ከቶ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? እንደ ነገርኩህ የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ ተመልሼ እመጣለሁ፤ በዚያን ጊዜ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች” አለው።
ሉቃስ 5:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ቀን ኢየሱስ በአንዲት ከተማ ውስጥ ሳለ ገላውን ለምጽ የወረሰው አንድ ሰው ወደ እርሱ መጣ፤ ኢየሱስን ባየው ጊዜ በግንባሩ ተደፍቶ ጌታ ሆይ፥ “ብትፈቅድስ ልታነጻኝ ትችላለህ፤” ሲል ለመነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ከከተሞች በአንዱ በነበረበት ጊዜ፣ አንድ ለምጽ የወረሰው ሰው በዚያው ከተማ ነበር፤ ይህ ሰው ኢየሱስን ባየው ጊዜ በፊቱ ተደፋና፣ “ጌታ ሆይ፤ ብትፈቅድ እኮ ልታነጻኝ ትችላለህ” ብሎ ለመነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከከተማዎችም በአንዲቱ ሳለ፥ እነሆ፥ ለምጽ የወረሰው አንድ ሰው ነበረ፤ ኢየሱስንም ባየው ጊዜ በግንባሩ ተደፍቶ፦ “ጌታ ሆይ! ብትፈቅድስ ልታነጻኝ ትችላለህ፤” ሲል ተማጸነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአንዲት ከተማ ሳለም ሁለመናው ለምጻም የሆነ ሰው መጣ፤ ጌታችን ኢየሱስንም ባየው ጊዜ በፊቱ ወድቆ ሰገደለትና፥ “አቤቱ ብትወድስ ልታነጻኝ ትችላለህ” እያለ ማለደው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከከተማዎችም በአንዲቱ ሳለ፥ እነሆ፥ ለምጽ የሞላበት ሰው ነበረ፤ ኢየሱስንም አይቶ በፊቱ ወደቀና፦ ጌታ ሆይ፥ ብትወድስ፥ ልታነጻኝ ትችላለህ ብሎ ለመነው። |
ከቶ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? እንደ ነገርኩህ የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ ተመልሼ እመጣለሁ፤ በዚያን ጊዜ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች” አለው።
እግዚአብሔር በንዕማን አማካይነት ለሶርያ ሠራዊት ድልን ስለ አጐናጸፈ፥ የሶርያ ጦር አዛዥ የነበረው ንዕማን በሶርያ ንጉሥ ዘንድ እጅግ የተከበረና የተወደደ ባለሟል ነበር፤ ታዲያ ንዕማን ጀግና ወታደር ሆኖ ሳለ፥ በቈዳ በሽታ ይሠቃይ ነበር።
ከዚህም የተነሣ እነሆ፥ የንዕማን የቆዳ በሽታ ወደ አንተ ይተላለፋል፤ አንተና ዘሮችህ ለዘለዓለም ከዚያ በሽታ አትነጹም!” አለው። ግያዝም ወጥቶ ሲሄድ፥ ያ የቆዳ በሽታ ስለ ተጋባበት ገላው እንደ በረዶ ነጭ ሆነ።
ሰውነታቸው የቆዳ በሽታ የያዛቸው አራት ሰዎች ከሰማርያ ቅጽር በር ውጪ ነበሩ፤ እነርሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፤ “እስክንሞት ድረስ ስለምን በዚህ እንቈያለን?
ዳዊትም መልአኩ ኢየሩሳሌምን ለመደምሰስ ሰይፉን በእጁ እንደ ያዘ በምድርና በሰማይ መካከል ቆሞ አየው፤ በዚህ ጊዜ ዳዊትና ማቅ ለብሰው የነበሩት የሕዝቡ አለቆች በሙሉ በግንባራቸው በመሬት ላይ ተደፉ።
እንደገናም እግዚአብሔር ሙሴን “እጅህን ወደ ብብትህ አስገባው” አለው፤ እርሱም እጁን ወደ ብብቱ አስገባ፤ እጁንም ከብብቱ ባወጣው ጊዜ እንደ በረዶ ነጭ ሆነ።
እሳትም በድንገት ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ፥ በመሠዊያው ላይ የነበረውን መሥዋዕትና ስብ ሁሉ በላ፤ ሕዝቡ ሁሉ ይህን ባዩ ጊዜ እልል አሉ፤ በምድር ላይም በግንባራቸው ተደፍተው ሰገዱ።
ኢየሱስ ወደ ቤት በገባ ጊዜ ዕውሮቹ ወደ እርሱ ቀረቡ፤ እርሱም “እኔ ይህን ማድረግ እንደምችል ታምናላችሁን?” አላቸው። እነርሱም “አዎ፥ ጌታ ሆይ!” ሲሉ መለሱ።
ስለዚህ እነርሱን ለማማለድ ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ ስለሚኖር በእርሱ አማካይነት ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ሁሉ በፍጹም ሊያድናቸው ይችላል።
ጐልማሳውም “የእናንተም ሆነ የጠላት ወገን አይደለሁም፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሠራዊት አዛዥ እንደ መሆኔ መጠን እነሆ፥ መጥቻለሁ” አለ። ኢያሱም ወደ መሬት ወድቆ ሰገደለትና “ጌታዬ ሆይ፥ እኔ አገልጋይህ ምን ልታዘዝ?” አለው።