ማቴዎስ 28:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመልአኩ ፊት እንደ መብረቅ ያበራ ነበር፤ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልኩ እንደ መብረቅ ብሩህ፣ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልኩ እንደ መብረቅ፥ ልብሱ ደግሞ እንደ በረዶ ነጭ ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ። |
“እኔም እየተመለከትኩ ሳለሁ ዙፋኖች ተዘረጉ፤ ያ ጥንታዊው በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፤ ልብሱ እንደ በረዶ፥ ጠጒሩም እንደ ነጭ ሱፍ ነበር፤ ዙፋኑና የዙፋኑ መንኰራኲር እንደሚነድ እሳት ይንበለበሉ ነበር።
ከዚህ በኋላ ደመና የለበሰ ሌላ ብርቱ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱ ዙሪያ ቀስተ ደመና ነበረ፤ ፊቱ እንደ ፀሐይ፥ እግሮቹ እንደ እሳት ዐምዶች ነበሩ፤