ስለዚህም ቅጣቱ በኢዮአብና በቤተሰቡ ላይ ይውረድ! በዘመናት ሁሉ ከቤተሰቡ የአባለ ዘር ወይም የሥጋ ደዌ ያለበት ሰው አይጥፋ! እንዲሁም አካለ ስንኩል የሆነ ሰው፥ በጦር ሜዳ የሚሞት ወይም የሚበላው አጥቶ የሚራብ ሰው አይታጣ!”
ዘሌዋውያን 13:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ማንም ሰው በሰውነቱ ላይ እባጭ ወይም ሽፍታ ወይም ቋቊቻ ቢታይና በገላው ላይ የሥጋ ደዌ ቢመስል፥ ወደ ካህኑ ወደ አሮን ወይም ካህናት ከሆኑት ከልጆቹ ወደ አንዱ ያምጡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ማንኛውም ሰው በሰውነቱ ቈዳ ላይ ዕብጠት ወይም ችፍታ ወይም ቋቍቻ ቢወጣበትና ይህም ወደ ተላላፊ የቈዳ በሽታ የሚለወጥበት ከሆነ፣ ወደ ካህኑ አሮን ወይም ካህናት ከሆኑት ልጆቹ ወደ አንዱ ያምጡት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማናቸውም ሰው በሰውነቱ ቆዳ ላይ እባጭ ወይም ብጉር ወይም ቋቁቻ ቢታይ፥ በሰውነቱ ቆዳ እንደ ለምጽ ደዌ ቢሆን፥ ወደ ካህኑ ወደ አሮን ወይም ካህናት ከሆኑት ከልጆቹ ወደ አንዱ ያምጡት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሰው በሥጋው ቆዳ ላይ እባጭ ብትወጣበት፥ ብትነጣም፥ በሥጋውም ቆዳ እንደ ለምጽ ደዌ ብትመስል፥ ወደ ካህኑ ወደ አሮን ወይም ከካህናቱ ልጆች ወደ አንዱ ያምጡት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማናቸውም ሰው በሥጋው ቁርበት ላይ እባጭ ወይም ብጉር ወይም ቍቁቻ ቢታይ፥ በሥጋው ቁርበት እንደ ለምጽ ደዌ ቢመስል፥ ወደ ካህኑ ወደ አሮን ወይም ከካህናቱ ልጆቹ ወደ አንዱ ያምጡት። |
ስለዚህም ቅጣቱ በኢዮአብና በቤተሰቡ ላይ ይውረድ! በዘመናት ሁሉ ከቤተሰቡ የአባለ ዘር ወይም የሥጋ ደዌ ያለበት ሰው አይጥፋ! እንዲሁም አካለ ስንኩል የሆነ ሰው፥ በጦር ሜዳ የሚሞት ወይም የሚበላው አጥቶ የሚራብ ሰው አይታጣ!”
እግዚአብሔር በንዕማን አማካይነት ለሶርያ ሠራዊት ድልን ስለ አጐናጸፈ፥ የሶርያ ጦር አዛዥ የነበረው ንዕማን በሶርያ ንጉሥ ዘንድ እጅግ የተከበረና የተወደደ ባለሟል ነበር፤ ታዲያ ንዕማን ጀግና ወታደር ሆኖ ሳለ፥ በቈዳ በሽታ ይሠቃይ ነበር።
ከዚህም የተነሣ እነሆ፥ የንዕማን የቆዳ በሽታ ወደ አንተ ይተላለፋል፤ አንተና ዘሮችህ ለዘለዓለም ከዚያ በሽታ አትነጹም!” አለው። ግያዝም ወጥቶ ሲሄድ፥ ያ የቆዳ በሽታ ስለ ተጋባበት ገላው እንደ በረዶ ነጭ ሆነ።
ከዚህም የተነሣ ከእግር ጥፍር እስከ ራስ ጠጒር ድረስ ጤናማ የሆነ የአካል ክፍል የላችሁም፤ ቊስልና እባጭ መግልም የሞላበት ሆኖአል፤ ይህም ቊስላችሁ አልፈረጠም፤ አልታሰረም፤ ወይም በዘይት አለሰለሰም።
ካህኑም ቊስሉን ይመርምር፤ በዚያም ቊስል ላይ ያለው ጠጒር ወደ ነጭነት ቢለወጥ፥ ቊስሉም በዙሪያው ካለው ቆዳ ይልቅ ጐድጒዶ ቢገኝ፥ እርሱ የሥጋ ደዌ በሽታ ነው፤ ካህኑም ያ ሰው ርኩስ መሆኑን ያስታውቅ።
ደመናው ከድንኳኑ ላይ በተነሣ፤ ጊዜ ማርያም ለምጻም ሆነች፤ ለምጹም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ፤ አሮን ወደ ማርያም በተመለከተ ጊዜ ለምጻም ሆና አያት።
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ፥ ከለምጹ የዳነውን ሰው እንዲህ አለው፤ “ይህን ነገር ለማንም አትናገር፤ ነገር ግን ሄደህ መዳንህን ለካህን አሳይ፤ ምስክር ይሆንባቸው ዘንድ፥ ስለ መዳንህ ሙሴ ያዘዘውን መባ ለእግዚአብሔር አቅርብ” አለው።
“ይህን ነገር ለማንም እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ለሕዝቡም ምስክር እንዲሆን ስለ መዳንህ ሙሴ ያዘዘውን መሥዋዕት አቅርብ፤” ብሎ አዘዘው።
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ ሲል አዘዘው፤ “ይህን ነገር ለማንም አትናገር፤ ነገር ግን በቀጥታ ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ለሕዝብ ምስክር እንዲሆን ስለ መንጻትህ ሙሴ ያዘዘውን መሥዋዕት አቅርብ።”