ሚክያስ 3:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ራእይ የማያዩበት ሌሊት ይመጣባቸዋል፤ የማይገለጥላቸውም ጨለማ ሆኖባቸዋል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ራእይ አያዩም፥ ትንቢትም አይናገሩም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሌሊቱ ያለ ራእይ፣ ጨለማውም ያለ ሟርት ይመጣባችኋል፤ በነቢያት ላይ ፀሓይ ትጠልቅባቸዋለች፤ ቀኑም ይጨልምባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ለእናንተ ራእይ የሌለው ሌሊት ይሆንባችኋል፥ የማትጠነቁሉበት ጨለማ ይሆንባችኋል፤ ፀሐይ በነቢያት ላይ ትጠልቅባቸዋለች፥ ቀኑም ይጨልምባቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ሌሊት ይሆንባችኋል እንጂ ራእይ አይሆንላችሁም፥ ጨለማም ይሆንባችኋል እንጂ አታምዋርቱም፥ ፀሐይም በነቢያት ላይ ትገባለች፥ ቀኑም ይጠቁርባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ሌሊት ይሆንባችኋል እንጂ ራእይ አይሆንላችሁም፥ ጨለማም ይሆንባችኋል እንጂ አታምዋርቱም፥ ፀሐይም በነቢያት ላይ ትገባለች፥ ቀኑም ይጠቁርባቸዋል። |
በዳበሳ እንሄዳለን፤ መንገዳችንንም የምንከታተለው በዳበሳ ነው፤ በድንግዝግዝታ እንዳለን ዐይነት በቀትር እንደናቀፋለን፤ በኀያላን ሰዎችም መካከል እንደ ሞቱ ሰዎች ነን።
ጨለማን አምጥቶ በተራራዎች ከመሰናከላችሁ በፊት ተስፋ ያደረጋችኹትን ብርሃን ወደ ድቅድቅ ጨለማና ወደ ጥልቅ ጭጋግ ከመለወጡ በፊት አምላካችሁን እግዚአብሔርን አክብሩ።
ሰባት ልጆችዋን ያጣችው እናት፥ በታላቅ ተስፋ መቊረጥ ከእስትንፋስዋ ጋር እየታገለች ነው፤ የቀኑ ብርሃን ወደ ጨለማ ተለውጦባታል፤ ውርደትና ኀፍረት ደርሰውባታል፤ ገና በሕይወት ያላችሁትንም ጠላቶቻችሁ እንዲገድሉአችሁ አደርጋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
ከሕዝቡ መካከል አንዳንድ ሰዎች፦ “ኑ በኤርምያስ ላይ ዕቅድ እናውጣ! የእግዚአብሔርን ሕግ የሚያስተምሩ ካህናት፥ ምክር የሚሰጡ ጥበበኞች፥ የእግዚአብሔርን መልእክት የሚናገሩ ነቢያት ሁልጊዜ እናገኛለን፤ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲያ ኤርምያስን ከማድመጥ ይልቅ በንግግሩ አጥምደን በወንጀል እንክሰሰው ተባባሉ።”
ሐሰተኛ ራእይ በሚያዩና ሟርትን በሚያሟርቱ ነቢያት ላይ እጄን አነሣለሁ፤ እነርሱ በሕዝቤ ማኅበር ውስጥ አይገኙም፤ እንዲያውም በእስራኤል ሕዝብ መዝገብ ውስጥ አይመዘገቡም፤ ወደ እስራኤል ምድርም አይገቡም፤ በዚያን ጊዜ እኔ ልዑል እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።
አንዱ መቅሠፍት ሌላውን ያስከትላል፤ አንዱ ወሬም ሌላውን ወሬ ተከታትሎ ይመጣል፤ ነቢያት ያዩትን ራእይ እንዲነግሩአችሁ ትለምኑአቸዋላችሁ፤ ካህናት ሕዝቡን የሚያስተምሩት ሕግ፥ ሽማግሌዎችም ለሕዝቡ የሚሰጡት ምክር ጠፋባቸው።
“እነሆ በምድር ላይ ራብን የማመጣበት ጊዜ ይመጣል፤ በዚያን ጊዜም ሰዎች የሚራቡትና የሚጠሙት የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ነው እንጂ ምግብና ውሃ በማጣት አይደለም፤ እኔ ጌታ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።