ይሁን እንጂ እነርሱ ለዘለዓለም ፈጽሞ እንዲደመሰሱ ደግሞ የእግዚአብሔር ፈቃድ አልነበረም፤ ስለዚህም በዳግማዊ ኢዮርብዓም አማካይነት አዳናቸው።
ሰቈቃወ 3:66 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! በቊጣህ አሳዳቸው፤ ከሰማያትም በታች ደምስሳቸው!” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእግዚአብሔር ሰማያት በታች፣ በቍጣህ አሳድዳቸው፤ አጥፋቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ በቁጣ ታሳድዳቸዋለህ ከሰማይም በታች ታጠፋቸዋለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ እንደ ልባቸው ክፋት በቍጣህ ታሳድዳቸዋለህ፤ ከሰማይም በታች ታጠፋቸዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤቱ፥ በቍጣ ታሳድዳቸዋለህ ከሰማይም በታች ታጠፋቸዋለህ። |
ይሁን እንጂ እነርሱ ለዘለዓለም ፈጽሞ እንዲደመሰሱ ደግሞ የእግዚአብሔር ፈቃድ አልነበረም፤ ስለዚህም በዳግማዊ ኢዮርብዓም አማካይነት አዳናቸው።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ ማሳረፊያ ናት፤ ታዲያ ለእኔ ምን ዐይነት ቤት ትሠሩልኛላችሁ? የማርፍበትስ ቦታ ምን ዐይነት ነው?
እኔም እንዲህ አልኩ፦ “እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እባክህ አስታውሰኝ፤ እርዳኝም፤ አሳዳጆቼን ተበቀልልኝ፤ ከትዕግሥትህ ብዛት የተነሣ እንድጠፋ አታድርገኝ፤ ይህም ስድብ የደረሰብኝ በአንተ ምክንያት ነው።
ስለዚህም እግዚአብሔር አምላክህ ምድሪቱን አውርሶህ በዙሪያህ ከሚኖሩ ጠላቶችህ ሁሉ በሚያሳርፍህ ጊዜ በምድር ላይ ማንም የሚያስታውሳቸው እስኪጠፋ ድረስ ዐማሌቃውያንን ሁሉ ደምስስ! ይህን ከቶ አትርሳ!
እግዚአብሔር ለእንደዚህ ያለው ሰው ይቅርታ አያደርግም፤ ይልቁንም የእግዚአብሔር ቊጣና ቅናት በእርሱ ላይ እንደ እሳት ይነዳል፤ እግዚአብሔርም እንደዚህ ያለውን ሰው ፈጽሞ እስኪደመስሰው ድረስ በዚህ መጽሐፍ የተጻፉት መቅሠፍቶች ሁሉ ይወርዱበታል።
ንጉሦቻቸውን በእጅህ ይጥልልሃል፤ እነርሱንም ታጠፋና ስማቸው የተረሳ እንዲሆን ታደርጋለህ፤ ማንም ተቋቊሞ ሊገታህ አይችልም፤ ሁሉንም ታወድማለህ።