ቀድሞ ያልተነገራቸውን ነገር ስለሚያዩና ያልሰሙትን ነገር ስለሚያስተውሉ ብዙ ሕዝቦች ስለ አገልጋዬ ይደነቃሉ፤ ነገሥታትም በእርሱ በመደነቅ የሚናገሩትን ያጣሉ።”
ዘሌዋውያን 7:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መሥዋዕት ሆኖ የቀረበው እንስሳ፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርቡት እንስሶች በሚታረዱበት ስፍራ ይታረድ፤ ደሙም በመሠዊያው ጐን በአራቱም ማእዘን ይረጭ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ የበደሉም መሥዋዕት እዚያው ይታረድ፤ ደሙም በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ይረጭ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚቃጠለውን መሥዋዕት በሚያርዱበት ስፍራ የበደሉን መሥዋዕት ያርዱታል፤ ደሙንም በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጨዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚቃጠለውን መሥዋዕት በሚያርዱበት ስፍራ የበደሉን መሥዋዕት በግ በዚያ ያርዱታል፤ ደሙንም በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚቃጠለውን መሥዋዕት በሚያርዱበት ስፍራ የበደሉን መሥዋዕት ያርዱታል፤ ደሙንም በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጨዋል። |
ቀድሞ ያልተነገራቸውን ነገር ስለሚያዩና ያልሰሙትን ነገር ስለሚያስተውሉ ብዙ ሕዝቦች ስለ አገልጋዬ ይደነቃሉ፤ ነገሥታትም በእርሱ በመደነቅ የሚናገሩትን ያጣሉ።”
በመግቢያው ክፍል በኩል በግራና በቀኝ ትይዩ ሁለት ሁለት ጠረጴዛዎች ነበሩ፤ በእነዚያም ጠረጴዛዎች ላይ ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለኃጢአት መሥዋዕትና ለበደል መሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሶች ይታረድባቸው ነበር።
እርሱንም ከመሠዊያው በስተ ሰሜን በኩል በእግዚአብሔር ፊት ይረደው፤ የአሮን ዘር የሆኑ ካህናትም ደሙን ወስደው በመሠዊያው ጐኖች ሁሉ ላይ ይርጩት።
ይኸውም ከቀንድ ከብቱ መካከል አንዱን ለሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ ቢፈልግ ምንም ነውር የሌለበትን ኰርማ መርጦ ያምጣ፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት የሰመረ መሥዋዕት ይሆንለት ዘንድ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ በር በኩል ያቅርበው።
ያ ሰው ወይፈኑን በእግዚአብሔር ፊት ይረደው፤ ትውልዳቸው ከአሮን ወገን የሆነ ካህናት ደሙን ወደ እግዚአብሔር ያቅርቡት፤ በድንኳኑ በር መግቢያ በኩል በሚገኘው መሠዊያ ጐኖች ሁሉ ላይ ይርጩት።
ጠቦቱንም ለኃጢአት ስርየት መሥዋዕትና ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሶች በሚታረዱበት ቅዱስ ስፍራ ያርደዋል፤ ይህንንም የሚያደርግበት ምክንያት የበደል ዕዳ መሥዋዕት ልክ ለኃጢአት ስርየት እንደሚቀርበው መሥዋዕት የካህኑ ድርሻ ሆኖ ስለሚሰጥ ነው፤ እርሱም እጅግ የተቀደሰ ነው።
መሥዋዕት አቅራቢው ሰው መባ አድርጎ በሚያቀርበው እንስሳ ራስ ላይ እጁን ጭኖ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ ይረደው፤ የአሮን ዘር የሆኑ ካህናትም ደሙን ተቀብለው በመሠዊያው ዙሪያ ይርጩት።
እጁንም በፍየሉ ራስ ላይ ጭኖ፥ ከመሠዊያው በስተ ሰሜን በኩል ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሶች በሚታረዱበት ስፍራ በእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ይረደው፤ ይህም ኃጢአትን የሚያስወግድ መሥዋዕት ይሆናል።
እርሱም በእንስሳይቱ ራስ ላይ እጁን ይጫን፤ ከመሠዊያው በስተሰሜን በኩል ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሶች በሚታረዱበት ስፍራ ይረዳት፤
ቀድሞ መስጠት ይገባው ከነበረው ጋር አንድ አምስተኛ ጨምሮ ያምጣ፤ እርሱንም አምጥቶ ለካህኑ ይስጥ፤ ካህኑም እንስሳውን ስለ ሰውየው ኃጢአት መሥዋዕት አድርጎ ያቅርበው፤ በደል የሠራውም ሰው ኃጢአቱ ይቅር ይባልለታል።
“አንድ ሰው በግ ወይም ፍየል ማቅረብ ካልቻለ ግን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች፥ አንደኛይቱን ስለ ኀጢአት ለሚቀርብ መሥዋዕት፥ ሁለተኛይቱንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ የበደሉን ዕዳ ይከፍል ዘንድ ለእግዚአብሔር ያምጣ።
“ለአሮንና ለልጆቹ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘የኃጢአት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው፤ ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚቀርበው እንስሳ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ በእግዚአብሔር ፊት ይታረድ። ይህም እጅግ የተቀደሰ ነው።
በናዝራዊነትም ለማገልገል ራሱን እንደገና ለእግዚአብሔር የተለየ ያደርጋል፤ ለእግዚአብሔር የተቀደሰው ጠጒሩ ከመርከሱ የተነሣ ከዚያ በፊት በናዝራዊነት የነበረበት ክፍለ ጊዜ አይቈጠርለትም፤ ስለ በደልም ለሚከፈለው ዋጋ አንድ ዓመት የሞላው የበግ ጠቦት ያምጣ።
የበኲር ልጆችን ለመግደል የታዘዘው መልአክ የእስራኤላውያንን የበኲር ልጆች እንዳይገድል በማለት ሙሴ የፋሲካና የደም መርጨትን ሥርዓት ያደረገው በእምነት ነው።
እግዚአብሔር አብ አስቀድሞ በዐቀደው መሠረት ለተመረጣችሁት፥ ለኢየሱስ ክርስቶስ ለመታዘዝና በደሙ ተረጭታችሁ ለመንጻት በመንፈስ ቅዱስ ለተቀደሳችሁት፥ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።