Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ነህምያ 10:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 እነዚህ ሁሉ ወንድሞቻቸው ከሆኑት መሪዎቻቸው ጋር ተባብረው በእግዚአብሔር አገልጋይ በሙሴ አማካይነት ለተሰጡት ለጌታችን ለእግዚአብሔር ትእዛዞች፥ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች ሁሉ ታዛዦች እንደሚሆኑ በእርግማንና በመሐላ ቃል ገቡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 እነርሱም ከወንድሞቻቸውና ከመኳንንታቸው ጋራ በመሆን በእግዚአብሔር ባሪያ በሙሴ አማካይነት የተሰጠውን የእግዚአብሔርን ሕግ የጌታችንን የእግዚአብሔርን ትእዛዞች፣ ደንቦችና ሥርዐቶች ሁሉ ለመታዘዝ በዚህ ርግማንና መሐላ ቃል ገቡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 የቀሩት ሕዝብ፥ ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ በር ጠባቂዎቹ፥ መዘምራን፥ የቤተ መቅደስ አገልጋዮች፥ ከምድር ሕዝቦች ወደ እግዚአብሔር ሕግ ራሳቸውን የለዩ ሁሉ፥ ሚስቶቻቸው፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው፥ የሚያውቁትና የሚያስተውሉት ሁሉ፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባሪያ በሙሴ እጅ በተ​ሰ​ጠው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ይሄዱ ዘንድ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ሁሉ፥ ፍር​ዱ​ንም፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ይጠ​ብ​ቁና ያደ​ርጉ ዘንድ ርግ​ማ​ን​ንና መሐ​ላን አደ​ረጉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ወደ ታላላቆቻቸው ተጠጉ፥ በእግዚአብሔርም ባሪያ በሙሴ እጅ በተሰጠው በእግዚአብሔር ሕግ ይሄዱ ዘንድ፥ የጌታችንንም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሁሉ ፍርዱንም ሥርዓቱንም ይጠብቁና ያደርጉ ዘንድ እርግማንና መሐላውን አደረጉ።

Ver Capítulo Copiar




ነህምያ 10:29
38 Referencias Cruzadas  

መንፈሴን አሳድርባችኋለሁ፤ የሰጠኋችሁንም ሕግና ሥርዓት ሁሉ በጥንቃቄ መፈጸም እንድትችሉ አደርጋችኋለሁ።


እውነተኛ ትእዛዞችህን ለመጠበቅ በመሐላ የገባሁትን ቃል አጸናለሁ።


እናንተም እኔ የማዛችሁን ብትፈጽሙ ወዳጆቼ ናችሁ።


ግብዝነት የሌለበት እውነተኛ ፍቅር ይኑራችሁ፤ ክፉውን ነገር ጥሉ፤ መልካሙን ነገር ተከተሉ።


ንጉሡ በዐምዱ አጠገብ ቆሞ በሙሉ ልቡና ሐሳቡ እግዚአብሔርን ለመከተልና ትእዛዞቹን፥ ደንቦቹንና ድንጋጌዎቹን ለመጠበቅ በእርሱ ፊት ቃል ኪዳኑን አደሰ፤ ስለዚህም በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ቃል ኪዳን አረጋገጠ።


ንጉሡ በዐምዱ አጠገብ ቆሞ በሙሉ ልቡና ሓሳቡ እግዚአብሔርን ለመከተልና ትእዛዞቹን፥ ደንቦቹንና ድንጋጌዎቹን ለመጠበቅ በእርሱ ፊት ቃል ኪዳኑን አደሰ፤ ስለዚህም በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ቃል ኪዳን አረጋገጠ፤ ሕዝቡም በቃል ኪዳኑ ተባበረ።


ነገር ግን እሺ አትበላቸው፤ እርሱን ሳንገድል እህል አንበላም፤ ውሃም አንጠጣም በማለት የተማማሉ ከአርባ የሚበልጡ ሰዎች እርሱን ለመግደል አድፍጠዋል፤ አሁን እነርሱ የሚጠብቁት የአንተን መልስ ብቻ ነው።”


አንዳንድ ሰዎች ግን ከእርሱ ጋር ተባበሩና አመኑ፤ ካመኑትም ሰዎች መካከል የአርዮስፋጎስ ጉባኤ አባል የሆኑት ዲዮናስዮስ የተባለ ሰውና ደማሪስ የተባለች አንዲት ሴት፥ ሌሎችም ይገኙባቸዋል።


እርሱም ሄዶ እግዚአብሔር ጸጋውን ለሕዝቡ እንዴት እንደ ሰጠ ባየ ጊዜ ደስ አለው፤ ሁሉም በሙሉ ልብ ጸንተው ለጌታ ታማኞች ሆነው እንዲኖሩም መከራቸው።


ሙሴ ሕግን ሰጥቶአችሁ የለምን? ነገር ግን ከእናንተ ሕግን የሚፈጽም ማንም የለም። እናንተ ለምን ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ?”


ሕግ በሙሴ በኩል ተሰጠ፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መጣ።


“የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ይመሩበት ዘንድ በሲና ተራራ ላይ ለአገልጋዬ ለሙሴ የሰጠሁትን ሕግና ትእዛዝ አስታውሱ።


እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ብለህ ተናገር አለኝ፦ “እኔ እግዚአብሔር የሰጠኋችሁን ሕግ ባትከተሉና ባትታዘዙኝ፥


እግዚአብሔር ለሕዝቡ ለእስራኤል እንደገና ምሕረትን ያደርጋል፤ የራሱ ወገኖችም አድርጎ ይመርጣቸዋል፤ እንደገናም በአገራቸው እንዲኖሩ ይፈቅድላቸዋል፤ መጻተኞችም እንኳ መጥተው ከእነርሱ ጋር ተስማምተው አብረው ይኖራሉ።


ይህንንም ሁሉ ማድረጉ ሕዝቡ ድንጋጌውን እንዲጠብቁና ሕጉንም እንዲፈጽሙ ነው። እግዚአብሔር ይመስገን!


ጌታችን እግዚአብሔር ሆይ! ስምህ በዓለም ሁሉ የገነነ ነው!


ጌታችንና እግዚአብሔር ሆይ! ስምህ በዓለም ሁሉ የገነነ ነው። ክብርህንም ከሰማያት ሁሉ በላይ አድርገሃል።


እነዚህንም ሰዎች ገሠጽኳቸው፤ ረገምኳቸውም፤ ደብድቤም ጠጒራቸውን ነጨሁ፤ ከዚህም በኋላ እነርሱም ሆኑ ልጆቻቸው ከባዕዳን ሕዝብ ጋር ጋብቻ እንዳይፈጽሙ በእግዚአብሔር ስም አስማልኳቸው።


የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ለአባቴ ለዳዊት ‘አንተ ሕጌን በጥንቃቄ እንደ ጠበቅህ ልጆችህም ቢጠብቁ፥ ከዘርህ መካከል በእስራኤል ላይ በፊቴ የሚነግሥ ዘወትር ይኖራል’ በማለት የገባህለትን ቃል ኪዳን አሁን እንድታጸናልኝ እለምንሃለሁ፤


ኢዩ ግን ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ሕግ በፍጹም ልቡ ታዛዥ ሆኖ አልተገኘም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራቸውን የኢዮርብዓምን ክፉ አርአያነት ተከተለ።


የእስራኤል ሕዝብ ርስት የሆነውን፥ ሙሴ የሰጠንን ሕግ ይጠብቃሉ።


“ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁ ያዘዛችሁን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁዎች ሁኑ፤ ከሕግጋቱም አንዱን እንኳ አትጣሱ፤


ሙሴም የእስራኤልን ሕዝብ ሁሉ በአንድነት ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፥ ዛሬ የምነግራችሁን ሕግና ሥርዓት ሁሉ አድምጡ፤ በጥንቃቄም አጥንታችሁ እነዚህን ትእዛዞች ጠብቁ።


ካህኑ ሴቲቱን እንዲህ ብሎ የመርገም መሐላ ያስሞላት፦ ‘እግዚአብሔር ጭንሽን እያሰለሰለና ሆድሽን እየነፋ በሕዝብሽ መካከል ለመሓላና ለእርግማን የተገባሽ ያድርግሽ፤


ስለ ሆነው ነገር ሁሉ እኛ የጽሑፍ ስምምነት ለማድረግ ወሰንን፤ በስምምነቱም ጽሑፍ ላይ መሪዎቻችን፥ ሌዋውያኖቻችንና ካህናቶቻችን ማኅተማቸውን አኖሩበት።


እነሆ እናንተም ከጥቂት ቀኖች በፊት ተጸጸታችሁ እኔን ደስ የሚያሰኝ ነገር መሥራት ጀምራችሁ ነበር፤ ሁላችሁም ከእስራኤላውያን ወገን የሆኑ ባሪያዎቻችሁን ነጻ ለመልቀቅ ተስማማችሁ፤ እኔ በምመለክበትም ቤተ መቅደስ ተሰብስባችሁ በፊቴ ቃል ኪዳን ገባችሁ፤


እኔ እግዚአብሔር ቅዱስ ስለ ሆንኩና የእኔ ትሆኑ ዘንድ እናንተን ከአሕዛብ ስለ ለየኋችሁ፥ እናንተ ለእኔ የተቀደሳችሁ ሁኑ።


በየከተማው ወዳለው ይዞታቸው የተመለሱት የመጀመሪያዎቹ ካህናት፥ ሌዋውያን፥ የቤተ መቅደስ አገልጋዮችና ሌሎችም እስራኤላውያን ነበሩ።


ከምርኮ የተመለሱ የቤተ መቅደስ ሠራተኞች፥ ዘሮች በየጐሣቸው፦ ጺሐ፥ ሐሱፋ፥ ጣባዖት፥ ቄሮስ፥ ሲዓ፥ ፋዶን፥ ለባና፥ ሐጋባ፥ ሻልማይ፥ ሐናን፥ ጊዴል፥ ጋሐር፥ ረአያ፥ ረጺን፥ ነቆዳ፥ ጋዛም፥ ዑዛ፥ ፓሴሐ፥ ቤሳይ፥ መዑኒም፥ ነፉሸሲም፥ ባቅቡቅ፥ ሐቁፋ፥ ሐርሑር፥ ባጽሊት፥ መሒዳ፥ ሐርሻ፥ ባርቆስ፥ ሲስራ፥ ቴማሕ፥ ነጺሐና ሐጢፋ።


ስለዚህም ካህኑ ዕዝራ ሰባተኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን፥ ማስተዋል የሚችል ሕዝብ ሁሉ ሴት፥ ወንድ፥ ልጅ ዐዋቂው በሙሉ ወደተሰበሰቡበት ስፍራ፥ የሕጉን መጽሐፍ አመጣ፤


በዚያም አደባባይ ዕዝራ በቅጽሩ በር አጠገብ ቆሞ ከንጋት እስከ ቀትር የሕጉን መጽሐፍ ከፍ ባለ ድምፅ አነበበላቸው፤ ወንዶችም ሴቶችም ሁሉ በከፍተኛ ስሜት አዳመጡት።


ራሳቸውንም ከባዕዳን ሕዝቦች ሁሉ ለዩ፤ ከዚህም በኋላ ሁሉም ተነሥተው በመቆም፥ እነርሱና የቀድሞ አባቶቻቸው የሠሩትን ኃጢአት ሁሉ ተናዘዙ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios