ነቢዩ ኤልሳዕም የሆነውን ነገር ሁሉ በሰማ ጊዜ ወደ ንጉሡ መልእክት ልኮ “ስለምን ልብስህን ቀደድክ? ሰውየውን ወደ እኔ ላከው፤ እኔም በእስራኤል ነቢይ መኖሩን አሳየዋለሁ!” አለው።
ሉቃስ 9:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም እንዲህ አለ፦ “እናንተ እምነት የሌላችሁ ጠማማ ትውልድ! እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? እስቲ ልጅህን ወዲህ አምጣው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም “የማታምን ጠማማ ትውልድ ሆይ፤ እስከ መቼ ከእናንተ ጋራ እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ልጅህን ወደዚህ አምጣው!” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም መልሶ፦ “የማታምን ጠማማ ትውልድ ሆይ! እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ልጅህን ወደዚህ አምጣው፤” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፥ “የማታምን ከዳተኛ ትውልድ፥ እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ልጅህን ወደዚህ አምጣው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም መልሶ፦ እናንተ የማታምን ጠማማ ትውልድ፥ እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ልጅህን ወደዚህ አምጣው አለ። |
ነቢዩ ኤልሳዕም የሆነውን ነገር ሁሉ በሰማ ጊዜ ወደ ንጉሡ መልእክት ልኮ “ስለምን ልብስህን ቀደድክ? ሰውየውን ወደ እኔ ላከው፤ እኔም በእስራኤል ነቢይ መኖሩን አሳየዋለሁ!” አለው።
እንደ ቀድሞ አባቶቻቸው ዐመፀኞችና እምቢተኞች አይሆኑም፤ እነዚያ እግዚአብሔርን በማመን የጸኑ አልነበሩም፤ ለእግዚአብሔር ታማኞች ሆነው አልኖሩም።
ስለዚህ ሙሴና አሮን ወደ ንጉሡ ሄደው እንዲህ አሉት፤ “የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ለእኔ መታዘዝን እምቢ የምትለው እስከ መቼ ነው? አሁንም ያገለግለኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ፤
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ይህ ሕዝብ እኔን የሚንቀው እስከ መቼ ነው? ብዙ ተአምራትን በፊቱ አድርጌአለሁ፤ ታዲያ፥ በእኔ መታመንን እምቢ የሚለው እስከ መቼ ነው?
“እነዚህ ክፉዎች የሆኑ ሰዎች በእኔ ላይ የሚያጒረመርሙት እስከ መቼ ነው? እነዚህ አጒረምራሚዎች እስራኤላውያን በእኔ ላይ ማጒረምረማቸውን ሰምቻለሁ።
እርሱ ግን እንዲህ ሲል መለሰላቸው “ክፉና የማያምን ትውልድ ተአምር ለማየት ይፈልጋል፤ ነገር ግን ከነቢዩ ከዮናስ ተአምር በቀር ሌላ ተአምር አይሰጠውም።
ከዚህ በኋላ፥ ርኩሱ መንፈስ ይሄድና ከእርሱ ይብስ የከፉትን ሌሎች ሰባት አጋንንት ይዞ ይመጣል። እነርሱም ቀድሞ የጋኔኑ ቤት ወደ ነበረው ሰው ልብ ገብተው አብረው በዚያ ይኖራሉ። ስለዚህ የዚያ ሰው የኋለኛው ሁኔታ ከመጀመሪያው ይልቅ የከፋ ይሆናል። በዚህ ክፉ ትውልድ ላይ የሚሆነው ይህንኑ የመሰለ ነገር ነው።”
ክፉና የማያምን ትውልድ፥ ምልክት ለማየት ይፈልጋል፤ ነገር ግን ከነቢዩ ዮናስ ምልክት በቀር ሌላ ምልክት አይሰጠውም።” ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ትቶአቸው ወደ ሌላ ስፍራ ሄደ።
ኢየሱስም “እናንተ የማታምኑ ጠማማ ትውልድ! እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? እስቲ ልጁን ወደ እኔ አምጡት!” አላቸው።
ነገር ግን፥ ዮሐንስ ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ለመጠመቅ ወደ እርሱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የእባብ ልጆች! ከሚመጣው ቊጣ እንድታመልጡ ማን አስጠነቀቃችሁ?
ኢየሱስም ይህን በማየት ተቈጥቶ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “የእግዚአብሔር መንግሥት እንደነዚህ ላሉት ስለ ሆነች ሕፃናት ወደ እኔ ይምጡ፤ ተዉ፤ አትከልክሉአቸው፤
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የማታምኑ ሰዎች! እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? እስቲ ልጁን ወደ እኔ አምጡት!”
ከዚያም በኋላ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፥ “እምነታችሁ የት አለ?” አላቸው። እነርሱ ግን እጅግ ተደንቀውና ፈርተው እርስ በርሳቸው፥ “ነፋስንና ማዕበልን ያዛል፤ እነርሱም ይታዘዙለታል፤ ለመሆኑ ይህ ማን ነው?” ተባባሉ።
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ፊልጶስ ሆይ! ይህን ያኽል ጊዜ ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አየ፤ ታዲያ፥ አንተ ‘አብን አሳየን’ እንዴት ትላለህ?
ከዚህ በኋላ ቶማስን፥ “ጣትህን ወዲህ አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና በጐኔ ውስጥ አግባው፤ እመን እንጂ እምነተ ቢስ አትሁን” አለው።
ወይስ የእግዚአብሔርን የደግነቱንና የቻይነቱን፥ የታጋሽነቱንም ብዛት ትንቃለህን? እግዚአብሔር ደግነቱን ያበዛልህ አንተን ወደ ንስሓ ለመምራት እንደ ሆነ አታውቅምን?
ስለዚህ እነርሱን ለማማለድ ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ ስለሚኖር በእርሱ አማካይነት ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ሁሉ በፍጹም ሊያድናቸው ይችላል።