ሉቃስ 13:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በጠባብዋ በር ለመግባት ተጣጣሩ፤ በዚህች በር መግባት የሚፈልጉ ብዙዎች ናቸው፤ ነገር ግን መግባት አይችሉም እላችኋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በጠባቡ በር ለመግባት ተጣጣሩ፤ እላችኋለሁ፤ ብዙዎች ለመግባት ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን አይችሉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በጠበበው በር ለመግባት ተጋደሉ፤ ብዙዎች ሊገቡ ይፈልጋሉ፥ አይችሉምም እላችኋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ወደ ጠባቡ በር ትገቡ ዘንድ በርቱ፤ እላችኋለሁ፥ ሊገቡ የሚሹ ብዙዎች ናቸው፤ ግን አይችሉም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጠበበው በር ለመግባት ተጋደሉ፤ እላችኋለሁና፥ ብዙዎች ሊገቡ ይፈልጋሉ አይችሉምም። |
“እጆቻችሁን ወደ እኔ ለጸሎት ብትዘረጉ፥ ወደ እናንተ አልመለከትም፤ እጆቻችሁ በደም የተበከሉ ስለ ሆኑ የቱንም ያኽል ልመና ብታበዙ አልሰማችሁም፤
ስለዚህም ሌሎች ሕዝቦች እንደሚያደርጉት ሕዝቤ አንተ ምን እንደምትናገር ለማዳመጥ ብቻ ይሰበሰባሉ፤ ነገር ግን የምትነግራቸውን ሁሉ አይፈጽሙም፤ የምትናገረውን ቃል የሚወዱት መስለው ይታያሉ፤ ነገር ግን ከበዝባዥነታቸው አይመለሱም፤
ልጆቼ ሆይ፥ ከእናንተ ጋር ብዙ ጊዜ አልቆይም፤ እናንተም ትፈልጉኛላችሁ፤ ለአይሁድ ባለሥልጣኖች ‘እኔ ወደምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም’ እንዳልኳቸው፥ አሁንም ለእናንተ እንዲሁ እላችኋለሁ።
አልፎ አልፎ የጌታ መልአክ ወደ ኲሬው ወርዶ ውሃውን ያናውጥ ነበር፤ ከውሃው መናወጥ በኋላ በመጀመሪያ ወደ ኲሬው የሚገባ ካደረበት ከማንኛውም በሽታ ይፈወስ ነበር።]
ለሚጠፋ ምግብ አትሥሩ፤ ይልቅስ እግዚአብሔር አብ የማረጋገጫ ማኅተም ስለ አተመው የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ፥ የዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው ምግብ ሥሩ።”
እንደገናም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “እኔ እሄዳለሁ፤ እናንተም እኔን ትፈልጉኛላችሁ፤ ነገር ግን ከነኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ እንጂ እኔ ወደምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም።”
ለኢያሱ ከዚህ የሚከተለውን ማስረጃ አቀረቡለት፦ “እነርሱ ጥቂቶች ስለ ሆኑ በዐይ ላይ አደጋ ለመጣል ያለውን ሰው ሁሉ በአጠቃላይ ማዝመት አያስፈልግም፤ ሁለት ወይም ሦስት ሺህ ሰዎች ብቻ ላክ፤ በዚያ ለመዋጋት መላውን ሠራዊት አትላክ።”