“የመንጻትዋም ወራት በተፈጸመ ጊዜ ስለ ወንድ ልጅም ሆነ ስለ ሴት ልጅ የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብ የአንድ ዓመት የበግ ጠቦትና ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚሆን ርግብ ወይም ዋኖስ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ አምጥታ በዚያ ለሚያገለግለው ካህን ትስጠው።
ዘሌዋውያን 5:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሰው በግ ወይም ፍየል ማቅረብ ካልቻለ ግን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች፥ አንደኛይቱን ስለ ኀጢአት ለሚቀርብ መሥዋዕት፥ ሁለተኛይቱንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ የበደሉን ዕዳ ይከፍል ዘንድ ለእግዚአብሔር ያምጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ሰውየው ስለ ሠራው ኀጢአት በግ ለማቅረብ ዐቅሙ ካልፈቀደ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የዋኖስ ጫጩቶች የመጀመሪያውን ለኀጢአት መሥዋዕት፣ ሁለተኛውን ለሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያቅርብ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እርሱም ጠቦትን ለማቅረብ በቂ ገንዘብ ባይኖረው፥ ስለ ሠራው ኃጢአት ለበደል መሥዋዕት ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች፥ አንደኛውን ለኃጢአት መሥዋዕት ሌላውን ደግሞ ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለጌታ ያመጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ስለ ሠራው ኀጢአት የበግ መግዣ ገንዘብ በእጁ ባይኖረው ግን፥ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች፥ አንዱን ለኀጢአት መሥዋዕት ሁለተኛውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለእግዚአብሔር ያቀርባል። ወደ ካህኑም ያመጣቸዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ሠራው ኃጢአት ለበደል መሥዋዕት ጠቦትን ለማምጣት ገንዘቡ ያልበቃ እንደ ሆነ፥ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች፥ አንዱን ለኃጢአት መሥዋዕት ሁለተኛውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለእግዚአብሔር ያቀርባል። |
“የመንጻትዋም ወራት በተፈጸመ ጊዜ ስለ ወንድ ልጅም ሆነ ስለ ሴት ልጅ የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብ የአንድ ዓመት የበግ ጠቦትና ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚሆን ርግብ ወይም ዋኖስ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ አምጥታ በዚያ ለሚያገለግለው ካህን ትስጠው።
“ሴትዮዋ የበግ ጠቦት ማምጣት ካልቻለች፥ ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች ታምጣ፤ እነርሱም አንዱ ለሚቃጠል መሥዋዕት ሌላውም ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ይቀርባሉ፤ ካህኑም ያስተሰርይላትና ትነጻለች፤ ከዚያም በኋላ የነጻች ትሆናለች።”
አንዱን ለኃጢአት መስዋዕት ሌላውን ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ፥ ከዚህም ጋር የእህል መባ ያቅርብ፤ ካህኑም ለሚነጻው ሰው በእግዚአብሔር ፊት ያስተስርይለት።
ካህኑም አንዱን ኃጢአት የሚሰረይበት መሥዋዕት፥ ሁለተኛውንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባል፤ በዚህም ዐይነት ካህኑ ስለሚፈሰው ርኲሰት በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይላታል፥
“ስእለት ያደረገው ሰው ይህን ተመን ለመክፈል የማይችል ሆኖ ከተገኘ ያ ለስጦታ የቀረበውን ሰው ወደ ካህኑ ያምጣው፤ ካህኑም ያ ሰው የሚችለውን ያኽል ገምቶ ዝቅተኛ ዋጋ ያስከፍለው።
“አንድ ሰው ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች ማቅረብ ባይችል፥ አንድ ኪሎ የላመ ዱቄት ስለ ኃጢአቱ ስርየት የሚቀርብ መሥዋዕት አድርጎ ያምጣ፤ እርሱም ስለ ኃጢአት ስርየት የሚቀርብ መሥዋዕት እንጂ የእህል መባ ስላልሆነ የወይራ ዘይት ወይም ዕጣን አይጨምርበት።
ከዚህ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚሆን አንድ ተባዕት ፍየል፥ ምንም ነውር የሌለባቸውን የአንድ ዓመት ጥጃና የአንድ ዓመት የበግ ጠቦት ለሚቃጠል መሥዋዕት እንዲያመጡ ንገራቸው።
“ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ በላቸው፦ ከወንዶችም ሆኑ ከሴቶች ማናቸውም ሰው ለእግዚአብሔር ታማኝ ሆኖ ባለመገኘት በማንም ሰው ላይ በደል ቢፈጽም፥ ያ ሰው በደለኛ ነው።
ካህኑም አንዱን ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት፥ ሌላውን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ በማቅረብ ናዝራዊው ሬሳ በመንካቱ ስለ ረከሰ ያስተሰርይለታል፤ በዚያኑ ቀን ናዝራዊው ጠጒሩን እንደገና ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ያደርገዋል።
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፤ በዚያም የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሰዎች ሁሉ አስወጣ። የገንዘብ ለዋጮችን ጠረጴዛዎችና የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠ።