ኢያሱ 10:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢያሱም ሌሊቱን ሙሉ ከጌልጌላ ወደ ገባዖን ሲገሠግሥ ዐድሮ በአሞራውያን ላይ ድንገተኛ አደጋ ጣለባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢያሱ ከጌልገላ ሌሊቱን ሁሉ ሲገሠግሥ ዐድሮ ድንገት ወረራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም ከጌልገላ ሌሊቱን ሁሉ ገሥግሦ በድንገት መጣባቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም ከጌልገላ ሌሊቱን ሁሉ ገሥግሦ በድንገት ደረሰባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም ከጌልገላ ሌሊቱን ሁሉ ገሥግሦ በድንገት መጣባቸው። |
እግዚአብሔርም በእስራኤል ሠራዊት ፊት አሞራውያን በድንጋጤ እንዲሸበሩ አደረገ፤ እስራኤላውያንም እነርሱን በገባዖን ዐረዱአቸው፤ የቀሩትንም በቤትሖሮን በኩል እስከ ተራራው መተላለፊያ ቊልቊለት እስከ ዐዜቃና እስከ ማቄዳ ድረስ አሳደዱአቸው።
እግዚአብሔርም ኢያሱን “እነርሱን አትፍራቸው፤ እኔ አንተን በእነርሱ ላይ ድልን አቀዳጅሃለሁ፤ ከእነርሱ አንድም የሚቋቋምህ አይኖርም” አለው።