Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 8:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 አንተ የፈጠርከውን ሰማይ በማይበት ጊዜ፥ በየስፍራቸው አጽንተህ ያኖርካቸውን ጨረቃንና ኮከቦችን በምመለከትበት ጊዜ፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የጣቶችህን ሥራ፣ ሰማያትህን ስመለከት፣ በስፍራቸው ያኖርሃቸውን፣ ጨረቃንና ከዋክብትን ሳይ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በጠላቶችህ ምክንያት ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ፥ ጠላትንና ቂመኛን ለማጥፋት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የጣ​ቶ​ች​ህን ሥራ ሰማ​ዮ​ችን፥ አንተ የሠ​ራ​ሃ​ቸ​ውን፥ ጨረ​ቃ​ንና ከዋ​ክ​ብ​ትን እና​ያ​ለ​ንና።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 8:3
18 Referencias Cruzadas  

በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ።


እግዚአብሔር ሰማያትን በቃሉ፥ በሰማይ የሚገኙትን ፍጥረቶች በትእዛዙ ፈጠረ።


እግዚአብሔር ብዙ አስደናቂ ነገሮችን አድርጎአል፤ በእርሱ አስደናቂ ሥራዎች የሚደሰት ሁሉ ያስባቸዋል።


ጨረቃን የወቅቶች ምልክት እንድትሆን፥ ፀሐይ የሚጠልቅበትን ጊዜ እንዲያውቅ አድርገሃል።


ሰማይና ምድር የአንተ ናቸው፤ ዓለምንና በውስጡ ያሉትን ሁሉ የፈጠርክ አንተ ነህ።


ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ለሰዎች የማይታየው የእግዚአብሔር ባሕርይ፥ ይኸውም ዘለዓለማዊው ኀይሉና አምላክነቱ እርሱ በፈጠራቸው ነገሮች አማካይነት ግልጥ ሆኖ ስለ ታየ ሰዎች ለሚያጠፉት ጥፋት ምክንያት የላቸውም።


እንግዲህ እኔ አጋንንትን በእግዚአብሔር ኀይል የማስወጣ ከሆነ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ መምጣትዋን ዕወቁ።


አስማተኞቹም “ይህ የእግዚአብሔር ሥራ ነው!” ብለው ለንጉሡ ነገሩት፤ ንጉሡ ግን ልቡን አደነደነ፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገረውም ሙሴንና አሮንን መስማት አልፈለገም።


“እግዚአብሔር ከፍ ባለው ሰማይ የሚኖር አይደለምን? ከዋክብት ምንም እንኳ ከፍ ባለ ስፍራ ቢሆኑ፥ እርሱ ከበላያቸው ሆኖ ይመለከታቸዋል።


በሰማይ ላይ የምታዩአቸውን ፀሐይንና ጨረቃን ወይም ከዋክብትን ወይም የሰማይን ሠራዊት ሁሉ በማምለክና ለእነርሱ በመስገድ እንዳትፈተኑ ተጠንቀቁ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ እነዚህን ሁሉ ሌሎች ሕዝቦች ብቻ ያመልኩአቸው ዘንድ አሳልፎ ሰጥቶአቸዋል።


እግዚአብሔር ሙሴን በሲና ተራራ ላይ ማነጋገሩን ከፈጸመ በኋላ በእግዚአብሔር ጣት በድንጋይ ላይ የተጻፈባቸውን ሁለቱን የቃል ኪዳን ጽላቶች ሰጠው።


ፀሐይና ጨረቃ አመስግኑት። የምትበሩ ከዋክብት ሁሉ አመስግኑት፤


ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፤ የሰማይ ጠፈርም፥ የእጁን ሥራ ያውጃል።


እነሆ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጨረቃ እንኳ ደማቅ አይደለችም፤ ከዋክብትም በእርሱ ፊት ንጹሖች አይደሉም።


የሠራዊቱ ብዛት ሊቈጠር ይቻላልን? የእርሱ ብርሃንስ የማያበራለት ማነው?


ሰዎች ሁልጊዜ በሚሠራው ሥራ በመዝሙር እንደሚያመሰግኑት። አንተም የእርሱን ሥራ በመዝሙር አመስግን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios