Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 28:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 እግዚአብሔር ልትድን በማትችልበት በግብጻውያን የእባጭ በሽታ፥ በኀይለኛ የጨጓራ በሽታ፥ በቊስልና በሚያሳክክ በሽታ ይመታሃል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 እግዚአብሔር በማትድንበት በግብጽ ብጉንጅ፣ በዕባጭ፣ በሚመግል ቍስልና በዕከክ ያሠቃይሃል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 በማትድንበት በግብጽ ብጉንጅ፥ በእባጭ፥ በሚመግል ቁስልና በዕከክ ጌታ ያሠቃይሃል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈውስ በሌ​ለው በግ​ብፅ ቍስል፥ በእ​ባ​ጭም፥ በቋ​ቁ​ቻም፥ በች​ፌም ይመ​ታ​ሃል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 እግዚአብሔር ፈውስ በሌለው በግብፅ ቁስል በእባጭም በቍቁቻም በችፌም ይመታሃል።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 28:27
16 Referencias Cruzadas  

ጠላቶቹ ተሸንፈው ወደ ኋላ እንዲሸሹና ዘለዓለማዊ ኀፍረት እንዲከናነቡ አደረገ።


እንዲህም አላቸው፤ “በጥሞና ትእዛዞቼን ብታዳምጡና በፊቴ መልካም የሆነውን ነገር በታዛዥነት ብታደርጉ፥ ኅጎቼንም ሁሉ ብትጠበቁ፥ በግብጻውያን ላይ ካመጣሁባቸው በሽታዎች በአንዱ እንኳ አልቀጣችሁም፤ ፈዋሻችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”


እነርሱም ጥቂት ዐመድ ከምድጃ ወስደው በንጉሡ ፊት ቆሙ፤ ሙሴም ወደ አየር በበተነው ጊዜ ሕዝቡና እንስሶቹ በብርቱ ቊስል ተመቱ።


እንደማንኛውም ግብጻዊ እነርሱም ቈስለው ስለ ነበረ በዚያን ጊዜ አስማተኞቹ በሙሴ ፊት መቅረብ አልቻሉም፤


እርሱም እንደ ደቃቅ ትቢያ ሆኖ በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ በሚሠራጭበት ጊዜ በሕዝብና በእንስሶቹ ላይ አሠቃቂ የሆነ ብርቱ ቊስል ያመጣል።”


እኔ በእነርሱ ራስ ላይ የቡሃና የቈረቈር በሽታ አመጣለሁ፤ የውስጥ ገላቸውም ይጋለጣል።”


በጀርባው ላይ ጉብር ያለበት ወይም ድንክ፥ የዐይን ሕመም ወይም ልዩ ልዩ ዐይነት የቆዳ በሽታ ያለበት፥ ወይም ጃንደረባ የምግብ ቊርባን ለእኔ ለእግዚአብሔር ሊያቀርብ አይገባውም።


“በግብጽ ምድር የላክሁትን ዐይነት መቅሠፍት ላክሁባችሁ፤ ጐልማሶቻችሁ በሰይፍ እንዲሞቱ፥ ፈረሶቻችሁም እንዲማረኩ አደረግሁ፤ በሰፈራችሁ በሞቱ ሰዎች የበድን ግማት አፍንጫችሁን ሞላሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም።


እግዚአብሔር አእምሮ በሚያሳጣ እብደትና ዕውርነት ይመታሃል።


እግዚአብሔር ቅልጥምህንና ጭንህን በማይፈወስ ቊስል እንዲሸፈን ያደርጋል፤ ብርቱ ቊስልና እባጭ ከራስ ጠጒርህ እስከ እግር ጥፍርህ ይሸፍንሃል።


እግዚአብሔር ከበሽታ ሁሉ ይጠብቅሃል፤ በግብጽ አገር በነበርክ ጊዜ ካየኸው አሠቃቂ በሽታ ሁሉ ማንኛውንም በአንተ ላይ አያመጣም፤ ነገር ግን እነዚህን በሽታዎች በሚጠሉህ ላይ ያመጣባቸዋል።


ከሞት የተረፉትም የእባጩ በሽታ በርትቶባቸው ስለ ነበር ሕዝቡ ርዳታ ለማግኘት ወደ አማልክታቸው በማልቀስ ጮኹ።


እግዚአብሔርም የአሽዶድን ሕዝብ በብርቱ አስጨነቃቸው፤ እነርሱንና በዙሪያቸው ያሉትን ሕዝብ ሁሉ በእባጭ መቅሠፍት ቀጣቸው።


ነገር ግን የቃል ኪዳኑ ታቦት እዚያ ከደረሰ በኋላ እግዚአብሔር ያቺንም ከተማ ጭምር ቀጣ፤ ሕዝብዋንም በብርቱ አስጨነቀ። ሕፃኑንም ሽማግሌውንም ሳይለይ ሕዝቡን ሁሉ በአንድነት በእብጠት በሽታ ቀጣቸው፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos