Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዕዝራ 10:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ስለዚህም ዕዝራ የካህናት፥ የሌዋውያንና የቀሩት ሕዝብ መሪዎች ሸካንያ ባቀረበው ሐሳብ መስማማታቸውን በመሐላ እንዲያረጋግጡለት በማድረግ ሥራውን ጀመረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ዕዝራም ተነሥቶ አለቆቹ ካህናት፣ ሌዋውያንና እስራኤል ሁሉ የቀረበውን ሐሳብ እንዲፈጽሙ አስማላቸው፤ እነርሱም ማሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ዕዝራም ተነሣ፤ አለቆቹን፥ ካህናቱን፥ ሌዋውያኑንና እስራኤልንም ሁሉ እንደዚህ ቃል እንዲያደርጉ አስማላቸው፥ እነርሱም ማሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ዕዝ​ራም ተነሣ፤ አለ​ቆ​ቹ​ንና ካህ​ና​ቱ​ንም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑ​ንም፥ እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ እን​ደ​ዚህ ቃል ያደ​ርጉ ዘንድ አማ​ላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ማሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ዕዝራም ተነሣ፤ አለቆቹንና ካህናቱን፥ ሌዋውያኑንና እስራኤልን ሁሉ እንደዚህ ቃል ያደርጉ ዘንድ አማለ፤ እነርሱም ማሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 10:5
10 Referencias Cruzadas  

እነዚህንም ሰዎች ገሠጽኳቸው፤ ረገምኳቸውም፤ ደብድቤም ጠጒራቸውን ነጨሁ፤ ከዚህም በኋላ እነርሱም ሆኑ ልጆቻቸው ከባዕዳን ሕዝብ ጋር ጋብቻ እንዳይፈጽሙ በእግዚአብሔር ስም አስማልኳቸው።


መሪዎቹም “እንዳዘዝከን እናደርጋለን፤ የተወሰደባቸውን ሀብትና ንብረት ሁሉ እንመልስላቸዋለን፤ የተበደሩትንም ዕዳ ክፈሉ ብለን አንጠይቃቸውም” ሲሉ መለሱልኝ። እኔም ካህናቱን ወደ ውስጥ ጠርቼ፥ መሪዎቹ የገቡትን ቃል ይፈጽሙ ዘንድ እንዲያስምሉአቸው አደረግሁ።


ኢየሱስ ግን ዝም አለ። የካህናት አለቃውም እንደገና ኢየሱስን “በሕያው እግዚአብሔር ስም ይዤሃለሁ! አንተ የእግዚአብሔር ልጅ መሲሕ እንደ ሆንክ ንገረን!” አለው።


ሽቶና መልካም መዓዛ ያለው ቅባት ሰውን ደስ እንደሚያሰኝ የወዳጅ ምክርም እንዲሁ ደስ ያሰኛል።


ተገቢውን ቃል በተገቢው ቦታ መናገር እጅግ ያስደስታል።


ጠቢብን አስተምረው፥ በይበልጥ ጥበበኛ ይሆናል፤ ደግን ሰው አስተምረው፤ ዕውቀትን ይጨምራል።


እነዚህ ምሳሌዎች ጠቢባን ዕውቀታቸውን እንዲያዳብሩ፥ አስተዋዮችም ተጨማሪ መመሪያ የሚሆናቸውን ምክር እንዲያገኙ ያደርጋሉ።


እነዚህ ሁሉ ወንድሞቻቸው ከሆኑት መሪዎቻቸው ጋር ተባብረው በእግዚአብሔር አገልጋይ በሙሴ አማካይነት ለተሰጡት ለጌታችን ለእግዚአብሔር ትእዛዞች፥ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች ሁሉ ታዛዦች እንደሚሆኑ በእርግማንና በመሐላ ቃል ገቡ።


አሁን እንግዲህ እነዚህን ባዕዳን ሴቶች ከነልጆቻቸው ማሰናበት እንደሚገባን ለአምላካችን ቃል እንግባ፤ አንተ ጌታዬና የአምላካችንን ትእዛዝ የሚያከብሩ ሌሎችም የምትሰጡንን ምክር ሁሉ እንፈጽማለን፤ የእግዚአብሔር ሕግ የሚያዘውን ሁሉ እናደርጋለን፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios