ማቴዎስ 24:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታላቅ የእምቢልታ ድምፅ የሚያሰሙ መላእክቱን ይልካል፤ እነርሱ በአራቱም የዓለም ማዕዘኖች ሄደው ከሰማይ ዳርቻ እስከ ሰማይ ዳርቻ ያሉትን የእርሱን ምርጥ ሰዎች ይሰበስባሉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም መላእክቱን ከታላቅ የመለከት ድምፅ ጋራ ይልካቸዋል፤ እነርሱም ምርጦቹን ከአራቱ ነፋሳት፣ ከሰማያት ከአንዱ ዳርቻ ወደ ሌላው ዳርቻ ይሰበስባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መላእክቱን ከታላቅ መለከት ጋር ይልካቸዋል፤ የእርሱን ምርጦች ከሰማያት ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ይሰበስባሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፤ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፥ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ። |
በሦስተኛው ቀን ማለዳ የነጐድጓድ ድምፅ አስተጋባ፤ የመብረቅ ብልጭልጭታና ጥቅጥቅ ያለ ደመና በተራራው ላይ ታየ፤ እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ የእምቢልታ ድምፅ ተሰማ። ሰዎቹም በሰፈሩበት ቦታ ፈርተው ተንቀጠቀጡ።
በዚያን ጊዜ ጌታ በመላው ዓለም ተበታትነው ይኖሩ የነበሩትን የእስራኤልንና የይሁዳን ሕዝብ ከአራቱ ማእዘን ሰብስቦ ያመጣቸው መሆኑን ለመንግሥታት ሁሉ የሚያሳውቅበትን አርማ ከፍ አድርጎ ያቆማል።
እነርሱም በምድር ዳርቻ ከሚገኙ ከሩቅ አገሮች የመጡ ናቸው፤ እግዚአብሔር አገሪቱን በሞላ ለማጥፋት የቊጣ መሣሪያ የሆነ ሠራዊቱን አሰልፎአል።
በዚያም ዘመን ትልቅ መለከት ይነፋል፤ በአሦር ምድር ጠፍተው የነበሩትና ወደ ግብጽ ተሰደው የነበሩት እስራኤላውያንም ተመልሰው በኢየሩሳሌም በሚገኘው በተቀደሰው ተራራ ላይ ይሰግዳሉ።
ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር ዘምሩ! የዓለም ሕዝቦች ሁሉ የምስጋና መዝሙር አቅርቡ! በባሕሩ ውስጥ ያሉት ሁሉ፥ የጠረፍ አገሮችና በእነርሱም የሚኖሩ ሁሉ ያመስግኑ!
“ወንዶች ልጆቼ ከሩቅ አገር እንዲመጡ በሰሜን በኩል ያሉትን አገሮች ተዉአቸው፥ በደቡብ በኩል ያሉትን አገሮች ‘አትያዙአቸውም’ ብዬ አዛለሁ።
ቀና ብለሽ ዙሪያሽን ተመልከቺ፤ ልጆችሽ ሁሉ ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ እንዲህ እላለሁ፦ ‘ሁሉንም እንደ ልብስ ትለብሺአቸዋለሽ፤ ሙሽራ በጌጣጌጥ እንደምታጌጥ አንቺም በእነርሱ ታጌጪአለሽ።’
ቀና ብለሽ በዙሪያሽ ያለውን ሁኔታ ተመልከቺ! ሁላቸውም ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ ወንዶች ልጆችሽ ከሩቅ አገር ይመጣሉ፤ ሴቶች ልጆችሽም በሞግዚቶቻቸው ክንድ ሆነው ወደ አንቺ ይመጣሉ።
እናንተም ተራራውን በሁለት ከፍሎ እስከ አጻል በደረሰው በዚህ ሸለቆ ውስጥ አልፋችሁ ታመልጣላችሁ፤ በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያ ዘመን ምድር በተናወጠች ጊዜ የቀድሞ አባቶቻችሁ በሸሹት ዐይነት ትሸሻላችሁ፤ እግዚአብሔር አምላኬም ቅዱሳኑን አስከትሎ ይመጣል።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ ሠረገሎችን ከእስራኤል፥ የጦር ፈረሶችንም ከኢየሩሳሌም አስወግዳለሁ፤ የጦር ቀስቶችን እሰባብራለሁ፤ ንጉሥሽ በሕዝቦች መካከል ሰላም እንዲኖር ያደርጋል፤ ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕርና ከታላቁ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይሆናል።”
እግዚአብሔር ከሕዝቡ በላይ ይገለጣል፤ የእርሱም ፍላጻዎች እንደ መብረቅ ይወረወራሉ፤ እግዚአብሔር አምላክ የመለከት ድምፅ ያሰማል፤ ከደቡብ በኩል እንደሚመጣ ዐውሎ ነፋስ ያልፋል።
በዚያን ጊዜ የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፤ እነርሱም የኃጢአት ምክንያት የሆኑትንና ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ ከእርሱ መንግሥት ሰብስበው ያወጣሉ፤
ሐሰተኞች መሲሖችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉ፤ እነርሱ ቢቻላቸውስ የእግዚአብሔርን ምርጦች እንኳ ለማሳሳት ታላላቅ ተአምራትንና ድንቅ ነገሮችን ያሳያሉ።
መላእክቱንም ይልካል፤ እነርሱ በአራቱም አቅጣጫ ሄደው ከምድር ዳርቻ እስከ ሰማይ ዳርቻ የሚገኙትን፥ ለእርሱ የተመረጡትን ሰዎች ይሰበስባሉ።
እስቲ ልጠይቅ፤ ታዲያ፥ ቃሉን አልሰሙም ማለት ነውን? በቅዱስ መጽሐፍ፥ “ድምፃቸው በዓለም ሁሉ ተሰማ፤ ቃላቸውም እስከ ምድር ዳርቻ ደረሰ” ተብሎ እንደ ተጻፈው፥ በእርግጥ ሰምተዋል።
የምንለወጠውም የመጨረሻው እምቢልታ በሚነፋበት ጊዜ እንደ ዐይን ቅጽበት በአንድ ጊዜ ነው። መለከቱ ይነፋል፤ የሞቱትም ሰዎች የማይጠፉ ሕያዋን ሆነው ይነሣሉ፤ እኛም እንለወጣለን፤
ጊዜው ሲደርስ እግዚአብሔር በሥራ ላይ የሚያውለው ዕቅድ በሰማይና በምድር ያሉት ፍጥረቶች ሁሉ ተጠቃለው በአንዱ በክርስቶስ ሥልጣን ሥር እንዲሆኑ ነው።
“እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ ከፈጠረበት ጊዜ አንሥቶ እናንተ ከመወለዳችሁ በፊት በነበረው ዘመን ያለፈውን ነገር ሁሉ እስቲ መርምሩ፤ ምድርን በሞላ መርምሩ፤ ከዚህ በፊት ይህን የመሰለ ታላቅ ነገር ከቶ ተደርጎ ያውቃልን? እንደዚህ ያለውን ነገር የሰማ ከቶ አለ ይሆን?
የትእዛዝ ድምፅ፥ የመላእክት አለቃ ድምፅ፥ የእግዚአብሔር እምቢልታም ይሰማል፤ ጌታ ራሱም በእነዚህ ታጅቦ ከሰማይ ይወርዳል፤ በክርስቶስ አምነው የሞቱትም አስቀድመው ይነሣሉ።
የእምቢልታ ድምፅ ወይም የሚነገረው ቃል ወደሚሰማበትም አልደረሳችሁም፤ ያንን ቃል የሰሙ ሰዎች “ከእንግዲህ ወዲህ ሌላ ቃል አይነገረን” በማለት እስከ መለመን ደርሰዋል።
በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ኮከቦችና የሰባቱም የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ኮከቦች የሰባቱ አብያተ ክርስቲያን መላእክት ናቸው፤ ሰባቱ መቅረዞችም ሰባት አብያተ ክርስቲያን ናቸው።”
ሰባተኛውም መልአክ እምቢልታውን ነፋ፤ በሰማይም “የዓለም መንግሥት የጌታ የአምላካችንና የመሲሑ ሆናለች፤ እርሱ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል፤” የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ።
ከዚህ በኋላ አራት መላእክት በአራቱ የምድር ማእዘኖች ቆመው አየሁ፤ እነርሱ በምድርም ሆነ በባሕር ወይም በዛፍ ላይ ምንም ነፋስ እንዳይነፍስ ከአራቱ አቅጣጫ የሚመጡትን የምድር ነፋሶች ያዙ።