ከእናንተ አንዱ ሄዶ ወንድማችሁን ያምጣ፤ የተናገራችሁት እውነት መሆኑ ተረጋግጦ ነጻ እስክትለቀቁ ድረስ የቀራችሁት እዚሁ በእስር ቤት ትቈያላችሁ አለበለዚያ ግን በፈርዖን ስም እምላለሁ፤ እናንተ ሰላዮች ናችሁ።”
ኢያሱ 2:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የነዌ ልጅ ኢያሱ ከሺጢም ሰፈር ሁለት ሰላዮችን ላከ፤ እነርሱም የከነዓንን ምድር በተለይም የኢያሪኮን ከተማ በምሥጢር ሰልለው እንዲመለሱ አዘዛቸው፤ ወደ ከተማይቱ በመጡ ጊዜ “ረዓብ” ተብላ ወደምትጠራ ወደ አንዲት ሴትኛ ዐዳሪ ቤት ገብተው ዐደሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የነዌ ልጅ ኢያሱ፣ “ሄዳችሁ ምድሪቱን፣ በተለይም የኢያሪኮን ከተማ ሰልሉ” ብሎ ከሰጢም ሁለት ሰላዮች በስውር ላከ፤ ሰዎቹም ሄደው ረዓብ ከተባለች ጋለሞታ ቤት ገቡ፤ በዚያም ዐደሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የነዌም ልጅ ኢያሱ ከሰጢም ሁለት ሰላዮች በስውር እንዲህ ብሎ ላከ፦ “ሄዱ፥ ምድሪቱንና ኢያሪኮን እዩ።” ሄዱም፤ ረዓብም ወደሚሉአት አመንዝራ ቤት ገቡ፥ በዚያም አደሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የነዌም ልጅ ኢያሱ፥ “ውጡና ምድሪቱን ኢያሪኮን እዩ” ብሎ ከሰጢም ሁለት ጐልማሶች ሰላዮችን በስውር ላከ። እነዚያም ሁለት ጐልማሶች ሄዱ፤ ወደ ኢያሪኮም ደረሱ፤ ረዓብ ወደሚሉአትም ዘማ ቤት ገቡ፤ በዚያም ዐደሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የነዌም ልጅ ኢያሱ፦ ሄዳችሁ ምድሪቱንና ኢያሪኮን እዩ ብሎ ከሰጢም ሁለት ሰላዮች በስውር ላከ። ሄዱም፥ ረዓብም ወደሚሉአት ጋለሞታ ቤት ገቡ፥ በዚያም አደሩ። |
ከእናንተ አንዱ ሄዶ ወንድማችሁን ያምጣ፤ የተናገራችሁት እውነት መሆኑ ተረጋግጦ ነጻ እስክትለቀቁ ድረስ የቀራችሁት እዚሁ በእስር ቤት ትቈያላችሁ አለበለዚያ ግን በፈርዖን ስም እምላለሁ፤ እናንተ ሰላዮች ናችሁ።”
ስለ እነርሱ ያየው ሕልም ሁሉ ትዝ አለውና “እናንተ ሰላዮች ናችሁ፤ የመጣችሁትም የአገራችንን ደካማነት እምን ላይ እንደ ሆነ ለመሰለል ነው” አላቸው።
ሕዝቤ ሆይ! የሞአብ ንጉሥ ባላቅ ምን እንደ ዐቀደብህና የቢዖር ልጅ በለዓም ምን እንደ መለሰለት አስታውስ፤ ከሺጢም ተነሥተህ ወደ ጌልጌላ በምትሄድበት ጊዜ በመንገድ ላይ የሆነውን ሁሉ አስታውስ፤ ይህን ሁሉ ብታስታውስ አንተን ለማዳን ያደረግኹትን ሁሉ ታውቃለህ።”
“ከዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች አንዳንድ የሕዝብ መሪዎችን መርጠህ፥ እኔ ለእስራኤላውያን ወደምሰጣት ወደ ከነዓን ምድር ሄደው የምድሪቱን ሁኔታ መርምረው እንዲመለሱ ላካቸው፤”
አመንዝራም ቢሆን፥ ማናቸውንም የርኲሰት ሥራ የሚያደርግ ቢሆን፥ ወይም ጣዖት እንደ ማምለክ የሆነ ስግብግብነት ቢሆን፥ በክርስቶስና በእግዚአብሔር መንግሥት ርስት እንደማያገኝ ዕወቁ።
አመንዝራይቱ ረዓብ የእስራኤልን መልእክተኞች በቤትዋ በተቀበለች ጊዜና በሌላም መንገድ እንዲሄዱ ባደረገቻቸው ጊዜ እርስዋስ በሥራዋ ጸድቃ የለምን?
በማግስቱ ኢያሱና የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ማልደው ተነሡ፤ የሺጢምን ሰፈር ለቀው ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ሄዱ፤ ከመሻገራቸውም በፊት በዚያ ሰፈሩ፤
በላዪሽ ዙሪያ ያለውን አገር ሊያጠኑ ተልከው የነበሩት አምስት ሰዎች ለጓደኞቻቸው “በዚህ ስፍራ ከነዚህ ቤቶች በአንዱ ውስጥ በብር የተለበጠ የእንጨት ጣዖት እንዳለ ታውቃላችሁን? ሌሎች ጣዖቶች አንድ ኤፉድም በተጨማሪ አለ፤ ታዲያ ምን ማድረግ የሚገባን ይመስላችኋል?” አሉአቸው።
አምስቱም ሰላዮች በቀጥታ ወደ ሚካ ቤት ገብተው ያንን በብር የተለበጠ የእንጨት ጣዖትና ሌሎቹንም ጣዖቶች ኤፉዱንም ጭምር ወሰዱ፤ ይህም በሚሆንበት ጊዜ ካህኑ የጦር መሣሪያ ከታጠቁት ስድስት መቶ ሰዎች ጋር በቅጽር በሩ አጠገብ ቆሞ ነበር።
ስለዚህ የዳን ሕዝብ ከነገዱ ቤተሰቦች መካከል ብርታት ያላቸውን አምስት ሰዎች መረጡ፤ ምድሪቱንም አጥንተው እንዲመለሱ መመሪያ በመስጠት ከጾርዓና ከኤሽታኦል ከተሞች ላኩአቸው፤ እነርሱም ኮረብታማ ወደ ሆነው ወደ ኤፍሬም አገር በደረሱ ጊዜ በሚካ ቤት አደሩ፤