ዘሌዋውያን 19:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእናንተ እያንዳንዱ እናትና አባቱን ያክብር፤ እኔ ባዘዝኩት መሠረት ሰንበትን ይጠብቅ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ከእናንተ እያንዳንዱ እናቱንና አባቱን ያክብር፤ ሰንበታቴን ጠብቁ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእናንተ እያንዳንዱ ሰው እናቱንና አባቱን ያክብር፥ ሰንበታቴንም ጠብቁ፥ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእናንተ እያንዳንዱ አባቱንና እናቱን ይፍራ፤ ሰንበታቴንም ጠብቁ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእናንተ ሰው ሁሉ እናቱንና አባቱን ይፍራ፥ ሰንበታቴንም ጠብቁ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። |
እኔ አንድ የዕረፍት ቀን ሰጥቻችኋለሁ፤ ዘወትር በስድስተኛው ቀን ለሁለት ቀን የሚበቃ ምግብ ስለምሰጣችሁ በሰባተኛው ቀን እያንዳንዱ ሰው ከቤት ሳይወጣ፥ ባለበት ስፍራ ሁሉ ዕረፍት አድርጎ ይዋል።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በተቀደሰው ቀኔ የራሳችሁን ጥቅም በማሳደድ ሰንበቴን ከመሻር ብትቈጠቡ፥ ሰንበቴን አስደሳች፥ የተከበረውንም የእኔን የእግዚአብሔርን ቀን የተከበረ ቀን ብትሉት፥ የግል ፍላጎታችሁንና የግል ጉዳያችሁን ተግባራዊ ለማድረግ በራሳችሁ አካሄድ መመራትን ትታችሁ ሰንበቴን ብታከብሩ፥
እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ፤ እኔ ቅዱስ ስለ ሆንኩ እናንተም ራሳችሁን የተቀደሰ አድርጉ፤ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱትን ነፍሳት በመብላት ራሳችሁን አታርክሱ።
በአምስተኛው ዓመት ግን ፍሬውን ትበላላችሁ፤ ይህን ብታደርጉ ዛፎቻችሁ በየጊዜው የሚሰጡአችሁ ፍሬ ይበልጥ እየበዛ ይሄዳል፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።
ለእስራኤላዊ ወገናችሁ በምታደርጉት ዐይነት መልካም ነገር አድርጉላቸው፤ እንደ ራሳችሁም አድርጋችሁ ውደዱአቸው፤ እናንተም ከዚህ በፊት በግብጽ ምድር ባዕዳን እንደ ነበራችሁ አስታውሱ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።
ሥራ የምትሠሩባቸው ስድስት ቀኖች አሉላችሁ፤ ሰባተኛው ዕለተ ሰንበት ግን የዕረፍት ቀን ነው፤ በዚያን ቀን ለአምልኮ ተሰብሰቡ እንጂ ምንም ሥራ አትሥሩበት፤ በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ሰንበት ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ዕለት ነው፤
የሠራዊት አምላክ ካህናቱን እንዲህ ይላቸዋል፦ “ልጅ አባቱን፥ አገልጋይም አሳዳሪ ጌታውን ያከብራል፤ እነሆ፥ እኔ አባታችሁ ከሆንኩ ለምን አታከብሩኝም? ጌታችሁም ከሆንኩ ለምን ክብር አትሰጡኝም? እናንተ የእኔን ስም ንቃችኋል፤ ነገር ግን ‘ስምህን የናቅነው እንዴት ነው?’ ብላችሁ ትጠይቃላችሁ።
“ ‘እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ባዘዝኩህ መሠረት አባትህንና እናትህን አክብር፤ ይህን ብታደርግ ሁሉ ነገር ይሳካልሃል፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ በምሰጥህ ምድር የረዥም ዘመን ዕድሜ ይኖርሃል።
ከዚህም በቀር እኛ ሁላችን የሚቀጡን የሥጋ አባቶች ነበሩን፤ እናከብራቸውም ነበር፤ ታዲያ፥ በሕይወት ለመኖር ለመንፈሳዊ አባታችን በይበልጥ መታዘዝ እንዴት አይገባንም!