እግዚአብሔር ይህን ያዘዛችሁ ከዚያ ዛፍ ፍሬ በበላችሁ ጊዜ እንደ እግዚአብሔር እንደምትሆኑና ደጉን ከክፉ ለይታችሁ እንደምታውቁ ስለሚያውቅ ነው”፤
ይሁዳ 1:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም እነዚህ ሰዎች በሕልማቸው እየተመሩ ሥጋቸውን ያረክሳሉ፤ ለባለ ሥልጣኖችም አይታዘዙም፤ በሰማይ ክብር ያላቸውንም ይሳደባሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ሁኔታ እነዚህ ሕልም ዐላሚዎች የገዛ ሥጋቸውን ያረክሳሉ፤ ሥልጣንን አይቀበሉም፤ በሰማይ ክብር ያላቸውንም ፍጥረታት ይሳደባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም በተመሳሳይ ሁኔታ እነዚህ ሕልመኞች ሥጋን ያረክሳሉ፥ ጌትነትን ይቃወማሉ፥ ክብር ያላቸውንም ይሳደባሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁም እነዚህ ሰዎች ደግሞ እያለሙ ሥጋቸውን ያረክሳሉ፤ ጌትነትንም ይጥላሉ፤ ሥልጣን ያላቸውንም ይሳደባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁም እነዚህ ሰዎች ደግሞ እያለሙ ሥጋቸውን ያረክሳሉ ጌትነትንም ይጥላሉ ሥልጣን ያላቸውንም ይሳደባሉ። |
እግዚአብሔር ይህን ያዘዛችሁ ከዚያ ዛፍ ፍሬ በበላችሁ ጊዜ እንደ እግዚአብሔር እንደምትሆኑና ደጉን ከክፉ ለይታችሁ እንደምታውቁ ስለሚያውቅ ነው”፤
የሚሰማብኝ የለም ብለህ በስውር እንኳ ቢሆን ንጉሥን አትማ፤ በተኛህበት አልጋህ ላይ ሆነህም ባለጸጋን አትስደብ፤ ምሥጢርህን የሰሙ ነገር ጠላፊዎች ክንፍ እንዳለው ወፍ በረው ሊነግሩብህ ይችላሉ።
እነርሱም በሙሴና በአሮን ፊት ተሰብስበው እንዲህ አሉአቸው፦ “እናንተ ከልክ አልፋችኋል! የዚህ ጉባኤ አባላት የሆኑ ሁሉ ለእግዚአብሔር የተለዩ ናቸው፤ እግዚአብሔርም ከእኛ ሁሉ ጋር ነው፤ ታዲያ በእግዚአብሔር ጉባኤ ላይ ራሳችሁን ከፍ ከፍ የምታደርጉት ስለምንድን ነው?”
“ሰዎች በየምኲራቡ ሲወስዱአችሁ፥ በገዢዎችና በባለሥልጣኖች ፊት ለፍርድ ሲያቀርቡአችሁ ‘ምን እንመልሳለን? እንዴትስ እንናገራለን?’ ብላችሁ አትጨነቁ።
ጳውሎስም “ወንድሞቼ ሆይ! የካህናት አለቃ መሆኑን አላወቅሁም ነበር፤ ምክንያቱም ‘በሕዝብህ አለቃ ላይ ክፉ ቃል አትናገር’ የሚል ተጽፎአል” አለ።
እንግዲህ ሰው የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነው፤ ይህም ቤተ መቅደስ እናንተ ናችሁ።
ለአመንዝሮችና ግብረ ሰዶምን ለሚያደርጉ፥ ሰውን አፍነው በመውሰድ ለሚሸጡ ነጋዴዎችና ለውሸታሞች፥ በሐሰት ለሚምሉና የእውነተኛ ትምህርት ተቃራኒ የሆነውን ነገር ሁሉ ለሚያደርጉ ነው፤
ለመሪዎቻችሁ ታዘዙ፤ በሥልጣናቸውም ሥር ሁኑ፤ እነርሱ የሚጠየቁበት ኀላፊነት ስላለባቸው ስለ ነፍሳችሁ ጉዳይ ይተጋሉ፤ እናንተ ብትታዘዙአቸው እነርሱ ሥራቸውን በደስታ ያከናውናሉ፤ ያለበለዚያ ሥራቸውን በሐዘን ይሠራሉ፤ ይህም እናንተን የሚጠቅም አይሆንም።