እስራኤላውያንን ከሰጠኋቸው ምድር ተነቃቅለው እንዲባረሩ አደርጋለሁ፤ ስሜ እንዲጠራበት የቀደስኩትንም ይህን ቤተ መቅደስ እተወዋለሁ፤ በየአገሩ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ እስራኤልን መሳለቂያና መዘባበቻ ያደርጓታል።
ሚክያስ 2:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በርኲሰት ምክንያት አሠቃቂ ጥፋት የሚደርስ በመሆኑ በዚህ ማረፍ አይቻልም፤ ስለዚህ ተነሥታችሁ ሂዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተነሡና ከዚያ ሂዱ፤ ይህ ማረፊያ ቦታችሁ አይደለምና፤ ምክንያቱም ረክሷል፤ ክፉኛም ተበላሽቷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተነሡና ሂዱ፥ ይህ የዕረፍት ቦታ አይደለምና፤ በርኩሰት ምክንያት ክፉ ጥፋት ትጠፋለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚህ ዕረፍት የላችሁምና ተነሥታችሁ ሂዱ፥ በርኵሰት ምክንያት ክፉ ጥፋት ታጠፋችኋለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚህ ዕረፍት የላችሁምና ተነሥታችሁ ሂዱ፥ በርኵሰት ምክንያት ክፉ ጥፋት ታጠፋችኋለች። |
እስራኤላውያንን ከሰጠኋቸው ምድር ተነቃቅለው እንዲባረሩ አደርጋለሁ፤ ስሜ እንዲጠራበት የቀደስኩትንም ይህን ቤተ መቅደስ እተወዋለሁ፤ በየአገሩ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ እስራኤልን መሳለቂያና መዘባበቻ ያደርጓታል።
የአሦር ንጉሠ ነገሥት ቲግላት ፐሌሴር ዒዮን፥ አቤልቤትማዕካ፥ ያኖሐ፥ ቄዴሽና ሐጾር ተብለው የሚጠሩትን ከተሞች፥ እንዲሁም የገለዓድን፥ የገሊላንና የንፍታሌምን ግዛቶች በመውረር ሕዝቡን ወደ አሦር ማርኮ የወሰደውም ይኸው ፋቁሔ በነገሠበት ዘመን ነበር።
ይኸውም ሆሴዕ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት ሰልምናሶር ድል አድርጎ ሰማርያን ያዘ፤ እስራኤላውያንንም ማርኮ በእስረኛነት ወደ አሦር ወሰዳቸው፤ ከእነርሱም ጥቂቶቹ በሐላሕ ከተማ፥ ጥቂቶቹ በጎዛን አውራጃ ውስጥ በሚገኘው በሐቦር ወንዝ አጠገብ፥ እንዲሁም ሌሎቹ በሜዶን ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ።
እኔ ከሰጠኋችሁ ከምድሬ ተነቅላችሁ እንድትባረሩ አደርጋለሁ፤ እኔ ለስሜ የቀደስኩትን ይህን ቤተ መቅደስ እተወዋለሁ፤ በሁሉ ስፍራ የሚኖሩ ሕዝቦችም በንቀት መሳለቂያና መዘባበቻ ያደርጉታል።
እነርሱ ለከነዓን ጣዖቶች መሥዋዕት አድርገው ያቀረቡአቸውን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በመግደል ንጹሕ ደም አፍስሰዋል፤ ምድሪቱም በደም ረከሰች።
እስቲ ቀና ብለሽ ወደ ኰረብቶች ራስ ተመልከቺ፤ ከቶ አንቺ ለጣዖቶች ያልሰገድሽበት ስፍራ ይገኛልን? ቀማኛ፥ ሸማቂ፥ ዘላን በበረሓ ተቀምጦ ሊዘርፈው የሚፈልገውን መንገደኛ እንደሚጠባበቅ፥ አንቺም ፍቅረኛዋን ለማጥመድ በየመንገዱ ዳር እንደምትጠባበቅ ሴት ሆነሽ በአምልኮ ዝሙትሽ ኃጢአት ምድርን አረከስሽ።
በጽዮን “ወዮልን ልንጠፋ ነው! ፈጽሞም ተዋረድን! ቤቶቻችን ስለ ፈራረሱ አገራችንን ለቀን መሄዳችን ነው” እየተባለ የሚያስተጋባውን የለቅሶ ጩኸት አድምጡ።
“የሰው ልጅ ሆይ! የእስራኤል ሕዝብ በዚህች አገር ሲኖሩ በከንቱ አኗኗራቸውና በመጥፎ ሥራቸው ሁሉ ምድሪቱን አርክሰዋት ነበር፤ በፊቴም የነበራቸው አካሄድ፥ ሴት በወር አበባዋ ወቅት እንደ ርኩስ ሆና የምትታይበትን ያኽል ነበር።
ይህን ብታደርጉ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርስዋት ምድር ረጅም ጊዜ እንደማትኖሩባትና በፍጹም እንደምትደመሰሱ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን ምስክር አድርጌ እነግራችኋለሁ።