በገለዓድ የምትገኘው የቱቢ ተወላጅ የሆነውና ኤልያስ ተብሎ የሚጠራው ነቢይ፤ ንጉሥ አክዓብን “በእኔ ቃል ካልሆነ በቀር በሚቀጥሉት ዓመቶች በምድር ላይ ጠል ወይም ዝናብ እንደማይኖር እኔ በማገለግለው በእስራኤል አምላክ፥ በሕያው እግዚአብሔር ስም እነግርሃለሁ” አለው።
ሉቃስ 1:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልክ እንደ ነቢዩ ኤልያስ በመንፈስና በኀይል ሆኖ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆቻቸው፥ የማይታዘዙትንም ሰዎች ልብ ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልሳል፤ ሕዝቡንም በማንቃት ለጌታ እንዲዘጋጅ ያደርጋል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአባቶችን ልብ ወደ ልጆቻቸው፣ የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ፣ ለጌታ የተገባ ሕዝብ ለማዘጋጀት በኤልያስ መንፈስና ኀይል በጌታ ፊት ይሄዳል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም የተዘጋጀን ሕዝብ ለጌታ አሰናድቶ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ለመመለስ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የከሓድያንንም ዐሳብ ወደ ጻድቃን ዕውቀት ይመልስ ዘንድ፥ ሕዝብንም ለእግዚአብሔር የተዘጋጀ ያደርግ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኀይል በፊቱ ይሄዳል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል። |
በገለዓድ የምትገኘው የቱቢ ተወላጅ የሆነውና ኤልያስ ተብሎ የሚጠራው ነቢይ፤ ንጉሥ አክዓብን “በእኔ ቃል ካልሆነ በቀር በሚቀጥሉት ዓመቶች በምድር ላይ ጠል ወይም ዝናብ እንደማይኖር እኔ በማገለግለው በእስራኤል አምላክ፥ በሕያው እግዚአብሔር ስም እነግርሃለሁ” አለው።
ኤልያስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “የእግዚአብሔርን ትእዛዞች በመጣስ ባዓል ተብሎ ለሚጠራው የባዕድ አምላክ ምስሎች በመስገድ ችግር የምታመጡ አንተና የአባትህ ቤተሰብ ናችሁ እንጂ እኔ በእስራኤል ላይ ችግር የማመጣ አይደለሁም!
አክዓብ ኤልያስን ባየው ጊዜ “ጠላቴ ሆይ! አገኘኸኝን?” አለው። ኤልያስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “አዎ! አግኝቼሃለሁ፤ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ሁሉ ለማድረግ ራስህን ለኃጢአት ሸጠሃል፤
“እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ ‘በእስራኤል አምላክ እንደሌለ በመቊጠር፥ የዔክሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን እንዲጠይቁልህ መልእክተኞች በመላክህ ምክንያት ትሞታለህ እንጂ አትድንም!’ ” አለው።
የቀድሞ አባቶቻችን የአብርሃም፥ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ይህ ታላቅ ፍቅር በሕዝብህ በእስራኤላውያን ልብ ለዘለዓለም ጸንቶ እንዲኖር አድርግ፤ ዘወትርም ለአንተ ታማኞች እንዲሆኑ አድርጋቸው፤
እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው፤ ትእዛዙን የሚፈጽሙትን ሁሉ አስተዋዮች ያደርጋቸዋል፤ እግዚአብሔር ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን!
እንደ ቀድሞ አባቶቻቸው ዐመፀኞችና እምቢተኞች አይሆኑም፤ እነዚያ እግዚአብሔርን በማመን የጸኑ አልነበሩም፤ ለእግዚአብሔር ታማኞች ሆነው አልኖሩም።
የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እነሆ እኔም እንደዚሁ አደርግባችኋለሁ፤ ስለዚህ ይህን ስለማደርግባችሁ ከእኔ ከአምላካችሁ ጋር በፍርድ ለመገናኘት ተዘጋጁ!”
“ ‘የጌታን መንገድ አዘጋጁ፥ ጥርጊያውንም አቅኑ!’ እያለ በበረሓ የሚጮኽ ሰው ድምፅ” ብሎ ነቢዩ ኢሳይያስ የተናገረው ስለ ዮሐንስ ነበር።
ስለዚህ ወዲያውኑ መልእክተኞች ወደ አንተ ላክሁ፤ አንተም በመምጣትህ መልካም አድርገሃል፤ እንግዲህ እግዚአብሔር እንድትናገር ያዘዘህን ሁሉ ለመስማት እኛ ሁላችን በእግዚአብሔር ፊት እዚህ ተሰብስበናል።”
ከእነዚህ ክብር ከሌላቸው ነገሮች ተለይቶ ንጹሕ ሆኖ የሚኖር ሰው ለተከበረ አገልግሎት እንደሚውል ዕቃ ይሆናል፤ ለማንኛውም መልካም አገልግሎት የተዘጋጀ ለጌታው የተቀደሰና ጠቃሚ መገልገያ ይሆናል።
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚያስደንቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችኹ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።
ከዚህ በኋላ ዙፋኖችን አየሁ፤ በዙፋኖቹም ላይ የመፍረድ ሥልጣን የተሰጣቸው ተቀምጠው አየሁ፤ ስለ ኢየሱስ በመመስከራቸውና ስለ እግዚአብሔር ቃል ራሶቻቸው የተቈረጡባቸውን ሰዎች ነፍሶች አየሁ፤ እነርሱ ለአውሬውና ለምስሉ ያልሰገዱ፥ ምልክቱንም በግንባራቸውም ሆነ በእጃቸው ላይ ያላደረጉ ናቸው፤ እነርሱ ከሞት ተነሥተው ከክርስቶስ ጋር ሺህ ዓመት ነገሡ።