ለዚህም ቃል ያ አገልጋዩ የሰጠው መልስ “እግዚአብሔር ራሱ የሰማይ መስኮቶችን ከፍቶ እህልን እንደ ዝናብ ቢያዘንብ እንኳ ይህ ሊሆን ከቶ አይችልም!” የሚል ነበር። ኤልሳዕም “ያን እህል በዐይንህ ታያለህ፤ ነገር ግን ከእርሱ ምንም ነገር አትቀምስም” ብሎት ነበር።
ሉቃስ 1:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ ግን ጊዜው ሲደርስ የሚፈጸመውን ቃሌን አላመንክም፤ ስለዚህ ይህ የነገርኩህ ሁሉ እስከሚፈጸም ድረስ ድዳ ትሆናለህ፤ መናገርም አትችልም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ ጊዜውን ጠብቆ የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንህ፣ ይህም እስከሚፈጸምበት ቀን ድረስ ድዳ ትሆናለህ፤ መናገርም አትችልም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆም፥ በጊዜያቸው የሚፈጸሙትን ቃሎቼን ስላላመንህ፥ ይህ ነገር እስከሚሆንበት ቀን ድረስ አንደበትህ ይታሰራል፤ መናገርም አትችልም፤” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም በጊዜው የሚሆነውንና የሚፈጸመውን ነገሬን አላመንኽኝምና ይህ እስኪሆን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ፤ መናገርም ይሳንሃል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆም፥ በጊዜው የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንህ፥ ይህ ነገር እስከሚሆን ቀን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ መናገርም አትችልም አለው። |
ለዚህም ቃል ያ አገልጋዩ የሰጠው መልስ “እግዚአብሔር ራሱ የሰማይ መስኮቶችን ከፍቶ እህልን እንደ ዝናብ ቢያዘንብ እንኳ ይህ ሊሆን ከቶ አይችልም!” የሚል ነበር። ኤልሳዕም “ያን እህል በዐይንህ ታያለህ፤ ነገር ግን ከእርሱ ምንም ነገር አትቀምስም” ብሎት ነበር።
በዚህ ጊዜ የንጉሡ የቅርብ ባለሟል የሆነ አገልጋዩ ኤልሳዕን፥ “እግዚአብሔር ራሱ የሰማይ መስኮቶችን ከፍቶ እህልን እንደ ዝናብ ቢያዘንብ እንኳ ይህ ሊሆን ከቶ አይችልም!” ሲል በመጠራጠር ተናገረ። ኤልሳዕም “ያን እህል በዐይንህ ታያለህ፤ ነገር ግን ከእርሱ ምንም ነገር አትቀምስም!” አለው።
ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለሰው አፍን የፈጠረለት ማነው? ድዳ ወይም ደንቆሮ፥ ዐይኑ እንዲያይ ወይም እንዳያይ የሚያደርግስ ማነው? ይህን ሁሉ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን?
በዚያኑ ቀን ከዚህ በፊት አጥተኸው የነበረውን የመናገር ችሎታ መልሰህ ታገኛለህ፤ ከእርሱም ጋር ትነጋገራለህ ለሕዝቡም ምልክት ትሆናለህ፤ እነርሱም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”
ነገር ግን እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ ሲል ገሠጻቸው፤ “በእስራኤላውያን ፊት የተቀደሰ ክብሬን ትገልጡ ዘንድ ስላላመናችሁብኝ፥ ልሰጣቸው ቃል ወደገባሁላቸው ምድር የዚህ ሕዝብ መሪዎች ሆናችሁ አትገቡም።”
ከዚያም በኋላ ዐሥራ አንዱ በማእድ ቀርበው ሲበሉ ኢየሱስ ተገለጠላቸው፤ “ኢየሱስ ከሞት ተነሥቶ በሕይወት አለ፤ በዐይናችንም አይተነዋል፤” ብለው የነገሩአቸውን ባለማመናቸውና በግትርነታቸው ነቀፋቸው።
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የማታምኑ ሰዎች! እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? እስቲ ልጁን ወደ እኔ አምጡት!”
መልአኩም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፤ ይህን የምሥራች እንድነግርህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኬ መጥቻለሁ።
ዘካርያስ ከቤተ መቅደስ በወጣ ጊዜ ከሰዎቹ ጋር መነጋገር አልቻለም፤ ስለዚህ እነርሱ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ራእይ የታየው መሆኑን ዐወቁ፤ እርሱ በእጁ እየጠቀሰ ያስረዳቸው ነበር። በዚህም ሁኔታ ዱዳ ሆኖ ቈየ።
በዚሁ ዐይነት እግዚአብሔር የማይለወጡትንና የማይዋሽባቸውን ሁለቱን ነገሮች፥ ማለትም ተስፋውንና መሐላውን ሰጥቶናል፤ በእነዚህም በሁለቱ ነገሮች አማካይነት በፊታችን ያለውን ተስፋ አጥብቀን መያዝ እንድንችል መጠጊያ ለማግኘት ወደ እርሱ የሸሸን እኛ ታላቅ መጽናናትን እናገኛለን።