ሚክያስ 2:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእነርሱ ነቢያት “ትንቢት አትናገር፤ እንደዚህ ያለው ውርደት የማይደርስብን ስለ ሆነ ስለ ነዚህ ጉዳዮች ትንቢት አትናገር” ይሉኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነቢያቶቻቸው፣ “ትንቢት አትናገርብን፤ ስለ እነዚህ ነገሮች ትንቢት አትናገር፤ ውርደት አይደርስብንም” ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አትስበኩ” ብለው ይሰብካሉ፤ “ስለ እነዚህ ነገሮች መስበክ የለባችሁም፤ ውርደት አይደርስብንም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትንቢት አትናገሩ ብለው ይናገራሉ፥ በእነዚህ ላይ ትንቢት አይናገሩም፥ ስድብም አይርቅም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትንቢት አትናገሩ ብለው ይናገራሉ፥ በእነዚህ ላይ ትንቢት አይናገሩም፥ ስድብም አይርቅም። |
ነቢያትንም አፋቸውን ለማስያዝ እንዲህ ይሉአቸዋል፦ ‘ቀጥተኛ የሆነውን ነገር አትንገሩን፤ እኛ ልንሰማ የምንፈልገውን ብቻ ንገሩን፤ ለስላሳና ማረሳሻ የሆነውን ነገር አስተምሩን።
አሁንም እግዚአብሔር የሚለውን ቃል ስማ፤ አንተ ‘በእስራኤል ላይ ትንቢት አትናገር፤ የይስሐቅ ዘሮች የሆኑትንም የእስራኤልን ሕዝብ አትስበክ’ ብለህ ከልክለኸኛል።
ይህ ሁሉ የሚደርስባችሁ የንጉሥ ዖምሪን ሥርዓት ስለ ጠበቃችሁና የንጉሥ አክዓብን አካሄድ ሁሉ ስለ ተከተላችሁ ነው፤ በእነርሱ ባህል ስለ ተመራችሁ አጠፋችኋለሁ፤ የከተማይቱን ነዋሪዎችም የሰው ሁሉ መሳቂያ አደርጋቸዋለሁ፤ በሕዝቤ ላይ የተሰነዘረውን ነቀፋ እንድትሸከሙ አደርጋችኋለሁ።”
“የኢየሱስን ስም በመጥራት እንዳታስተምሩ በጥብቅ አዘናችሁ ነበር፤ ነገር ግን እነሆ፥ ኢየሩሳሌምን በትምህርታችሁ ሞላችኋት፤ እናንተ ለዚያ ሰው ሞት እኛን ተጠያቂዎች ልታደርጉን ትፈልጋላችሁ።”