Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 1:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የእንስሳውንም ሥጋ ብልቶች በየዐይነታቸው ለያይተው ራሱንና ስቡንም ጭምር በመሠዊያው ላይ በተረበረበው እንጨት ላይ ያኑሩት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ካህናቱ የአሮን ልጆች ጭንቅላቱንና ሥቡን ጨምረው ብልቶቹን በመሠዊያው ላይ በሚነድደው ዕንጨት ላይ ይደርድሩት፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የአሮንም ልጆች ካህናቱ ብልቶቹንና ራሱን ስቡንም በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በእንጨቱ ላይ ይረበርቡታል፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የአ​ሮ​ንም ልጆች ካህ​ናቱ የተ​ቈ​ረ​ጡ​ትን ብል​ቶች፥ ራሱ​ንም፥ ስቡ​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በእ​ሳቱ ላይ ባለው በዕ​ን​ጨቱ ላይ ይረ​በ​ር​ቡ​ታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የአሮንም ልጆች ካህናቱ የተቈረጡትን ብልቶች ራሱንም ስቡንም በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በእንጨቱ ላይ ይረበርቡታል፤

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 1:8
9 Referencias Cruzadas  

እንግዲህ ሁለት ኰርማዎችን አምጡና የባዓል ነቢያት አንዱን ወስደው ይረዱት፤ ሥጋውንም ቈራርጠው እንጨት በመረብረብ በዚያ ላይ ያኑሩት፤ ነገር ግን በእሳት አያቀጣጥሉት፤ እኔም ሁለተኛውን ኰርማ ወስጄ እንደዚሁ አደርጋለሁ፤


እንጨቱንም በመሠዊያው ላይ በመረብረብ ኰርማውን በብልት በብልቱ ቈራርጦ በእንጨቱ ላይ ካኖረ በኋላ፥


ለጥቃቅን ዕቃዎች ማስቀመጫነት የሚያገለግል ስፋቱ አንድ ጋት የሆነ ክፈፍ በውስጥ በኩል በግድግዳዎቹ ላይ ዙሪያውን ተሠርቶ ነበር፤ በጠረጴዛዎቹም ላይ የመሥዋዕቱ ሥጋ ይቀመጥ ነበር።


ያም ሰው እንስሳውን በየብልቱ ከቈራረጠው በኋላ ካህኑ ብልቶቹን ሁሉ፥ ራሱንና ስቡን ጭምር በመሠዊያ ላይ ተረብርቦ በሚቃጠለው እንጨት ላይ ያኑር፤


ለአንድነት መሥዋዕት ከሚቀርበው መባ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ሆነው የሚቀርቡት ሆድ ዕቃውን የሚሸፍነው ስብ በሙሉ፥


ኲላሊቶቹና በእነርሱ ላይ የሚገኘው ስብ፥ እንዲሁም እንደ መረብ ሆኖ ጉበቱን ከሚሸፍነው ስብ ምርጥ የሆነው ናቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos