ሰቈቃወ 5:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ርስታችን ለባዕዳን ተሰጠ፤ ቤታችን ሁሉ የባዕዳን መኖሪያ ሆኖአል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ርስታችን ለመጻተኞች፣ ቤቶቻችን ለባዕዳን ዐልፈው ተሰጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ርስታችን ለእንግዶች፥ ቤቶቻችን ለሌሎች ሆኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ርስታችን ለሌላ፥ ቤቶቻችንም ለእንግዶች ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ርስታችን ለእንግዶች፥ ቤቶቻችን ለሌሎች ሆኑ። |
እነሆ አገራችሁ ምድረ በዳ ሆናለች፤ ከተሞቻችሁም በእሳት ጋይተዋል፤ የእርሻችሁም ቦታ ዐይናችሁ እያየ የውጪ ጠላት ይወስደዋል፤ ሁሉንም ነገር አጥፍቶ ምድራችሁን ውድማ ያደርጋታል።
ቊጣዬ እንደ እሳት እንዲቀጣጠል ስላደረጋችሁ እርሱም ለዘለዓለም ስለሚነድ የሰጠኋችሁን ርስት ሁሉ እንድታጡና በማታውቁት አገር ጠላቶቻችሁን እንድታገለግሉ አደርጋለሁ።”
በሕዝቦች መካከል እጅግ የከፉትን ወደዚህ አምጥቼ ቤቶቻችሁን እንዲወርሱ አደርጋለሁ፤ የኀያላንን ትዕቢት አጠፋለሁ፤ የተቀደሱ ቦታዎቻችሁንም ያረክሳሉ።
እነርሱ ነፋስን ዘርቶ ዐውሎ ነፋስን እንደሚያጭድ ይሆናሉ፤ ዛላ የሌለው የእህል አገዳ ምግብ ሊሆን አይችልም፤ ፍሬ ቢኖረውም እንኳ የሚበሉት ባዕዳን በሆኑ ነበር።
ሀብታቸው ይዘረፋል፤ ቤቶቻቸውም ይፈርሳሉ፤ በዚያን ጊዜ ቤት ይሠራሉ፤ ነገር ግን አይኖሩበትም፤ ወይንም ይተክላሉ፤ ነገር ግን የወይኑን ጠጅ አይጠጡም።”