Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዮናስ 4:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ቅልን አዘዘ፤ ከጭ​ን​ቀ​ቱም ታድ​ነው ዘንድ በራሱ ላይ ጥላ እን​ድ​ት​ሆን በዮ​ናስ ራስ ላይ ከፍ ከፍ አደ​ረ​ጋት፤ ዮና​ስም ስለ ቅሊቱ እጅግ ደስ አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እግዚአብሔር አምላክም የቅል ተክል አብቅሎ፣ የዮናስ ራስ ጥላ እንዲያገኝና ሙቀትም እንዳያስጨንቀው ከበላዩ እንዲያድግ አደረገ፣ ዮናስም ስለ ቅሉ እጅግ ደስ አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ጌታ እግዚአብሔርም የጉሎ ተክል አበቀለ፥ ከጭንቀቱም እንድታድነው፥ በራሱ ላይ ጥላ እንድትሆን በዮናስ ራስ ላይ ከፍ ከፍ እንድትል አደረጋት፤ ዮናስም ስለ ጉሎ ተክሉ እጅግ ተደሰተ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ጥላ በማግኘት ከፀሐይ ግለት እንዲድን እግዚአብሔር አምላክ አንድ የቅል ተክል አብቅሎ ቅጠሎችዋ ከዮናስ ራስ በላይ እንዲሆኑ አደረገ፤ ዮናስም ከቅሉ ሐረግ ጥላ በማግኘቱ እጅግ ተደሰተ።

Ver Capítulo Copiar




ዮናስ 4:6
11 Referencias Cruzadas  

ወይም ጌታ​ውን እን​ደ​ሚ​ፈራ አገ​ል​ጋይ ጥላ​ው​ንም እን​ደ​ሚ​መኝ፥ ወይም ደመ​ወ​ዙን እን​ደ​ሚ​ጠ​ብቅ ምን​ደኛ አይ​ደ​ለ​ምን?


በእርሱ ላይ ዐይንህን ብታተኩር አታገኘውም፥ ለእርሱ የንስር ክንፍ ተዘጋጅቶለታልና። ወደሚቆምበትም ቤት ይመለሳልና።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ስለ እነ​ርሱ እጅግ ደስ አለው፤ ግምጃ ቤቱ​ንም፥ ወር​ቁ​ንና ብሩን፥ ከር​ቤ​ው​ንና ዕጣ​ኑን፥ ዘይ​ቱ​ንም፥ መሣ​ሪ​ያም ያለ​በ​ትን ቤት ሁሉ፥ ልብ​ሱ​ንና ዕን​ቍ​ውን ሁሉ፥ በቤተ መዛ​ግ​ብ​ቱም የተ​ገ​ኘ​ውን ሁሉ አሳ​ያ​ቸው፤ በቤ​ቱና በግ​ዛቱ ሁሉ ካለው ሕዝ​ቅ​ያስ ያላ​ሳ​ያ​ቸው የለም።


በከ​ንቱ ነገር ደስ የሚ​ላ​ችሁ በኀ​ይ​ላ​ችን ቀን​ዶ​ችን አበ​ቀ​ልን የም​ትሉ አይ​ደ​ለ​ምን?


ዮና​ስም ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ወጣ፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ፊት ለፊት ተቀ​መጠ፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም የሚ​ሆ​ነ​ውን እስ​ኪ​ያይ ድረስ በዚያ ለራሱ ዳስ ሠርቶ ከጥ​ላው በታች ተቀ​መጠ።


በነ​ጋው ግን ወገግ ባለ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትልን አዘዘ፤ እር​ስ​ዋም ቅሊ​ቱን መታ​ቻት፤ ደረ​ቀ​ችም።


ነገር ግን አጋ​ን​ንት ስለ ተገ​ዙ​ላ​ችሁ በዚህ ደስ አይ​በ​ላ​ችሁ፤ ግን ስማ​ችሁ በሰ​ማ​ያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበ​ላ​ችሁ።”


ያለ​ቀሱ እን​ዳ​ላ​ለ​ቀሱ ይሆ​ናሉ፤ ደስ ያላ​ቸ​ውም ደስ እን​ዳ​ላ​ላ​ቸው ይሆ​ናሉ፤ የሸ​ጡም እን​ዳ​ል​ሸጡ ይሆ​ናሉ፤ የገ​ዙም እን​ዳ​ል​ገዙ ይሆ​ናሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos