የሃስናአ ጐሣ አባሎች የዓሣ ቅጽር በር የተባለውን ሠሩ፤ ምሰሶዎችንም አቆሙለት፤ በሮችንም ገጠሙ፤ ለበሮቹም መዝጊያ፥ መወርወሪያና ቊልፎችን አበጁ።
የዓሣ በሩን የሃስናአ ልጆች ሠሩ፤ እነርሱም ምሰሶዎቹን አቁመው መዝጊያዎቹን፣ መቀርቀሪያዎቹንና መወርወሪያዎቹን በየቦታቸው አኖሩ።
የስናአ ልጆች “የዓሣ በር” ሠሩ፤ ሰረገሎቹን አኖሩ፥ በሮቹን አቆሙ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም ሠሩ።
የአስናሃ ልጆችም የዓሣ በር ሠሩ፤ ሠረገሎቹንም አኖሩ፤ ሳንቃዎቹንም አቆሙ፥ ቍልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረጉ።
የሃስናአ ልጆችም የዓሣ በር ሠሩ፥ ሰረገሎቹን አኖሩ፥ ሳንቃዎቹንም አቆሙ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረጉ።
ከዚህ በኋላ ምናሴ በዳዊት ከተማ በስተ ምሥራቅ በኩል የሚገኘውን የውጪ ቅጽር ቁመት ከፍ አድርጎ ሠራ፤ ይህም ቅጽር በሸለቆው ውስጥ ከግዮን ምንጭ በስተ ምዕራብ በኩል አንሥቶ፥ በስተ ሰሜን እስከ ዓሣ ቅጽር በር የሚደርስ ሲሆን፥ በከተማይቱ አጠገብ የሚገኘውን ዖፌል ተብሎ የሚጠራውን ስፍራ የሚያጠቃልል ነው፤ እንዲሁም ምናሴ በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ሁሉ፥ ለእያንዳንዳቸው አንዳንድ የክፍለ ጦር አዛዥ መደበላቸው።
ከዚያም አልፈን የኤፍሬም ቅጽር በር፥ የይሻና ቅጽር በር፥ የዓሣ ቅጽር በር ተብለው ወደተሰየሙትና የሐናንኤል ግንብ የመቶዎቹ ግንብና የበጎች ቅጽር በር ተብለው ወደሚጠሩት ስፍራዎች መጣን፤ ሰልፋችንንም ያበቃነው ለቤተ መቅደሱ ቅርብ ወደ ሆነው የዘበኞች ቅጽር በር ወደሚባለው ቦታ ስንደርስ ነበር።
እንዲሁም አሳፍ የተባለው፥ የመንግሥት ደን ጠባቂ የሆነው፥ ለቤተ መቅደሱ ቅጽር በርና ለከተማይቱ ቅጽር በሮች ሁሉ እኔም ለማርፍበት ቤት ጭምር መጠበቂያዎች ማሠሪያ የሚሆን የጥድና የዝግባ እንጨት ለመቊረጥ እንዲፈቅድልኝ የሚያዝ ደብዳቤ እንዲሰጠኝም ጠየቅሁ፤ እግዚአብሔርም በቸርነቱ ስለ ረዳኝ፥ ንጉሠ ነገሥቱ የጠየቅሁትን ነገር ሁሉ ሰጠኝ።
የሀቆጽ የልጅ ልጅ የሆነው የኡሪያ ልጅ መሬሞት ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠራ። (አደሰ ቢሆን ይመረጣል) የመሼዛቤል የልጅ ልጅ የሆነው የበራክያ ልጅ መሹላም ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠራ፤ ከዚያም ቀጥሎ የሚገኘውን ክፍል የበዓና ልጅ ሳዶቅ ሠራው። (አደሰ ቢሆን ይመረጣል)
የፓሴሕ ልጅ ዮዳሄ፥ የበሶድያ ልጅ መሹላም የይሻናን ቅጽር በር ሠሩ፤ ምሰሶዎችንም አቆሙለት፤ በሮችንም ገጠሙ፤ ለበሮቹም ቊልፎችንና መወርወሪያዎችን አበጁ።
ሰንባላጥ፥ ጦቢያ፥ ዐረባዊው ጌሼምና ሌሎችም ጠላቶቻችን የቅጽሩን ግንብ ሠርቼ መፈጸሜንና ያልተሠራ ክፍት ቦታ አለመኖሩን ሰሙ፤ ይሁን እንጂ በቅጽር በሮቹ ላይ መዝጊያዎችን አላቆምኩም ነበር።
እነሆ የቅጽሩ ግንብ ተሠርቶ አለቀ፤ የቅጽር በሮችም ሁሉ በየቦታቸው ተገጣጥመው ነበር፤ ቤተ መቅደሱን የሚጠብቁ ዘበኞች ለመዘምራን ቡድን አባላትና ለሌሎችም ሌዋውያን የሥራ ድርሻቸው ተመድቦላቸው ነበር።
እርሱ የበሮችሽን መወርወሪያ አጠንክሮ ይጠብቃል፤ በውስጥሽ ያሉትንም ሕዝቦችሽን ይባርካል።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በዚያን ቀን ከኢየሩሳሌም ቅጽር በዓሣ በር በኩል ኡኡታ ይሰማል፤ ከአዲሱም አደባባይ የዋይታ ድምፅ ያስተጋባል፤ በኰረብቶችም አካባቢ ከፍተኛ ሽብር ይሰማል።