ሉቃስ 21:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ ስሜም በሰው ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ስሜም በሰዎች ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሁሉም ከስሜ የተነሣ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁሉም ስለ ስሜ ይጠሉአችኋል፤ ይገድሉአችኋልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሁሉም ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ። |
የዓለም ብትሆኑ ዓለም የራሱ የሆነውን በወደደ ነበር፤ ነገር ግን የዓለም ስላልሆናችሁና እኔ ከዓለም ለይቼ ስለ መረጥኳችሁ፥ ዓለም ይጠላችኋል።
እኛ የምናስተምረው ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ መሆኑንና እኛም ራሳችን ስለ ኢየሱስ የእናንተ አገልጋዮች መሆናችንን ነው እንጂ ስለ ራሳችንስ አንሰብክም።