ዮናስ 1:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ግን በባሕሩ ላይ ከባድ ነፋስን አስነሣ፤ በባሕሩም ላይ የተቀሰቀሰው ማዕበል ብርቱ ከመሆኑ የተነሣ መርከቢቱ ልትሰበር ተቃረበች፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም በባሕሩ ላይ ታላቅ ነፋስን ላከ፤ ከባድ ማዕበልም ተነሥቶ መርከቢቱን አንገላታት፤ ልትሰበርም ተቃረበች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ግን በባሕሩ ላይ ታላቅ ነፋስን አስነሣ፥ በባሕሩም ላይ ታላቅ ማዕበል ተነሣ፥ መርከቢቱም ልትሰበር ቀረበች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም በባሕሩ ላይ ታላቅ ነፋስን አመጣ፤ በባሕሩም ላይ ታላቅ ማዕበል ሆነ፤ መርከቢቱም ልትሰበር ቀረበች። |
ስለዚህ ሙሴ በግብጽ ምድር ላይ እጁን ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም በዚያን ቀንና ሌሊት የምሥራቅ ነፋስ አስነሣ፤ በነጋም ጊዜ ያ የምሥራቅ ነፋስ አንበጦችን አመጣ።
እግዚአብሔርም የምሥራቁን ነፋስ የሚቋቋምና አንበጦቹንም ጠራርጎ ወደ ቀይ ባሕር የሚነዳ ብርቱ ነፋስ ከምዕራብ በኩል አስነሣ፤ በዚህ ዐይነት በመላው የግብጽ ምድር አንድ አንበጣ እንኳ አልቀረም።
ሙሴ እጁን በባሕሩ ላይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም በብርቱ የምሥራቅ ነፋስ ባሕሩን ወደ ኋላ መለሰው፤ ነፋሱም ሌሊቱን ሙሉ በመንፈሱ፥ ባሕሩን ወደ ደረቅ ምድር ለወጠው፤ ውሃውም ከሁለት ተከፈለ፤
በሰማይ ያለው ውሃ በእርሱ ትእዛዝ ይናወጣል፤ እርሱ ደመናትን ከምድር ዳርቻ ያመጣል፤ ከዝናብ ጋርም መብረቅ እንዲበርቅ ያደርጋል፤ ከማከማቻው በማውጣት ነፋስ እንዲነፍስ ያደርጋል።
ተራራዎችን የሠራ፥ ነፋሶችን የፈጠረ፥ ያሰበውን ነገር ለሰው የሚገልጥ፥ የቀኑን ብርሃን ወደ ጨለማ የሚለውጥ፥ በምድር ከፍታዎች ላይ የሚራመድ፥ ስሙ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው።
በድንገትም እግዚአብሔር ድርጭቶችን ከባሕር እየነዳ የሚያመጣ ነፋስ ላከ፤ ድርጭቶችም ከምድር አንድ ሜትር ያኽል ከፍ ብለው እየበረሩ መጡ፤ በሰፈሩና በሰፈሩ ዙሪያ የተከማቹበት ስፍራ የአንድ ቀን መንገድ ያኽል ነው፤