ዘሌዋውያን 6:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወይም የጠፋ ነገር አግኝቶ አላየሁም በማለት በሐሰት ቢምል፥ ሰዎች ከሚፈጽሙአቸው ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ በአንዲቱ ቢበድል፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወይም የጠፋ ነገር አግኝቶ አላየሁም ቢል ወይም በሐሰት ቢምል ወይም ሰዎች የሚያደርጉትን እንዲህ ያለውን ማንኛውንም ኀጢአት ቢሠራ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይም የጠፋውን ነገር ቢያገኝ፥ ያንንም ሸሽጎ በሐሰት ቢምል፥ ሰው ከሚያደርጋቸው ከእነዚህ ሁሉ ነገሮች ኃጢአት በአንዱ ቢሠራ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይም የጠፋውን ነገር ቢያገኝ፥ ስለዚህም ቢዋሽ፥ ሰው ኀጢአትን ለመሥራት ከሚያደርጋቸው ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ በአንዲቱ በሐሰት ቢምል፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይም የጠፋውን ነገር ቢያገኝ፥ ያንንም ሸሽጎ በሐሰት ቢምል፥ ሰው ከሚያደርጋቸው ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ በአንዲቱ ቢበድል፥ |
ብዙ ሀብት ቢኖረኝ “እግዚአብሔር ማን ነው?” ብዬ አንተን እስከ መካድ እደርሳለሁ፤ ድኻ ብሆን ደግሞ እሰርቅ ይሆናል፤ በዚህም ሁኔታ የአንተን የአምላኬን ስም አሰድባለሁ።
ከዚህም የተነሣ ትሰርቃላችሁ፤ ትገድላላችሁ፤ ታመነዝራላችሁ፤ ምላችሁም በሐሰት ትመሰክራላችሁ፤ ለባዓል መሥዋዕት ታቀርባላችሁ፤ ከዚህ በፊት የማታውቁአቸውን አማልክት ታመልካላችሁ።
ሕዝቡ ወደሚገኙበት ወደ ውጪው አደባባይ ከመውጣታቸው በፊት በቤተ መቅደስ ለአገልግሎት የተጠቀሙባቸውን አልባሳት አውልቀው በተቀደሱት ዕቃ ቤቶች ማኖርና ለራሳቸውም ሌላ ልብስ መልበስ አለባቸው፤ ይህንንም የሚያደርጉት ሕዝቡ ያልተፈቀደለትን የእነርሱን የተቀደሰ ልብስ ነክቶ እንዳይጐዳ ነው።
“አሮን ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ከመግባቱ በፊት ሰውነቱን ታጥቦ የክህነት ልብሱን ይልበስ፤ ይኸውም ከበፍታ የተሠራውን ቀሚስና ሱሪ ይልበስ፤ እንዲሁም ከበፍታ የተሠራውን ቀበቶ ይታጠቅ፤ ከበፍታ የተሠራውንም መጠምጠሚያ ራሱ ላይ ያድርግ።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ‘ይህን ርግማን እልካለሁ፤ ወደ እያንዳንዱ ሌባና በስሜ ምሎ በሐሰት ወደሚናገር ሰው ቤት ይገባል፤ በገባበትም ጊዜ በዚያ ቈይቶ ቤታቸውን ሁሉ ያፈራርሰዋል’ ይላል።”
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት መስካሪዎች፥ የቀን ሠራተኞችን ደመወዝ አታለው በሚያስቀሩ አሠሪዎች፥ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች፥ እናትና አባት የሌላቸው ልጆችንና ስደተኞችን በሚጨቊኑና እኔን በማይፈሩ ሰዎች ላይ ፈጣን ፍርዴን አስተላልፋለሁ።