ማቴዎስ 16:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ “እኔን መከተል የሚፈልግ ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ “ሊከተለኝ የሚወድድ ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው “ሊከተለኝ የሚወድ ራሱን ይካድ፥ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ “እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ። |
ኢየሱስም ተመለከተውና ወደደው፤ እንዲህም አለው፦ “አንድ ነገር ብቻ ቀርቶሃል፤ ሂድ፤ ያለህን ሁሉ ሸጠህ ገንዘብህን ለድኾች ስጥ፤ የተከማቸ ሀብት በሰማይ ታገኛለህ፤ ከዚህም በኋላ ና፤ ተከተለኝ።”
ሲሄዱም ሳሉ የቀሬና ሰው የሆነውን የእስክንድርንና የሩፎስን አባት ስምዖንን ከገጠር ወደ ከተማ ሲገባ አገኙት፤ የኢየሱስን መስቀል እንዲሸከም አስገደዱት።
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ሕዝቡን ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ሊከተለኝ የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ፤
ስለዚህ ኢየሱስን ወሰዱት፤ ይዘውት ሲሄዱ ሳሉም የቀሬና ሰው የሆነውን ስምዖንን ከገጠር ወደ ከተማ ሲገባ አገኙት፤ እርሱን ይዘው የኢየሱስን መስቀል አሸከሙትና ኢየሱስን እንዲከተል አደረጉት።
በእነዚያም አገሮች ሁሉ አማኞች በእምነታቸው እንዲጸኑ በማበረታታትና በመምከር “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት ብዙ መከራ መቀበል አለብን” እያሉ አስተማሩአቸው።
አሁን ስለ እናንተ በምቀበለው መከራ ደስ ይለኛል፤ አካሉ ስለ ሆነችው ስለ ቤተ ክርስቲያንም ከክርስቶስ መከራ ከመካፈል የጐደለብኝን በሥጋዬ አሟላለሁ።