ሃማን ከግብዣው ወጥቶ ሲሄድ እጅግ ተደስቶ በልቡም ሐሴት ያደርግ ነበር፤ ነገር ግን ወደ ቤተ መንግሥቱ በሚያስገባው በር አጠገብ መርዶክዮስን ተቀምጦ አየው፤ አልፎም ሲሄድ መርዶክዮስ ከተቀመጠበት ስፍራ እንዳልተነሣለትና ምንም ዐይነት አክብሮት እንዳላሳየው በተመለከተ ጊዜ ሃማን መርዶክዮስን እጅግ ተቈጣው፤
ዮናስ 4:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥላ በማግኘት ከፀሐይ ግለት እንዲድን እግዚአብሔር አምላክ አንድ የቅል ተክል አብቅሎ ቅጠሎችዋ ከዮናስ ራስ በላይ እንዲሆኑ አደረገ፤ ዮናስም ከቅሉ ሐረግ ጥላ በማግኘቱ እጅግ ተደሰተ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር አምላክም የቅል ተክል አብቅሎ፣ የዮናስ ራስ ጥላ እንዲያገኝና ሙቀትም እንዳያስጨንቀው ከበላዩ እንዲያድግ አደረገ፣ ዮናስም ስለ ቅሉ እጅግ ደስ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔርም የጉሎ ተክል አበቀለ፥ ከጭንቀቱም እንድታድነው፥ በራሱ ላይ ጥላ እንድትሆን በዮናስ ራስ ላይ ከፍ ከፍ እንድትል አደረጋት፤ ዮናስም ስለ ጉሎ ተክሉ እጅግ ተደሰተ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር አምላክም ቅልን አዘዘ፤ ከጭንቀቱም ታድነው ዘንድ በራሱ ላይ ጥላ እንድትሆን በዮናስ ራስ ላይ ከፍ ከፍ አደረጋት፤ ዮናስም ስለ ቅሊቱ እጅግ ደስ አለው። |
ሃማን ከግብዣው ወጥቶ ሲሄድ እጅግ ተደስቶ በልቡም ሐሴት ያደርግ ነበር፤ ነገር ግን ወደ ቤተ መንግሥቱ በሚያስገባው በር አጠገብ መርዶክዮስን ተቀምጦ አየው፤ አልፎም ሲሄድ መርዶክዮስ ከተቀመጠበት ስፍራ እንዳልተነሣለትና ምንም ዐይነት አክብሮት እንዳላሳየው በተመለከተ ጊዜ ሃማን መርዶክዮስን እጅግ ተቈጣው፤
ሕዝቅያስም መልእክተኞቹን በደስታ ተቀበላቸው፤ በቤተ መንግሥቱም የዕቃ ግምጃ ቤት ያለውን ሀብት በሙሉ ብሩንና ወርቁን፥ ቅመማ ቅመሙንና፥ ሽቶውን፥ የጦር መሣሪያውንና በዕቃ ቤት ያለውን ንብረት ሁሉ አሳያቸው፤ በቤተ መንግሥቱ ግምጃ ቤትም ሆነ በመንግሥቱ በማንኛውም ስፍራ ካለው ሀብት ሁሉ ሕዝቅያስ ያላሳያቸው ምንም ነገር አልነበረም።
ዮናስም ከከተማይቱ ወጥቶ ከከተማይቱም በስተ ምሥራቅ በኩል ዳስ በመሥራት ከጥላው ሥር ተቀመጠ፤ በዚያም ሆኖ በነነዌ ላይ የሚደርሰውን ነገር ይጠባበቅ ነበር።