Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘሌዋውያን 4:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 እጁንም በእንስሳይቱ ራስ ላይ ይጫን፤ ከመሠዊያው በስተ ሰሜን ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሶች በሚታረዱበት ስፍራ ይረዳት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 እጁን ለኀጢአት መሥዋዕት በቀረበችው ፍየል ራስ ላይ ይጫን፤ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራም ይረዳት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 እጁንም የኃጢአት መሥዋዕት በሆነችው እንስሳ ራስ ላይ ይጭናል፤ የሚቃጠልም መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ የኃጢአትን መሥዋዕት ያርዳል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 እጁ​ንም በኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ራስ ላይ ይጭ​ናል፤ ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት እን​ስ​ሳ​ትን በሚ​ያ​ር​ዱ​በት ስፍራ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ፍየ​ል​ዋን ያር​ዳ​ታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 እጁንም በኃጢአት መሥዋዕት ራስ ላይ ይጭናል፤ የሚቃጠልም መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ የኃጢአትን መሥዋዕት ያርዳል።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 4:29
10 Referencias Cruzadas  

እጁንም በፍየሉ ራስ ላይ ጭኖ፥ ከመሠዊያው በስተ ሰሜን በኩል ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሶች በሚታረዱበት ስፍራ በእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ይረደው፤ ይህም ኃጢአትን የሚያስወግድ መሥዋዕት ይሆናል።


ኰርማውንም ወደ ድንኳኑ ደጃፍ አምጥቶ እጁን በእንስሳው ራስ ላይ በመጫን በእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ይረደው።


የማኀበሩም አለቆች እጆቻቸውን በኰርማው ራስ ላይ ይጫኑበትና በዚያው በእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ይታረድ።


ሰውየው ለሚቃጠል መሥዋዕት ባቀረበው እንስሳ ራስ ላይ እጆቹን ይጫን፤ እርሱም ለኃጢአቱ ማስተስረያ የሰመረ መሥዋዕት ይሆንለታል።


እርሱም በእንስሳይቱ ራስ ላይ እጁን ይጫን፤ ከመሠዊያው በስተሰሜን በኩል ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሶች በሚታረዱበት ስፍራ ይረዳት፤


ያ ሰው ወይፈኑን በእግዚአብሔር ፊት ይረደው፤ ትውልዳቸው ከአሮን ወገን የሆነ ካህናት ደሙን ወደ እግዚአብሔር ያቅርቡት፤ በድንኳኑ በር መግቢያ በኩል በሚገኘው መሠዊያ ጐኖች ሁሉ ላይ ይርጩት።


እርሱንም ከመሠዊያው በስተ ሰሜን በኩል በእግዚአብሔር ፊት ይረደው፤ የአሮን ዘር የሆኑ ካህናትም ደሙን ወስደው በመሠዊያው ጐኖች ሁሉ ላይ ይርጩት።


ስለ በደልና ስለ ኃጢአት መሥዋዕት የሚከፈለው ገንዘብ ግን ለካህናቱ ጥቅም የሚውል እንጂ ወደ ቤተ መቅደሱ ሣጥን ውስጥ አይገባም ነበር።


ከዚህ በኋላም ፍየሎቹን ወደ ንጉሡና ወደተሰበሰቡት ሰዎች አቀረቡአቸው፤ ንጉሡና ሰዎቹም እጃቸውን ጫኑባቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios