ነህምያ 5:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መሪዎቹም “እንዳዘዝከን እናደርጋለን፤ የተወሰደባቸውን ሀብትና ንብረት ሁሉ እንመልስላቸዋለን፤ የተበደሩትንም ዕዳ ክፈሉ ብለን አንጠይቃቸውም” ሲሉ መለሱልኝ። እኔም ካህናቱን ወደ ውስጥ ጠርቼ፥ መሪዎቹ የገቡትን ቃል ይፈጽሙ ዘንድ እንዲያስምሉአቸው አደረግሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም፣ “እንመልሳለን፤ ምንም ዐይነት ትርፍ አንጠይቃቸውም፤ እንዳልኸን እናደርጋለን” አሉ። ካህናቱን ጠራኋቸው፤ መኳንንቱንና ሹማምቱም የገቡትን ቃል እንዲፈጽሙ አማልኋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም፦ “እንመልስላቸዋለን፥ ከእነርሱም ምንም አንፈልግም፤ አንተ እንዳልኸው እናደርጋለን” አሉ። ካህናቱንም ጠርቼ ቃል እንደገቡት እንዲያደርጉ አስማልኳቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፥ “እንመልስላቸዋለን፤ ከእነርሱም ምንም አንሻም፤ እንደተናገርህ እንዲሁ እናደርጋለን” አሉ። ካህናቱንም ጠርቼ እንደዚህ ነገር ያደርጉ ዘንድ አማልኋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ እንመልስላቸዋለን፥ ከእነርሱም ምንም አንሻም፥ እንደ ተናገርህ እንዲሁ እናደርጋለን አሉ። ካህናቱንም ጠርቼ እንደዚህ ነገር ያደርጉ ዘንድ አማልኋቸው። |
ስለዚህም ዕዝራ የካህናት፥ የሌዋውያንና የቀሩት ሕዝብ መሪዎች ሸካንያ ባቀረበው ሐሳብ መስማማታቸውን በመሐላ እንዲያረጋግጡለት በማድረግ ሥራውን ጀመረ።
እነዚህ ሁሉ ወንድሞቻቸው ከሆኑት መሪዎቻቸው ጋር ተባብረው በእግዚአብሔር አገልጋይ በሙሴ አማካይነት ለተሰጡት ለጌታችን ለእግዚአብሔር ትእዛዞች፥ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች ሁሉ ታዛዦች እንደሚሆኑ በእርግማንና በመሐላ ቃል ገቡ።
በአካባቢአችን ላሉት አሕዛብ ሴቶች ልጆቻችንን በጋብቻ እንደማንሰጥና ወይም የእነርሱን ሴቶች ልጆች ለወንዶች ልጆቻችን በጋብቻ እንደማንወስድ ቃል እንገባለን።
የባዕዳን አገር ሕዝቦች በሰንበት ቀን ወይም በሌሎች በዓላት እህልም ሆነ ሌላ የንግድ ሸቀጥ ይዘው ቢመጡ፥ ከእነርሱ አንገዛም። በየሰባት ዓመት አንድ ጊዜ ምድሪቱን አናርስም፤ ያበደርነውንም ዕዳ ሁሉ እንሰርዛለን።
እነዚህንም ሰዎች ገሠጽኳቸው፤ ረገምኳቸውም፤ ደብድቤም ጠጒራቸውን ነጨሁ፤ ከዚህም በኋላ እነርሱም ሆኑ ልጆቻቸው ከባዕዳን ሕዝብ ጋር ጋብቻ እንዳይፈጽሙ በእግዚአብሔር ስም አስማልኳቸው።
ገንዘብም ሆነ እህል ወይም ወይንና የወይራ ዘይት ቢሆን ያበደራችሁትን ሁሉ ወለዱን ተዉላቸው፤ እርሻቸውን የወይንና የወይራ ዘይት ተክላቸውንና ቤታቸውን ሁሉ አሁኑኑ መልሱላቸው።”
ኢየሱስ ግን ዝም አለ። የካህናት አለቃውም እንደገና ኢየሱስን “በሕያው እግዚአብሔር ስም ይዤሃለሁ! አንተ የእግዚአብሔር ልጅ መሲሕ እንደ ሆንክ ንገረን!” አለው።
ዘኬዎስ ግን ቆሞ ጌታ ኢየሱስን እንዲህ አለው፦ “ጌታ ሆይ! እነሆ፥ ካለኝ ሀብት ሁሉ እኩሌታውን ለድኾች እሰጣለሁ፤ በማታለል ከሰው ላይ የወሰድኩትም ገንዘብ ቢኖር፥ አራት እጥፍ አድርጌ እመልሳለሁ።”