ከዚህ በኋላ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሞራ እንደ መረብ ሆኖ ጉበቱን የሚሸፍነውን ሞራ ሁለቱን ኲላሊቶቹንና እነርሱን የሚሸፍነውን ሞራ ወስደህ በመሠዊያው ላይ አቃጥለው።
ዘሌዋውያን 3:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኲላሊቶቹና በእነርሱ ላይ የሚገኘው ስብ፥ እንዲሁም እንደ መረብ ሆኖ ጉበቱን ከሚሸፍነው ስብ ምርጥ የሆነው ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁለቱን ኵላሊቶች፣ በኵላሊቶቹ ላይና በጐድኑ አጠገብ ያለውን ሥብ እንዲሁም የጕበቱን መሸፈኛ፣ ከኵላሊቶቹ ጋራ አንድ ላይ አውጥቶ ያቅርብ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለቱንም ኩላሊቶች፥ በእነርሱም ላይና በጎድኑ አጠገብ ያለውን ስብ፥ በጉበቱም ላይ ያለውን መረብ ከኩላሊቶች ጋር ወስዶ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለቱንም ኵላሊቶች፥ በእነርሱም ላይና በጎድኑ አጠገብ ያለውን ስብ፥ በጉበቱም ላይ ያለውን መረብ ከኵላሊቶቹ ጋር ያመጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለቱንም ኵላሊቶች፥ በእነርሱም ላይና በጎድኑ አጠገብ ያለውን ስብ፥ በጕበቱም ላይ ያለውን መረብ ከኵላሊቶች ጋር ይወስዳል። |
ከዚህ በኋላ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሞራ እንደ መረብ ሆኖ ጉበቱን የሚሸፍነውን ሞራ ሁለቱን ኲላሊቶቹንና እነርሱን የሚሸፍነውን ሞራ ወስደህ በመሠዊያው ላይ አቃጥለው።
“የሚካኑበት ስለ ሆነ የአውራውን በግ ሞራ ላቱን፥ የውስጥ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሞራ፥ እንደ መረብ ሆኖ ጉበቱን ከሚሸፍነው ሞራ የተሻለውን ክፍል፥ ሁለቱን ኲላሊቶቹን፥ እነርሱን የሚሸፍነውን ሞራና በቀኝ በኩል ያለውን የኋላ እግር ቈርጠህ ለያቸው።
ያም ሰው እንስሳውን በየብልቱ ከቈራረጠው በኋላ ካህኑ ብልቶቹን ሁሉ፥ ራሱንና ስቡን ጭምር በመሠዊያ ላይ ተረብርቦ በሚቃጠለው እንጨት ላይ ያኑር፤
ይህ የሚቃጠል መሥዋዕት በመሆኑ የአሮን ልጆች በሚቃጠለው መሥዋዕት መሠዊያ ላይ ያቃጥሉት፤ ይህ ዐይነቱ መሥዋዕት መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነው።
ኲላሊቶቹና በእነርሱ ላይ የሚገኘው ስብ፥ እንዲሁም እንደ መረብ ሆኖ ጉበቱን ከሚሸፍነው ስብ ምርጥ የሆነው ክፍል ተወስዶ በመሠዊያው ላይ መሥዋዕት ሆኖ ይቅረብ፤
ሙሴ በእንስሳው ሆድ ዕቃ ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥ ጒበቱን እንደ መረብ ሆኖ የሚሸፍነው ስብ፥ ኲላሊቶቹንና በእነርሱ ላይ ያለውን ስብ ወስዶ፥ ሁሉንም በመሠዊያው ላይ አቃጠለው።
ስቡን፥ ላቱን፥ ሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ስብ ሁሉ፥ እንደ መረብ ሆኖ ጒበቱን ከሚሸፍነው ስብ ምርጥ የሆነውን ክፍል፥ ኲላሊቶቹን፥ በእነርሱ ላይ ያለውን ስብና በቀኝ በኩል ያለውን ወርች ወሰደ፤
ከዚህም በኋላ ስቡን፥ ኲላሊቶቹን እንደ መረብ ሆኖ ጒበቱን ከሚሸፍነው ስብ ምርጥ የሆነውን ወስዶ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት በመሠዊያው ላይ አቃጠለው፤
አሮንም የወይፈኑንና የበግ አውራውን ስብ ሁሉ ማለትም ላቱን፥ ሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ስብ፥ እንደ መረብ ሆኖ ጒበቱን የሚሸፍነውን ስብ ምርጥ የሆነውን ክፍል፥ ኲላሊቶቹንና በእነርሱ ላይ ያለውን ስብ ወስዶ፥