በዚያን ዕለት እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ በማለት ቃል ኪዳን ገባለት፦ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ሁሉ ለዘሮችህ እሰጣለሁ፤
ዘሌዋውያን 26:42 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከያዕቆብ፥ ከይስሐቅና ከአብርሃም ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አስባለሁ፤ ምድሪቱንም ለሕዝቤ ለመስጠት የሰጠሁትን የተስፋ ቃል አድሳለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ ከያዕቆብ ጋራ የገባሁትን ኪዳኔን፣ ከይሥሐቅም ጋራ የገባሁትን ኪዳኔን፣ ደግሞም ከአብርሃም ጋራ የገባሁትን ኪዳኔን ዐስባለሁ፤ ምድሪቱንም ዐስባታለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም ለያዕቆብ የማልሁትን ቃል ኪዳኔን አስታውሳለሁ፤ እንዲሁም ለይስሐቅና ለአብርሃም የማልሁትንም ቃል ኪዳኔን አስታውሳለሁ፤ ምድሪቱንም አስታውሳለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያን ጊዜ እኔ ከያዕቆብ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፤ ደግሞም ከይስሐቅ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳኔን፥ ከአብርሃምም ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፤ ምድሪቱንም አስባለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ለያዕቆብ የማልሁትን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፤ ደግሞ ለይስሐቅና ለአብርሃም የማልሁትን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፤ ምድሪቱንም አስባለሁ። |
በዚያን ዕለት እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ በማለት ቃል ኪዳን ገባለት፦ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ሁሉ ለዘሮችህ እሰጣለሁ፤
በዚያን ሌሊት እግዚአብሔር ተገለጠለትና “እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክ ነኝ፤ እኔ ከአንተ ጋር ስለ ሆንኩ አትፍራ፤ ለአገልጋዬ ለአብርሃም በገባሁት ቃል ኪዳን መሠረት እባርክሃለሁ፤ ዘርህንም አበዛዋለሁ” አለው።
እግዚአብሔርም በአጠገቡ ቆሞ እንዲህ አለው፤ “እኔ የአባትህ የአብርሃምና የይስሐቅ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ፤ ለአንተና ለትውልድህ እንዲሆን ይህን የተኛህበትን ምድር እሰጥሃለሁ፤
አይዞህ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፤ በምትሄድበትም ስፍራ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ወደዚህም ምድር በደኅና እመልስሃለሁ፤ የገባሁልህን ቃል ኪዳን ሁሉ እፈጽምልሃለሁ፤ ከቶም አልተውህም።”
ደግሞም እግዚአብሔር ያዕቆብን እንዲህ አለው፦ “ሁሉን ቻይ አምላክ እኔ ነኝ፤ ብዙ ልጆች ይኑርህ፤ ዘርህም ይብዛ፤ የብዙ ሕዝብ አባት ሁን፤ ነገሥታትም ከአንተ ይወለዱ።
‘ከእንግዲህ ወዲህ የጥፋት ውሃ፤ ሕያዋን ፍጥረቶችን ሁሉ ከቶ አያጠፋም’ ብዬ ከእናንተና ከሌሎች ሕያዋን ፍጥረቶች ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ።
ቀስት በደመናዎች ላይ በሚታይበት ጊዜ ተመልክቼ በእኔና በምድር ላይ ባሉት ሕይወት ባላቸው ፍጥረቶች መካከል ያለውን ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ።”
እንደዚህ ባለ ጊዜ ችላ ብለሽ ዝም ብትዪ፥ ለአይሁድ ከሌላ ቦታ ርዳታ መምጣቱ አይቀርም፤ እነርሱም በእርግጥ ይድናሉ፤ አንቺ ግን ትሞቻለሽ፤ የአባትሽም የቤተሰብ ሐረግ ተቋርጦ ይቀራል፤ ነገር ግን አንቺ ንግሥት የሆንሽው በዚህ መከራ ጊዜ እኛን ለመታደግ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?”
እነሆ፥ አሁንም ግብጻውያን ባርያዎች አድርገው የሚያስጨንቁአቸውን የእስራኤላውያንን መራራ ጩኸት ሰምቼአለሁ፤ የገባሁትንም ቃል ኪዳን አስታውሼአለሁ።
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ለእስራኤል እንደገና ምሕረትን ያደርጋል፤ የራሱ ወገኖችም አድርጎ ይመርጣቸዋል፤ እንደገናም በአገራቸው እንዲኖሩ ይፈቅድላቸዋል፤ መጻተኞችም እንኳ መጥተው ከእነርሱ ጋር ተስማምተው አብረው ይኖራሉ።
እርሱም ይቅር ባይ አምላክ ስለ ሆነ አይተዋችሁም፤ ፈጽሞ እንድትደመሰሱም አያደርግም፤ ከቀድሞ አባቶቻችሁ ጋር በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳን ከቶ አይረሳም።
የእግዚአብሔር መልአክ ከጌልጌላ ወደ ቦኪም ሄዶ እስራኤላውያንን እንዲህ አላቸው፤ “እኔ ከግብጽ ምድር አውጥቼ ለቀድሞ አባቶቻችሁ ልሰጣቸው ቃል ወደገባሁላቸው ምድር አመጣኋችሁ፤ እንዲህም አልኩ፦ ‘ከእናንተ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ከቶ አላፈርስም፤