ማቴዎስ 22:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ነገር ግን ንጉሡ ተጋባዦቹን ለማየት ወደ አዳራሽ በገባ ጊዜ፥ የሠርግ ልብስ ያልለበሰ አንድ ሰው በዚያ አየ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ንጉሡም የተጋበዙትን እንግዶች ለማየት ሲገባ፣ አንድ የሰርግ ልብስ ያልለበሰ ሰው አየ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ንጉሡም ተጋባዦቹን ለማየት በገባ ጊዜ፥ የሰርግ ልብስ ያልለበሰ አንድ ሰው በዚያ አየ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ንጉሡም የተቀመጡትን ለማየት በገባ ጊዜ በዚያ የሰርግ ልብስ ያለበሰ አንድ ሰው አየና ‘ወዳጄ ሆይ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም የተቀመጡትን ለማየት በገባ ጊዜ በዚያ የሰርግ ልብስ ያለበሰ አንድ ሰው አየና፦ ወዳጄ ሆይ፥ |
ጽዮን ሆይ! ተነሺ፤ ንቂ! ኀይልሽን እንደ ልብስ ልበሺ! ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ! የተዋበ ልብስሽን ልበሺ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ያልተገረዙና በሥርዓት ያልነጹ ሰዎች ወደ ቅጥርሽ ውስጥ አይገቡም።
እኛ ሁላችን በኃጢአት ረክሰናል፤ ጽድቃችንም እንደ አደፍ ጨርቅ ሆኖአል፤ ከኃጢአታችን ብዛት የተነሣ ደርቀው በነፋስ እንደሚረግፉ ቅጠሎች ሆነናል።
“በዚያን ቀን መብራት ይዤ ኢየሩሳሌምን እፈትሻለሁ፤ በመንደላቀቅ ኑሮ በአተላ ውስጥ አቅርሮ እንደ ቀረ የወይን ጠጅ የሆኑትንና ‘እግዚአብሔር በጎም ሆነ ክፉ ነገር አያደርግም’ የሚሉትን እቀጣለሁ።
ስለዚህ ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ ድረስ ስንዴውም እንክርዳዱም አብረው ይደጉ፤ በመከር ጊዜ ዐጫጆችን እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ንቀሉ፤ በእሳት እንዲቃጠልም በየነዶው እሰሩ፤ ስንዴውን ግን ሰብስቡና በጐተራዬ ክተቱ’ እላቸዋለሁ።”
እርሱ መንሹ በእጁ ነው። በእርሱም አውድማውን ደኅና አድርጎ ያጠራል። ስንዴውን በጐተራ ይከተዋል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”
ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ፥ ጌታ ለፍርድ ከመምጣቱ በፊት በማንም ላይ አትፍረዱ፤ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ በጨለማ የተሰወረውን ምሥጢር ወደ ብርሃን ያወጣዋል፤ በሰዎች ልብ የተደበቀውን ሐሳብ ይገልጠዋል፤ በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ተገቢውን ምስጋና ያገኛል።
“እነሆ! እኔ እንደ ሌባ በድንገት እመጣለሁ! ራቁቱን እንዳይሆንና ኀፍረቱን ሰዎች እንዳያዩበት ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ሰው የተመሰገነ ነው!”
ልጆችዋንም በሞት እቀጣለሁ፤ አብያተ ክርስቲያንም ሁሉ የሰውን ሐሳብና ምኞት የምመረምር እኔ መሆኔን ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደየሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።
ሀብታም ለመሆን በእሳት የተፈተነውን ወርቅ ከእኔ እንድትገዛ፥ የራቊትነትህን ኀፍረት ለመሸፈን ነጭ ልብስ እንድትለብስ፥ ለማየትም እንድችል የዐይን መድኃኒት ገዝተህ እንድትቀባ እመክርሃለሁ።