጀት፥ ሥራው ባልተጠናቀቀበት ቦታ ሁሉ በቅጽሩ ግንብ በስተጀርባ እንዲመሸጉ አደረግሁ።
ከዚህም የተነሣ ሰንባላጥና ጌሼም በተለይ ኦኖ ተብሎ በሚጠራው ሜዳ ከሚገኙት መንደሮች በአንዲቱ እንድንገናኛቸው መልእክት ላኩብኝ፤ ይህም እኔን ለመጒዳት በተንኰል የተዶለተ ዘዴ ነበር።