Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ናሆም 3:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 የአሦር ንጉሥ ሆይ፥ ጠባቂዎችህ ተኝተዋል፤ ልዑላንህ አንቀላፍተዋል፤ ሕዝብህ በተራራ ላይ ተበትነዋል፤ የሚሰበስባቸውም የለም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 የአሦር ንጉሥ ሆይ፤ እረኞችህ አንቀላፉ፤ መኳንንትህ ዐርፈው ተኙ፤ ሕዝብህ ሰብሳቢ ዐጥተው፣ በተራራ ላይ ተበትነዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 የአሦር ንጉሥ ሆይ፥ እረኞችህ አንቀላፍተዋል፤ መኳንንቶችህም ዐርፈዋል፤ ሕዝብህ በተራሮች ላይ ተበትነዋል፥ የሚሰበስባቸውም የለም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የአሦር ንጉሥ ሆይ፥ እረኞችህ አንቀላፍተዋል፣ መኳንንቶችህም ዐርፈዋል፣ ሕዝብህም በተራሮች ላይ ተበትኖአል፥ የሚሰበስበውም የለም።

Ver Capítulo Copiar




ናሆም 3:18
13 Referencias Cruzadas  

ሚክያስም “መላው የእስራኤል ሠራዊት ጠባቂ እንደሌላቸው በጎች በኮረብታዎች ላይ ተበታትነው አያለሁ፤ እግዚአብሔርም ‘እነዚህ ሰዎች መሪ የላቸውም፤ ስለዚህ ወደየቤታቸው በሰላም ይመለሱ ብሎአል’ ሲል መለሰለት።”


አምላክ ሆይ፥ ሕዝብህ እስኪያልፍ ድረስ፥ የተቤዠኸው ሕዝብ እስኪያልፍ ድረስ፥ ፍርሀትና ድንጋጤ ወደቀባቸው፤ በሥልጣንህ እንደ ድንጋይ ጸጥ አሉ።


“አዳኝ እንዳባረረው አጋዘንና ጠባቂ እንደሌለው የበግ መንጋ ይባዝን የነበረው እያንዳንዱ ሰው ወደ ወገኖቹ ይመለሳል፤ ወደ አገሩም ይሸሻል።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “አንቺ በማንም ያልተደፈርሽ የባቢሎን ከተማ ሆይ! ወርደሽ በዐቧራ ላይ ተቀመጪ፤ ወርደሽ በዙፋን ላይ ሳይሆን፤ በመሬት ላይ ተቀመጪ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ቅምጥልና ለስላሳ መባልሽ ይቀራል።


ስለዚህ እኔ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ የአሦርን ንጉሠ ነገሥት እንደቀጣሁ፥ ናቡከደነፆርንና አገሩን ጭምር እቀጣለሁ።


ሞቅ ባላቸው ጊዜ የመጠጥ ግብዣ አደርግላቸዋለሁ፤ እስኪሰክሩ ድረስም አጠጣቸዋለሁ፤ ከዚያም ዘለዓለማዊ እንቅልፍ ያንቀላፋሉ፤ እስከ መቼም አይነቁም።


መሳፍንትዋ፥ የጥበብ ሰዎችዋ፥ መሪዎችዋ፥ የጦር አዛዦችዋና ወታደሮችዋ ጠጥተው እንዲሰክሩ አደርጋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ይተኛሉ፤ እስከ ዘለዓለም አይነቁም፤ ይህን የተናገርኩ እኔ ንጉሡ ነኝ፤ ስሜም የሠራዊት አምላክ ነው።


የምድር ነገሥታት፥ ገዢዎች፥ የጦር አለቆች፥ ሀብታሞች፥ ኀይለኞች፥ አገልጋዮችና ጌቶችም ሁሉ በዋሻዎችና በተራራዎች አለቶች ውስጥ ተሸሸጉ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos