በእነርሱም ላይ ይህን ሁሉ የማደርግበት ምክንያት የቀድሞ አባቶቻቸው ከግብጽ ከወጡበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አሁን ድረስ ኃጢአት ሠርተው እኔን በማሳዘናቸውና ቊጣዬን በማነሣሣታቸው ነው።”
ሰቈቃወ 1:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከኃጢአትዋ ብዛት የተነሣ እግዚአብሔር ችግር እንዲደርስባት አደረገ፤ ጠላቶችዋ ገዢዎችዋ ሆነዋል፤ ልጆችዋም በጠላት ተማርከው ተወስደዋል ጠላቶችዋ ግን ተሳክቶላቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባላጋሮቿ ገዦቿ ሆኑ፤ ጠላቶቿ ተመችቷቸዋል፤ ከኀጢአቷ ብዛት የተነሣ፣ እግዚአብሔር ከባድ ሐዘን አምጥቶባታል። ልጆቿ በጠላት ፊት ተማርከው፣ ወደ ግዞት ሄደዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሄ። ስለ ኃጢአትዋ ብዛት እግዚአብሔር አስጨንቆአታልና አስጨናቂዎችዋ ራስ ሆኑ ጠላቶችዋም ተከናወነላቸው፥ ሕፃናቶችዋ በአስጨናቂዎች ፊት ተማርከዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሄ። ስለ ኀጢአቷ ብዛት እግዚአብሔር አዋርዶአታልና የሚዘባበቱባት በራስዋ ላይ ሆኑ፤ ጠላቶችዋም ተደሰቱ፤ ሕፃናቶችዋም በአስጨናቂዎች ፊት ተማርከዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሄ። ስለ ኃጢአትዋ ብዛት እግዚአብሔር አስጨንቆአታልና አስጨናቂዎችዋ ራስ ሆኑ ጠላቶችዋም ተከናወነላቸው፥ ሕፃናቶችዋ በአስጨናቂዎች ፊት ተማርከዋል። |
በእነርሱም ላይ ይህን ሁሉ የማደርግበት ምክንያት የቀድሞ አባቶቻቸው ከግብጽ ከወጡበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አሁን ድረስ ኃጢአት ሠርተው እኔን በማሳዘናቸውና ቊጣዬን በማነሣሣታቸው ነው።”
ይህ በራእይ ሸለቆ የጭንቅ፥ የመረገጥ፥ የሽብር ጊዜ ነው፤ ይህ ሁሉ በእኛ ላይ እንዲፈጸም የፈቀደው የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው፤ የከተማችን ቅጽሮች ፈራርሰው ወድቀዋል፤ ርዳታ ለማግኘት የሚደረገውም ጩኸት እስከ ተራራዎች በማስተጋባት ላይ ነው።
ድንኳኖቻችን ፈራረሱ፤ መወጠሪያ ገመዶችም ተቈራረጡ፤ ልጆቻችን በሙሉ ተሰደው ስለ ሄዱ፥ ድንኳኖቻችንን መልሶ የሚተክልልንና መጋረጃዎቻችንን የሚሰቅልልን አንድ እንኳ አልቀረም።”
ነገር ግን በኢየሩሳሌም የሚገኙ ነቢያትም ከዚህ የባሰ ክፋት ሲያደርጉ አይቼአለሁ፤ እነርሱ ያመነዝራሉ፤ ሐሰትም ይናገራሉ፤ ሰዎችን ለክፉ ሥራ ያነሣሣሉ፤ ከዚህም የተነሣ ሕዝቡ ከክፉ ሥራቸው አይመለሱም። ስለዚህ እነርሱ በእኔ ዘንድ እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ሕዝብ የከፉ ናቸው።
በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ የክብር ዘቡ አዛዥ ናቡዛርዳን በከተማ የቀሩትን ሕዝብና ቀደም ብለው ወደ እርሱ ከድተው የገቡትንም ሁሉ በአንድነት ሰብስቦ በእስረኛነት ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፤
“በትእዛዙ ላይ ያመፅሁ ስለ ሆነ፥ እግዚአብሔር ባደረገው ነገር እውነተኛ ነው፤ እናንተ ሕዝቦች ሁሉ አድምጡ ሥቃዬንም ተመልከቱ፤ ወጣቶች ወንዶችና ሴቶች ልጆቼ ተማርከው ተወስደዋል።
ኢየሩሳሌም ከባድ ኃጢአት ሠርታለች፤ መሳለቂያም ሆናለች፤ ዕርቃንዋን ስላዩአት የሚያከብሩአት ሁሉ ይንቁአታል፤ እርስዋ ራስዋ እየቃተተች ፊትዋን ታዞራለች።
እግዚአብሔር ያሰበውን ፈጸመ፤ ቀድሞ የተናገረውን ቃል ተግባራዊ አደረገ፤ ከረጅም ጊዜ በፊት በወሰነው መሠረት ያለ ርኅራኄ አፈራረሰ፤ ጠላት በእናንተ ላይ ደስ እንዲሰኝ አደረገ፤ የጠላቶቻችሁንም ኀይል አበረታ።
እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ፦ “የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ እጅግ የከፋ ኃጢአት በመሥራት በድለዋል፤ በምድሪቱ ሁሉ ላይ ግድያ ፈጽመዋል፤ ከተማይቱንም በዐመፅ የተሞላች አድርገዋታል፤ ‘እግዚአብሔር አገራችንን ትቶአታል፤ እኛንም አይመለከተንም’ ይላሉ፤
እኔ ከሞትሁ በኋላ ካዘዝኳቸው ትእዛዝ በመውጣት የርኲሰትን ሥራ እንደሚፈጽሙ ዐውቃለሁ፤ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራ በመሥራት ስለሚያስቈጡት መቅሠፍት ያመጣባቸዋል።”