Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




አስቴር 5:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ሃማን ከግብዣው ወጥቶ ሲሄድ እጅግ ተደስቶ በልቡም ሐሴት ያደርግ ነበር፤ ነገር ግን ወደ ቤተ መንግሥቱ በሚያስገባው በር አጠገብ መርዶክዮስን ተቀምጦ አየው፤ አልፎም ሲሄድ መርዶክዮስ ከተቀመጠበት ስፍራ እንዳልተነሣለትና ምንም ዐይነት አክብሮት እንዳላሳየው በተመለከተ ጊዜ ሃማን መርዶክዮስን እጅግ ተቈጣው፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ሐማ በዚያ ቀን ደስ ብሎትና መንፈሱ ረክቶ ወጣ፤ ነገር ግን መርዶክዮስን በንጉሡ በር ላይ ሲያየው ከተቀመጠበት አለመነሣቱንና በፊቱም አለመንቀጥቀጡን ሲመለከት፣ ቍጣው በመርዶክዮስ ላይ ነደደ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 በዚያም ቀን ሐማ ደስ ብሎት በልቡም ተደስቶ ወጣ፥ ነገር ግን መርዶክዮስ በንጉሡ በር ያለ መነሣትና ያለ መናወጥ ተቀምጦ ባየ ጊዜ ሐማ በመርዶክዮስ ላይ እጅግ ተቈጣ።

Ver Capítulo Copiar




አስቴር 5:9
19 Referencias Cruzadas  

አክዓብ፥ የእዝራኤላዊው ናቡቴ “ከአባቶቼ የወረስኩትን ለአንተ አልሰጥህም!” ስላለው በንዴት እየተበሳጨ ወደ ቤቱ ገባ፤ ፊቱንም ወደ ግድግዳ አዙሮ በአልጋው ላይ ተጋደመ፤ ምግብ መብላትም አልፈቀደም።


እርሱም “እኔን ያበሳጨኝ ከናቡቴ ያገኘሁት መልስ ነው፤ ይኸውም የእርሱን የወይን ተክል ቦታ እንድገዛ ወይም ከፈለገ ልዋጩን እንድሰጠው ብጠይቀው የወይን ተክል ቦታውን ‘በምንም ዐይነት አልሰጥህም’ ብሎ አናደደኝ” ሲል መለሰላት።


ደናግሉ ዳግመኛ በተሰበሰቡ ጊዜ መርዶክዮስ በንጉሡ ቤተ መንግሥት በር ላይ ሥልጣን ተሰጥቶት ነበር።


ንጉሡም በግዛቱ ሥር ያሉ ባለሥልጣኖች ሁሉ በጒልበታቸው ተንበርክከው እየሰገዱ እጅ በመንሣት ያከብሩት ዘንድ አዘዘ፤ እነርሱም ሁሉ እንደ ታዘዙት አደረጉ፤ ይህን ለማድረግ እምቢ ያለ መርዶክዮስ ብቻ ነበር።


ሃማንም መርዶክዮስ ተንበርክኮ የማይሰግድለት መሆኑን ባየ ጊዜ እጅግ ተቈጣ።


ነገር ግን ያን አይሁዳዊ መርዶክዮስን በቤተ መንግሥቱ መግቢያ በር አጠገብ ተቀምጦ በማየቴ ይህ ሁሉ ክብር ለእኔ ምንም ትርጒም ሊሰጠኝ አልቻለም።”


የክፉ ሰው ድንፋታ ለአጭር ጊዜ ነው፤ እግዚአብሔርንም የሚክዱ ሰዎች ደስታቸው በቅጽበት የሚጠፋ ነው።


በእርግጥ ቤተሰቦቼ ‘ከእርሱ ዘንድ ምግብ በልቶ ያልጠገበ ከቶ ማነው?’ ብለው ይመሰክራሉ።


ክፉ ሰዎችን የሚንቅ፥ ለእግዚአብሔር የሚታዘዙትን ግን የሚያከብር፥ ምንም ያኽል ከባድ ቢሆን የገባውን ቃል ኪዳን የሚፈጽም፥


ብዙ ሠራዊት ቢከበኝም አልፈራም፤ ጠላቶቼ በጦርነት ቢያጠቁኝ እንኳ በእግዚአብሔር መተማመኔን አልተውም።


ንጉሡ ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጥቶ ሲድራቅ፥ ሚሳቅና አብደናጎ እንዲጠሩ አዘዘ፤ እነርሱም መጥተው በንጉሡ ፊት ቀረቡ።


ሥጋን ከመግደል አልፈው ነፍስን መግደል የማይችሉትን ሰዎች አትፍሩ፤ ይልቁንስ ነፍስንና ሥጋን በገሃነም ሊያጠፋ የሚችለውን አምላክ ፍሩ።


ከዚያ በኋላ ሄሮድስ፥ የከዋክብት ተመራማሪዎቹ እንዳታለሉት በተገነዘበ ጊዜ፥ በጣም ተቈጣ፤ ወደ ቤተልሔምና በዙሪያዋም ወዳሉት መንደሮች ሁሉ ወታደሮቹን ልኮ፥ ከከዋክብት ተመራማሪዎቹ በተረዳው ዘመን መሠረት፥ ዕድሜአቸው ሁለት ዓመት የሆናቸውንና ከዚያ በታች የሆኑትን በቤተልሔምና በአካባቢው የነበሩትን ወንዶች ሕፃናትን አስገደለ።


“እናንተ አሁን የጠገባችሁ፥ ኋላ ትራባላችሁና ወዮላችሁ! እናንተ አሁን የምትስቁ፥ ኋላ ስለምታዝኑና ስለምታለቅሱ ወዮላችሁ!


እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ እናንተ ታለቅሳላችሁ፤ ትጮኻላችሁም፤ ዓለም ግን ደስ ይለዋል፤ እናንተ ታዝናላችሁ፤ ነገር ግን ሐዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል።


የሸንጎ አባሎች ይህን በሰሙ ጊዜ ተናደዱ፤ በእስጢፋኖስ ላይም በቊጣ ጥርሳቸውን አፋጩ።


ተጨነቁ፤ እዘኑ፤ አልቅሱ፤ ሳቃችሁ ወደ ለቅሶ፥ ደስታችሁ ወደ ሐዘን ይለወጥ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos