ነህምያ 13:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላካችን በእኛና በከተማይቱ ላይ ይህን ጥፋት ያመጣው የቀድሞ አባቶቻችሁ ይህን ጥፋት ስላደረጉ አይደለምን? አሁንም እናንተ ሰንበትን ባለማክበራችሁ የእግዚአብሔርን ቊጣ በእስራኤል ላይ ታነሣሣላችሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቀድሞ አባቶቻችሁ ያደረጉት ይህንኑ አልነበረምን? አምላካችንስ ይህን ሁሉ ጥፋት በእኛና በዚች ከተማ ላይ ያመጣው በዚሁ በደላችን አይደለምን? አሁንም እናንተ ሰንበትን በማርከስ የባሰ መከራ በእስራኤል ላይ ታመጣላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባቶቻችሁ እንደዚህ አድርገው አልነበረምን? አምላካችንስ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ በእኛና በዚህ ከተማ ላይ አምጥቶ አልነበረምን? እናንተም ሰንበትን በማርከሳችሁ በእስራኤል ላይ መዓትን ትጨምራላችሁ አልኋቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቶቻችሁ እንደዚህ አድርገው አልነበረምን? አምላካችንስ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ በእኛና በዚች ከተማ ላይ አምጥቶ አልነበረምን? እናንተስ ሰንበትን በማርከሳችሁ በእስራኤል ላይ መዓትን ትጨምራላችሁ?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባቶቻችሁ እንደዚህ አድርገው አልነበረምን? አምላካችንስ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ በእኛና በዚህ ከተማ ላይ አምጥቶ አልነበረምን? እናንተም ሰንበትን በማርከሳችሁ በእስራኤል ላይ መዓትን ትጨምራላችሁ አልኋቸው። |
ነገር ግን ለእኔ መታዘዝና ሰንበትንም የተቀደሰ ቀን አድርገው ማክበር ይገባቸዋል፤ በዚህ ዕለት በኢየሩሳሌም የቅጽር በሮች ምንም ዐይነት ሸክም ይዘው መግባት የለባቸውም፤ ትእዛዜን ባለመቀበል ይህን ቢያደርጉ ግን የኢየሩሳሌም ቅጽር በሮች በእሳት እንዲጋዩ አደርጋለሁ፤ የኢየሩሳሌም ቤተ መንግሥቶችም በእሳት ይነዳሉ፤ እሳቱንም ሊያጠፋ የሚችል የለም።’ ”
እነሆ በአሁኑ ጊዜ ምድራችሁ ፍርስራሽ ሆናለች፤ የሚኖርባትም የለም፤ ምድሪቱ አጸያፊ ሆናለች፤ ሕዝብም ሁሉ እንደ ተረገመች ይቈጥሩአታል፤ እግዚአብሔር የዐመፅና የክፋት ሥራችሁን ሁሉ አይታገሥም።
ይህም ሁሉ መቅሠፍት የደረሰባችሁ ለባዕዳን አማልክት መሥዋዕት በማቅረባችሁ፥ እግዚአብሔርን በማሳዘናችሁ፥ ለሕጉ፥ ለድንጋጌውና ለሥርዓቱም ባለመታዘዛችሁ ነው።”
በቀድሞ አባቶቻችሁ፥ በይሁዳ ነገሥታትና በሚስቶቻቸው፥ በእናንተ በራሳችሁና በሚስቶቻችሁ አማካይነት በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ላይ የተፈጸመውን ክፉ ሥራ ሁሉ ረስታችሁታልን?
ክብርናዋን ባጣችበት በግብጽ የጀመረችውን አመንዝራነት ቀጥላለች፤ ከልጃገረድነትዋ ጊዜ ጀምሮ ወንዶች ሁሉ እርስዋን እንደ አመንዝራ በመቊጠር ከእርስዋ ጋር ያመነዝራሉ።
እናንተ እንዲህ ትላላችሁ፦ “እህላችንን መሸጥ እንድንችል የወር መባቻው በዓል ምነው ቶሎ ባለፈልን! ስንዴ ወደ ገበያ ለመውሰድ ሰንበትም መቼ ያልፍልናል? በዓላቱ ካለፉልን የእህሉን መስፈሪያ አሳንሰን ከፍተኛ ዋጋ እንጠይቃለን፤ በሐሰተኛ ሚዛንም ሕዝቡን እናታልላለን፤
አሁን ደግሞ እናንተ በአባቶቻችሁ ስፍራ ተተክታችኋል፤ የእግዚአብሔርንም ቊጣ በእስራኤል ላይ ለማምጣት የተዘጋጀ አዲስ ኃጢአተኛ ትውልድ ሆናችኋል።