መልአኩም “ልጁን አትንካ፤ ምንም ዐይነት ጒዳት አታድርስበት፤ አንድ ልጅህን እንኳ ለእኔ ከመስጠት ስለ አልተቈጠብክ እነሆ፥ እኔን እግዚአብሔርን የምትፈራ መሆንህን ተረድቼአለሁ።”
ማርቆስ 12:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁን ማድረግ የቀረው የሚወደውን ልጁን መላክ ብቻ ነበር፤ ስለዚህ ‘ልጄንስ ያከብሩት ይሆናል’ ብሎ በማሰብ በመጨረሻ አንድ ልጁን ላከ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አሁንም የሚላክ ሌላ ነበረው፤ እርሱም የሚወድደው ልጁ ነበረ፤ ‘ልጄንስ ያከብሩታል’ በማለት ከሁሉ በኋላ ላከው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም የሚላክ ሌላ ነበረው፤ እርሱም የሚወደው ልጁ ነበረ፤ “ልጄንስ ያከብሩታል” በማለት ከሁሉ በኋላ ላከው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚወደው አንድ ልጅ ገና ነበረው፤ ‘ልጄንስ ያፍሩታል፤’ ብሎ እርሱን ከሁሉ በኋላ ወደ እነርሱ ላከ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚወደው አንድ ልጅ ገና ነበረው፤ ልጄንስ ያፍሩታል ብሎ እርሱን ከሁሉ በኋላ ወደ እነርሱ ላከ። |
መልአኩም “ልጁን አትንካ፤ ምንም ዐይነት ጒዳት አታድርስበት፤ አንድ ልጅህን እንኳ ለእኔ ከመስጠት ስለ አልተቈጠብክ እነሆ፥ እኔን እግዚአብሔርን የምትፈራ መሆንህን ተረድቼአለሁ።”
እግዚአብሔርም “የምትወደውን አንድ ልጅህን ይስሐቅን ይዘህ ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ፤ እዚያ በማሳይህ አንድ ኮረብታ ላይ እርሱን መሥዋዕት አድርገህ አቅርብልኝ” አለው።
እኛም ‘ሽማግሌ አባት አለን፤ በስተርጅና የወለደውም ታናሽ ወንድም አለን፤ የልጁ ወንድም ሞቶአል፤ ከእናቱ ልጆች የቀረው እርሱ ብቻ ስለ ሆነ አባቱ በጣም ይወደዋል’ ብለንህ ነበር፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ የምደግፈው የመረጥኩትና በእርሱም ደስ የሚለኝ አገልጋዬ ይህ ነው፤ መንፈሴ በእርሱ እንዲያድርበት አደርጋለሁ፤ እርሱ ለሕዝቦች ሁሉ ትክክለኛ ፍርድን ያመጣል።
“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙም ‘ዐማኑኤል’ ተብሎ ይጠራል።” ዐማኑኤል ማለትም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው” ማለት ነው።
አባቴ ሁሉን ነገር ሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ ማንም የለም። እንዲሁም ከወልድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም፤ ማንም ወልድ ካልገለጠለት በቀር አብን ሊያውቅ አይችልም።
ጴጥሮስ ገና ይህን ሲናገር ሳለ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ ከደመናውም ውስጥ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት!” የሚል ድምፅ መጣ።
ኢየሱስ ግን ዝም አለ። የካህናት አለቃውም እንደገና ኢየሱስን “በሕያው እግዚአብሔር ስም ይዤሃለሁ! አንተ የእግዚአብሔር ልጅ መሲሕ እንደ ሆንክ ንገረን!” አለው።
መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ሆኖ በእርሱ ላይ ወረደ፤ በዚያኑ ጊዜ “አንተ የተወደድክ ልጄ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል” የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ።
ይህንንም ያደረገው ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩ፥ እንዲሁም ወልድን እንዲያከብሩ ነው፤ ወልድን የማያከብር፥ ወልድን የላከውን አብን አያከብርም።