በጒድጓዱም አፍ ላይ ድንጋይ ተገጠመበት፤ ማንም ሰው ዳንኤልን አውጥቶ ለማዳን እንዳይሞክር ንጉሡ የራሱን መንግሥታዊ ማኅተምና የባለሟሎቹን ማኅተም አተመበት።
ማቴዎስ 27:66 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሄደው ድንጋዩን በማኅተም አሸጉና መቃብሩን በወታደሮች አስጠበቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ሄደው መቃብሩን በማኅተም አሽገው ጠባቂ አቆሙበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሄደውም መቃብሩን ድንጋዩን በማተም ጠባቂዎች አቆሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ሄደው ከጠባቆች ጋር ድንጋዩን አትመው መቃብሩን አስጠበቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ሄደው ከጠባቆች ጋር ድንጋዩን አትመው መቃብሩን አስጠበቁ። |
በጒድጓዱም አፍ ላይ ድንጋይ ተገጠመበት፤ ማንም ሰው ዳንኤልን አውጥቶ ለማዳን እንዳይሞክር ንጉሡ የራሱን መንግሥታዊ ማኅተምና የባለሟሎቹን ማኅተም አተመበት።
ይህንንም ያሉት መቃብሩ የተዘጋበት ድንጋይ እጅግ ትልቅ ስለ ነበረ ነው፤ ቀና ብለውም በተመለከቱ ጊዜ ግን ድንጋዩ ወደ ጐን ተንከባሎ አዩት።
እሑድ ጠዋት በማለዳ፥ ገና ጎሕ ሳይቀድ፥ መግደላዊት ማርያም ወደ ኢየሱስ መቃብር ሄደች፤ እዚያም እንደ ደረሰች መቃብሩ ተዘግቶበት የነበረው ድንጋይ ከመቃብሩ በር ላይ ተነሥቶ አየች።
ነገር ግን “ጌታ የራሱ የሆኑትን ያውቃል፤” እንዲሁም “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከክፋት ይራቅ” የሚል ማኅተም ያለበት የማይነቃነቅ የእግዚአብሔር መሠረት ጸንቶ ይኖራል።
ሺህ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ ሕዝቦችን እንዳያስት መልአኩ ዘንዶውን ወደ ጥልቁ ጒድጓድ ጣለው፤ ዘግቶም በማኅተም አሸገው፤ ከዚያ በኋላ ለጥቂት ጊዜ መፈታት ይገባዋል።