“አደጋ ለመጣል የሚያስችል ምልክት ስጡ! ሕዝቦች ሁሉ መስማት እንዲችሉ እምቢልታ ንፉ! ባቢሎንን ይወጉ ዘንድ ሕዝቦችን አዘጋጁ! የአራራት፥ የሚኒና የአሽኬናዝ መንግሥታት አደጋ እንዲጥሉ ንገሩአቸው፤ የጦር አዛዥ የሚሆን ሰው ሹሙ፤ ብዛታቸው እንደ አንበጣ መንጋ የሆነ ፈረሶችን አምጡ።
ናሆም 3:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠባቂዎችሽ እንደ ኲብኲባ፥ ባለ ሥልጣኖችሽ በብርድ ቀን በአጥር ላይ እንደ ሰፈረ የአንበጣ መንጋ ናቸው፤ ፀሐይ ሲወጣ በረው ይሄዳሉ፤ ወዴት እንደሚሄዱ ግን የሚያውቅ የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠባቂዎችሽ እንደ አንበጣ፣ መኳንንትሽም በብርድ ቀን በቅጥር ሥር እንደሚቀመጥ ኵብኵባ ናቸው፤ ፀሓይ ሲወጣ ግን ይበርራሉ፤ ወዴት እንደሚበርሩም አይታወቅም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠባቂዎችሽ እንደ አንበጣ፥ መኳንንቶችሽም በብርድ ቀን በቅጥር ላይ እንደ ሰፈረ የኩብኩባ መንጋ ናቸው፤ ፀሐይም በወጣች ጊዜ ይበራሉ፥ ስፍራቸው የት እንደሆነ አይታወቅም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአንቺ ዘንድ ዘውድ የጫኑት እንደ አንበጣ፥ አለቆችሽም እንደሚንቀሳቀሱ ኩብኩባዎች ናቸው፣ በብርድ ቀን በቅጥር ውስጥ ይቀመጣሉ፥ ፀሐይም በወጣች ጊዜ ያኰበኵባሉ፣ ስፍራቸው በየት እንደ ሆነ አይታወቅም። |
“አደጋ ለመጣል የሚያስችል ምልክት ስጡ! ሕዝቦች ሁሉ መስማት እንዲችሉ እምቢልታ ንፉ! ባቢሎንን ይወጉ ዘንድ ሕዝቦችን አዘጋጁ! የአራራት፥ የሚኒና የአሽኬናዝ መንግሥታት አደጋ እንዲጥሉ ንገሩአቸው፤ የጦር አዛዥ የሚሆን ሰው ሹሙ፤ ብዛታቸው እንደ አንበጣ መንጋ የሆነ ፈረሶችን አምጡ።
ከምድር ሕዝቦች በጣም ጨካኞች የሆኑት ዛፉን ቈርጠው ይጥላሉ። ቀንበጦቹም በተራሮችና በሸለቆዎች ላይ ይወድቃሉ፤ ቅርንጫፎቹ ተሰባብረው በወራጅ ውሃ ላይ ይጋደማሉ። በጥላው ሥር ተጠልለው የነበሩት የምድር ሕዝቦች ሁሉ ትተውት ይሄዳሉ።
አንበጣዎቹ ለጦርነት የተዘጋጁ ፈረሶችን ይመስሉ ነበር፤ በራሳቸው ላይ የወርቅ አክሊል የመሰለ ነገር ነበር፤ ፊታቸውም የሰው ፊት ይመስል ነበር፤