ዘሌዋውያን 26:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “ትሰግዱላቸው ዘንድ ማናቸውንም ዐይነት ጣዖቶች አትሥሩ፤ እንዲሁም ምስል ወይም ሐውልት ወይም የተቀረጸ የድንጋይ ዐምድ አታቁሙ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ትሰግዱላቸው ዘንድ ጣዖታትን አታብጁ፤ ምስል ወይም የማምለኪያ ዐምድ አታቁሙ፤ በምድራችሁም ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝና ለራሳችሁ ይሆኑ ዘንድ ጣዖታትን አትሥሩ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ለእርሱም ለመስገድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለእናንተ በእጅ የተሠራ ጣዖት አታድርጉ፤ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና ለእናንተ ጣዖት አታድርጉ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ። |
የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ሁሉ በመጣስ የሚሰግዱላቸውን ከወርቅ የተሠሩ ሁለት ጥጆችን አቆሙ፤ እንዲሁም አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስል ሠሩ፤ ለከዋክብት ሰገዱ፤ ባዓል ተብሎ ለሚጠራውም ባዕድ አምላክ አገልጋዮች ሆኑ።
ሕዝቡ ወደ ፊት እየገፋ በመጣ ጊዜ ከፊታቸው ነቃቅሎ ያጠፋላቸውን የአሕዛብን መጥፎ ልማድ ተከተሉ፤ እንዲሁም የእስራኤል ነገሥታት ያሠራጩትን መጥፎ ልማድ ተቀባዮች ሆኑ።
ለእነርሱ አማልክት በመንበርከክ አትስገድ፤ አታምልካቸው፤ ሃይማኖታዊ ልማዶቻቸውንም አትከተል፤ አማልክታቸውን አጥፋ፤ ለእነርሱ ቅዱሳን የሆኑትን የድንጋይ ዐምዶቻቸውንም አፈራርስ፤
እስራኤላውያን የእኔ አገልጋዮች ስለ ሆኑ እስራኤላዊ የሆነ ማንም ሰው ለዘለቄታው ባርያ ሆኖ መገዛት የለበትም፤ እስራኤላውያን ከግብጽ ምድር ያወጣኋቸው ናቸው፤ እኔም እግዚአብሔር አምላካቸው ነኝ።”
በምድሪቱ ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ሁሉ ከፊታችሁ አስወጡአቸው፤ ከድንጋይና ከብረት የተሠሩትን ጣዖቶቻቸውንም ሰባበሩ፤ በኮረብታ ላይ ያሉ መስገጃዎቻቸውንም አፈራርሱ።
እንግዲህ እኛ የእርሱ ልጆች ከሆንን ‘እግዚአብሔር በሰው ጥበብና አሳብ ከወርቅ ወይም ከብር ወይም ከድንጋይ የተሠራውን ቅርጽ ይመስላል’ ብለን ማሰብ አይገባንም።
“ ‘እንጨት ጠርቦ፥ ድንጋይ አለዝቦ፥ ብረት አቅልጦ ጣዖት በመሥራት በስውር የሚሰግድለት ማንኛውም ሰው የተረገመ ይሁን! እግዚአብሔር የጣዖት አምልኮን ይጠላል።’ “ሕዝቡም ሁሉ ሲመልሱ ‘አሜን!’ ይበሉ።
እንደ ውሻ የሚልከፈከፉ፥ አስማተኞች፥ አመንዝሮች፥ ነፍሰ ገዳዮች፥ ጣዖት አምላኪዎች፥ ውሸትን የሚወዱና በሐሰት መንገድ የሚሄዱ ሁሉ ከከተማይቱ ውጪ ይሆናሉ።
የዳን ሰዎችም ያመልኩት ዘንድ ያን ጣዖት በዚያ አኖሩ፤ ከሙሴ ልጅ ከጌርሾም የተወለደው ዮናታንም ለዳን ነገድ ካህን ሆኖ ማገልገል ጀመረ። የእርሱም ዘሮች ሕዝቡ ተማርከው እስከ ተሰደዱበት ጊዜ ድረስ ማገልገላቸውን ቀጠሉ።