ኢያሱ 15:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዖትኒኤልም በሠርጋቸው ቀን ዓክሳን ከአባትዋ የእርሻ መሬት እንድትለምን መከራት፤ እርስዋም ከበቅሎዋ ላይ ወረደች፤ (መሳ 1፥14 ተመልከት) ካሌብም “ምን ትፈልጊአለሽ” ሲል ጠየቃት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዓክሳ ወደ ጎቶንያል በመጣች ጊዜም፣ ከአባቷ ላይ የዕርሻ መሬት እንዲለምን አጥብቃ ነገረችው። ከአህያዋ ላይ እንደ ወረደች ካሌብ፣ “ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ?” ሲል ጠየቃት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም ወደ እርሱ በመጣች ጊዜ ከአባትዋ እርሻ እንዲለምን መከረችው፤ እርሷም ከአህያዋ ወረደች፤ ካሌብም፦ “ምን ፈለግሽ?” አላት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም ወደ እርሱ በመጣች ጊዜ “አባቴን እርሻ ልለምነው” ብላ አማከረችው፤ እርስዋም በአህያዋ ላይ ሆና ጮኸች፤ ካሌብም፥ “ምን ሆንሽ?” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም ወደ እርሱ በመጣች ጊዜ ከአባትዋ እርሻ እንዲለምን መከረችው፥ እርስዋም ከአህያዋ ወረደች፥ |
እርስዋም “የሰጠኸኝ ምድር ደረቅ ስለ ሆነ ጥቂት የውሃ ጒድጓዶች እንድትሰጠኝ እፈልጋለሁ” አለችው። ካሌብም ከላይና ከታች በኩል ያሉትን ሁለቱን የውሃ ምንጮች ሰጣት።
በጋብቻቸውም ቀን ዖትኒኤል ዓክሳን “አባትሽ የእርሻ መሬት እንዲሰጥሽ ጠይቂ” አላት፤ እርስዋም ካሌብን ስታይ ከበቅሎዋ ላይ ወረደች፤ ካሌብም “ምን እንድሰጥሽ ትፈልጊአለሽ” ብሎ ጠየቃት።