“እንስሳ በምትሠዉልኝ ጊዜ እርሾ የነካው እንጀራ መባ አድርጋችሁ አታቅርቡ፤ በእነዚህ በዓላት የሚሠዉት እንስሶች ስብ ለሚቀጥለው ቀን አይትረፍ።
ዘሌዋውያን 2:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ ለእግዚአብሔር ከሚቀርበው መባ ጋር የሚገኘውን እርሾም ሆነ ማር. በእሳት ማቃጠል ስለሌለብህ፥ ለእግዚአብሔር የምታቀርበው የእህል መባ ሁሉ ምንም ዐይነት እርሾ ያልነካው ይሁን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ለእግዚአብሔር በእሳት በምታቀርቡት ቍርባን ውስጥ እርሾ ወይም ማር ጨምራችሁ ማቃጠል ስለማይገባችሁ፣ በምታቀርቡት በማንኛውም የእህል ቍርባን እርሾ አይኑርበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ማንኛውም እርሾ ያለበትን ነገርና ማርን፥ ለጌታ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጋችሁ አታቃጥሉትምና ለጌታ የምታቀርቡት የእህል ቁርባን ሁሉ በእርሾ የተዘጋጀ አይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለእግዚአብሔር የምታቀርቡት የእህል ቍርባን ሁሉ እርሾ አይሁንበት፤ እርሾ ያለበት ነገር፥ ማርም ለእግዚአብሔር ቍርባን ይሆን ዘንድ አታቀርቡምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሾ ያለበት ነገር ማርም ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን ይሆን ዘንድ አታቀርቡምና ለእግዚአብሔር የምታቀርቡት የእህል ቍርባን ሁሉ እርሾ አይሁንበት። |
“እንስሳ በምትሠዉልኝ ጊዜ እርሾ የነካው እንጀራ መባ አድርጋችሁ አታቅርቡ፤ በእነዚህ በዓላት የሚሠዉት እንስሶች ስብ ለሚቀጥለው ቀን አይትረፍ።
ከእነርሱም በመቀበል ለእኔ የምግብ መባ አድርገህ ታቀርበው ዘንድ በሚቃጠለው መሥዋዕት ጫፍ ላይ አኑረህ በመሠዊያው ላይ አቃጥለው፤ ይህም መባ መዓዛው እኔን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል።
“ለእኔ የእንስሶች መሥዋዕት በምትሠዉበት ጊዜ ደሙን እርሾ ካለበት ኅብስት ጋር አታቅርቡልኝ ለፋሲካ በዓል ከታረደው እንስሳ ምንም ሥጋ እስከ ማግስቱ ጠዋት ድረስ አታቈዩ።
ሰውየውም የእንስሳውን የሆድ ዕቃና የኋላ እግሮቹን በውሃ ይጠብ፤ ካህኑም ያን ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጎ በማቅረብ በመሠዊያው ላይ በሙሉ ያቃጥለው፤ ይህም ዐይነት በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል።
ካህኑም ከከፈይ የተሠራ ቀሚሱንና ሱሪውን ለብሶ የሚቃጠለውን መሥዋዕት እሳት ከበላው በኋላ የቀረውን ዐመድ ሰብስቦ በመሠዊያው ጐን ያፍስሰው።
በዚያን ጊዜ በብዙ ሺህ የሚቈጠሩ ሰዎች ተሰበሰቡ፤ ከብዛታቸውም የተነሣ እርስ በርሳቸው እየተጋፉ ይረጋገጡ ነበር፤ ኢየሱስም በቅድሚያ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ይል ጀመር፤ “ከፈሪሳውያን እርሾ ማለትም ከግብዝነታቸው ተጠንቀቁ ማለት ነው።
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በመብልና በመጠጥ ብዛት በስካርም በመባከንና ስለ ዓለማዊ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝል ተጠንቀቁ! አለበለዚያ ያ ቀን እንደ ወጥመድ በድንገት ይይዛችኋል።
በእነዚያም አገሮች ሁሉ አማኞች በእምነታቸው እንዲጸኑ በማበረታታትና በመምከር “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት ብዙ መከራ መቀበል አለብን” እያሉ አስተማሩአቸው።